ዶ/ር መራራ ጉዲና አሜሪካን ሀገር ገብተዋል

Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 10 ቀን 2002 ዓ.ም. March 19, 2010)፦ መድረክ በሚሳተፍበት የመጭው 2002 ዓ.ም. ምርጫ የገንዘብ ማሰባሰብና ከደጋፊዎቹ ጋር ለመወያየት አንድ የልዑካን ቡድን ሊልክ በዝግጅት ላይ መሆኑን የድርጅቱ አመራር አባል ዶ/ር መራራ ጉዲና በተለይ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጹ።

 

ዶ/ር መራራ የልዑካን ቡድኑ ለሚያካሂደው ተልዕኮ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ በአሜሪካዋ ከተማ ሲያትል ቀድመው የተገኙ ሲሆን፤ የልዑካን ቡድኑ ዋና ዓላማ በመጭው ግንቦት ይካሄዳል በሚካሄደው ምርጫ መድረክ ዝግጅት ከማድረጉም በላይ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በዚሁ ምርጫ ላይ የሚያበረክቱት አስተዋጽዖ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

 

የልዑካን ቡድኑ በመጀመሪያ የመድረክን አቋም ማስተዋወቅና ለምርጫው ማስኬጃ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰብን ዓላማ ያደረገ ሲሆን፤ በቀጣይነትም አንድነት ለዲሞክራሲ ፓርቲ ተመሳሳይ ቅስቀሳና ውይይቶችን በአሜሪካና በአውሮፓ እንደሚያደርግ ዶ/ር መራራ ገልጸዋል።

 

የልዑካን ቡድኑ የዘገየበት ምክንያትም የአሜሪካ መግቢያ ፈቃድ (ቪዛ) ለማግኘት ምላሽ በመጠባበቅ ላይ በመሆኑ እንደሆነ አስረድተዋል።

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!