አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በለንደኑ ኦሎምፒክ በ10 ሺህ ሜትር በአንደኝነት ስታሸንፍ Tirunesh Dibaba wins gold in the women's 10,000m final on Day 7 of London 2012.

Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 27 ቀን 2004 ዓ.ም. August 3, 2012) የ27 ዓመትዋ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ዛሬ በለንደኑ የ2012 ኦሎምፒክ ውድድር በተደረገው የሴቶች የአስር ሺህ ሜትር ለኢትዮጵያም ለራሷም የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች። አትሌት ወርቅነሽ ኪዳኔ እና በላይነሽ ኡልጂራ አራተኛና አምስተኛ በመሆን ጨርሰዋል።

 

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በለንደኑ ኦሎምፒክ በ10 ሺህ ሜትር በአንደኝነት ስታሸንፍ Tirunesh Dibaba wins gold in the women's 10,000m final on Day 7 of London 2012.

አትሌት ጥሩነሽ ውድድሩን የጨረሰችው 30፡20.75 ደቂቃ ሲሆን፣ ኬንያውያኖቹ አትሌቶች ሳሊ ጄፕኮሰጊ ኪፒጎ እና ቪቪአነ ጄፕኬሞይ በ30፡26.37 እና በ30፡30.44 ደቂቃ በመግባት ሁለተኛና ሦስተኛ በመግባት የብርና የነኀስ ሜዳሊያ አስገኝተዋል።

 

ኢትዮጵያውያኖቹ አትሌቶች ወርቅነሽ ኪዳኔ እና በላይነሽ ኡልጂራ ደግሞ በ30፡39.38 እና በ30፡45.56 ደቂቃ ውድድሩን ጨርሰዋል።

 

ጥሩነሽ ዲባባ ባለፈው እ.ኤ.አ. 2008 በቤጂንጉ (ቻይና) ኦሎምፒክ በተመሳሳይ ሁኔታ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ከማስገኘትዋም በላይ ውድድሩን በ29፡54.66 ደቂቃ በመጨረስ በርቀቱ የኦሎምፒክ ክብረወሰን መስበርዋ የሚታወስ ነው። አትሌት ጥሩነሽ በቤጂንጉ ኦሎምፒክ በአምስት ሺህ ርቀትም የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘቷ ይታወሳል።

 

በዛሬው ዕለት በተካሄደው የወንዶች የሦስት ሺህ የመሰናክል የማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ናሆም መስፍን አምስተኛ በመውጣት ለፍጻሜው ማለፉን አረጋግጧል።

 

ከዚህም ሌላ በወንዶች የ1500 ሜትር በተካሄዱት ሦስት ውድድሮች ከተካፈሉት ሦስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውስጥ አትሌት መኮንን ገብረመድኅን በመጀመሪያው ምድብ ሁለተኛ በመውጣት ማጣሪያውን አልፏል። በሁለተኛው ምድብ የተሳተፈው አትሌት ዳዊት ወልዴ 10ኛ በመውጣት፣ በሦስተኛው ምድብ የተሳተፈው አትሌት አማን ዎቴ ደግሞ 8ኛ በመውጣት ማጣሪያውን ሳያልፉ ቀርተዋል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ