- በፍርድ ቤት አካባቢ ህዝቡ በእጥፍ ጨምሯል

- ችሎቱ ሰፊ አዳራሽ ውስጥ ነበር

Teddy Afro

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሚያዝያ 15 ቀን 2000 ዓ.ም. April 23, 2008) ቴዲ አፍሮ ዛሬ ወደ ችሎት ሲቀርብ በርካታ አድናቂዎቹና ጋዜጠኞች እንዲሁም ብዛት ያላቸው የፍርድ ቤቱ ሰራተኞች ከአሁን በፊት ከነበረው ችሎት ሰፋ ወዳለ አዳራሽ የተቀየረውን ቦታ አጨናንቀውት እንደነበር የአዲስ አበባ ሪፖርተራችን ዘገበ።

 

እንደዘጋቢያችን ገለጻ ቀድሞ ቴዲ አፍሮ ይቀርብበት የነበረው የስምንተኛ ወንጀል ችሎት ጠባብ ከመሆኑና የፍርድ ሂደቱን ለመከታተል የቀረበው ህዝብ ጋር በፍጹም ሊመጣጠን ካለመቻሉ የተነሳ በሰፊ አዳራሽ የተሰየመውና በአቶ ልዑል ገ/ማሪያም ዳኝነት የሚካሄደው ችሎት ዓቃቤ ሕግ አሻሽዬና አብራርቼ አቅርቤያለሁ ያለውን ክስ በመስማት ነበር ችሎቱ የተጀመረው።

 

እንደ ዓቃቤ ሕግ ክስ በቴዲ ላይ የቀረበው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀጽ 543 ንዑስ ቁጥር 3 ሲሆን፣ ከ10 እስከ 15 ዓመት ሊያስፈርድበት የሚችል መሆኑ የተለጸ ሲሆን፣ በትራንስፖርትና መገናኛ በ1959 የወጣውን አዋጅ በመጥቀስም ያለመንጃ ፈቃድ በማሽከርከር የሚል በክሱ ላይ የተካተተ መሆኑን ለማወቅ ችለናል።

 

ተሻሻለ የተባለው ክስ ጸንቶ ከቀረበ በኋላ የተከሳሹ ጠበቃ የዋስትና መብታችን መጠበቅ አለበት ሲል የመከራከሪያ ነጥብ ያቀረበ ሲሆን፣ መከራከሪያቸውም ፕላኑ ከተነሳ በኋላ የፈረሙ ምስክሮች እንጅ የይን ምስክር ባለመኖሩና የቀረቡት ማስረጃዎች የሰነድ ብቻ በመሆናቸው የዋስትና መብታችን መፈቀድ አለበት ሲሉ አቅርበዋል።

 

የተከሳሽ ጠበቃ የተቃወመው ዓቃቤ ሕግ፤ የቀረበበትን አንቀጽ እንጅ ምስክሮችንና ሰነድን መመልከት አይገባም በማለትና ከአሁን በፊት በዚህ አንቀጽ የተከሰሰ የዋስትና መብት አልተሰጠም ለእሱም በምንም ምክንያት የዋስትና መብት ሊፈቀድለት አይገባም ሰሉ የተከራከረ መሆኑን የደረሰን ዘባ ያስረዳል።

 

ከክርክሩ በኋላ ተከሳሽ ቴዎድሮስ ካሳሁን የእምነት ክህደት ቃሉን እንዲሰጥ የተጠየቀ ሲሆን ድርጊቱን አልፈምኩም ጥፋተኛም አይደለሁም ሲል የእምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቷል።

 

ዳኛውም የዋስትናውን ክርክር በመመለከት የግራና የቀኙን ክርክር በማየት ውሳኔ ለምጠት ለማክሰኞ ሚያዚያ 21 ቀን 2000 ዓ.ም. ጠዋት ሶስት ሰአት ተኩል ቀጠሮ በመስጠት ችሎቱን ዘግተው አሰናብተዋል።

 

ችሎቱን ለመከታተል የመጣው ህዝብ የወከባና የፌደራል ፖሊስ የዱላ ውርጅብኝ የደረሰበት ሲሆን ሰው በተቀናጀ መልኩ ወደፍርድ ቤቱ አካባቢ የታየ በመሆኑ የህይወትና የንብረት አደጋ ያልደረሰ ሞኑን ለመረዳት ተችሏል።

 

የቴዲ አፍሮን የፍርድ ሂደት በሚመለከት አንድ የህግ ባለሙያ አነጋግረን በሰጡን ምላሽ ማናቸውንም አይነት ወንጀል የሰራ ግለሰብም ሆነ ቡድን ለፍርድ መቅረብ ያለበት ቢሆንም የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጉዳይ ለአመት ከስድስት ወር በላይ አቆይቶ አቃቢህግ ለፍርድ ቤቱ ማቅረቡ አስገራሚና ኢፍትሃዊ ነው ሲለ አስተያየታቸውን ሰጠተዋል።

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!