የሕወሀት ቱባ ባለስልጣናት በሚስጢር ተከታታይ ስብሰባዎችን እያደረጉ ነው

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሐምሌ 12 ቀን 2004 ዓ.ም. July 19, 2012)፦ የጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የጤና ሁኔታ አሁንም አወዛጋቢነቱ የቀጠለ ሲሆን በቤጂየም ሆስቲታል በኢንቴንሲቭ ኬር ክፍል አካባቢ ጠባቂዎቻቸውን የተመለከተ ኢትዮጵያዊ ይፋ አደረገ። የህወሃት ቱባ ባለስልጣናት በሀገር ቤት በሚስጥር በተደጋጋሚ ስብሰባዎችን እያደረጉ መሆኑም ታውቋል።

 

 

በጽኑ መታመማቸው በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ለመጀመሪያ ጊዜ በሰበር ዜና የተገለጸውና ከሳምንታት በኋላ በመላ አለም በሚገኙ ታላላቅ የመገናኛ ብዙሀን አውታራት ዘንድ ዋና ርእስ የሆነው የአቶ መለስ የጤና ሁናቴ በባለስልጣናት በኩል በሽታው የከፋ አይደለም የሚል ማስተባበያ እየተሰጠው ቢሆንም የጤናቸው ሁኔታ ከእለት እለት የከፋ መሆኑን ዘገባዎች እያስረዱ ይገኛሉ።

 

ቤልጅየም ብራሰልስ የሚገኝ አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ ታማኝ ኢትዮጵያዊ የአቶ መለስን ሁለት ጠባቂዎች ብራሰልስ በሚገኘው የSaint Luc University Hospital ሁለተኛ ፎቅ ላይ እንዳያቸው ገልጾ ባለፈው አርብ ጁላይ 14 ለሕክምና ቀጠሮው ወደ ሆስፒታሉ በሄደበት ጊዜ በቴሌቪዥን የተመከታቸውን የአቶ መለስን የግል ጠባቂዎችና አቶ ብርሃነ ገብረክርስቶስን እንደተመለከተና፤ ጠባቂዎቹ እሱን ሲያዩት እንደተርበተበቱ ተናግሯል። በሆስፒታሉ ሁለተኛው ፎቅ የ”ኢንቴንሲቭ ኬር” ክፍሎች ያሉበት ስለሆነ፤ አቶ መለስ የተኙት እዚያ ሊሆን እንደሚችል ይህ ኢትዮጵያዊ ጠቁሟል። ኢትዮጵያዊው ባለፈው ማክሰኞ በዚሁ አቶ መለስ በተኙበት ሆስፒታል ሌላ ቀጠሮ የነበረው ቢሆንም፤ ሆስፒታሉ ዶክተሩ አይመቸውም በሚል ቀጠሮውን ለሌላ ቀን እንዳራዘሙበት ገልጿል።

 

በተያያዘም የአቶ መለስ የጤና ሁኔታ ከተባባሰበትና ወደቤልጂየም ከተጓዙበት ጊዜ ጀምሮ የሕወሀት ፖሊት ቢሮና ማእከላዊ ምክር ቤት አባላት ተከታታይ ዝግ ስብሰባዎችን እያደረጉ ሲሆን፤ ለአራት ቀናት ባለቤታቸውን ሲያስታምሙ የሰነበቱት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ባለፈው እሁድ ሌሊት ወደኢትዮጵያ ከተመለሱ በሁዋላም ይሄው ስብሰባ ቀጥሏል። ሚስጥራዊው ስብሰባ ሌሎች የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችን ያላካተተ መሆኑን ምንጮች ይፋ አድርገዋል።

 

አቶ መለስ በህይወት ቢተርፉም ዘላቂ እንደማይሆንና አስጊ ደረጃ ላይ እንዳሉ የዘገቡት ታላላቅ የመገናኛ ብዙሀን እንደገለጹት ከሆነ በኢትዮጵያ መጻኢ ሁኔታ ላይ ምንም አይነት ድርሻ ሊኖራቸው እንደማይችል የታመነበት ሆኗል።

 

ፓርላማው ተሰብስቦ የምክር ቤቱን የመጨረሻ ውሳኔ እንዲያጸድቅ የተወሰነውም ወ/ሮ አዜብ ወደኢትዮጵያ ከተመለሱ በሁዋላ እንደሆነና፤ የሕወሀት ፖሊት ቢሮ የተጠባባቂውን ጠ/ሚ የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝን ማናቸውንም እንቅስቃሴ እየመራ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ