ሂላሪ ክሊንተን የአዲስ አበባ ጉብኝታቸውን አቋረጡ

Ethiopia Zare (ሰኞ ሰኔ 6 ቀን 2003 ዓ.ም. June 13, 2011)፦ ትላንት እሁድ ምሽት ላይ በቀይ ባህር በስተደቡብ ክልል በተከሰተ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ምክንያት በአዲስ አበባ የነበሩት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሂላሪ ክሊንተን በአፋጣኝ ሀገር መልቀቃቸው ተዘገበ።

 

ወ/ሮ ክሊንተን በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ የአምባገነንነትን አስከፊ ገጽታ የቱኒዚያውን ህዝባዊ አመጽ በማጣቀስ እና የሊቢያውን መሪ ሞሀመድ ጋዳፊን አፍሪካውያኖች መደገፍ በማቆም ለአማጽያኑ እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀረበ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ከአቶ መለስ ዜናዊ ጋርም ውይይት አድርገዋል።

 

ወ/ሮ ሂላሪ ከተለያዩ ጋዜጠኞች ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ይሰጣሉ ተብለው የተጠበቁ ቢሆንም፣ በኤርትራ በተነሳው የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ብናኝ ጉዟቸው እንዳይስተጓጎል ጠቅላላ የጉብኝት ጊዜያቸውን እንዳቋረጡ ለማወቅ ተችሏል።

 

በቀይ ባህር አካባቢ የተነሳው እሳተ ገሞራ በርእደ ምድር መለኪያ 5.7 እንደሚደርስ የታወቀ ሲሆን፣ በንብረትና በሰው ላይ ያደረሰው ጉዳት አልተገለጸም።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ