Haile GebreselassieEthiopia Zare (ሰኞ ኅዳር 6 ቀን 2003 ዓ.ም. November 15, 2010)፦ በረዥም ርቀት ውድድሮች ተደጋጋሚ የክብረ ወሰኖች ባለቤት የሆነው ኃይሌ ገብረሥላሴ በድጋሚ ወደ ሩጫ እንደሚመለስ በክብር እንግድነት የተገኘበት ነቀምት ከተማ ህዝብ ፊት በመቅረብ ይፋ አደረገ። ከኒው ዮርኩ ውድድር ነኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በቀጣይ ለሚደረገው የለንደኑ ውድድር ዝግጅቱን እንደሚቀጥልም አብስሯል።

 

ኃይሌ ኒው ዮርክ ውስጥ በተደረገ የአገር አቋራጭ ውድድር ጉልበቱ ላይ በታየ ፈሳሽ ምክንያት ከአሁን በኋላ ይብቃኝ በማለት ከአትሌቲክሱ አለም ራሱን ማግለሉን ሀዘኑን መቆጣጠር በማይችልበት ሁኔታ ሲገልጽ በአትሌቲክስ አድናቂዎችና ቤተሰቦች ዘንድ ከፍተኛ የሀዘን ድባብ መስተጋባቱ የሚታወስ ሲሆን በበርካቶች ዘንድ የተለያዩ አስተያየቶች ሲደመጡ መሰንበታቸው ይታወቃል።

 

ብዙ ውትወታ ሲደርስበት የሰነበተው ኃይሌ ለመጀመሪያ ጊዜ ወለጋ - ነቀምት ውስጥ በተደረገ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ተገኝቶ ባደረገው ንግግር ወደ ሩጫ ለመመለስ መወሰኑን ባበሰረበት ወቅት በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ጩኸትና ሁካታ መስተጋባቱን ከስፍራው የደረሰን ሪፖርት አብራርቷል። ኃይሌ ከአሁን በኃላ ከሁለት አመት በላይ መሮጥ እንደሚችል የህክምና ባለሙያዎቹ ሲገልጹ መሰማታቸው የሚታወስ ነው።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ