ፕሬዝዳንት ባራክ ሁሴን ኦባማ በድጋሚ ተመረጡ Presidant Barack Obama re election

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥቅምት 28 ቀን 2005 ዓ.ም. November 7, 2012)፦ በዩናይትድ ስቴስ ኦፍ አሜሪካ እስከ ትናንት እኩለ ሌሊት ሲደረግ በነበረው ምርጫ ፕሬዝዳንት ባራክ ሁሴን ኦባማ ለሁለተኛ ጊዜ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል። ተቀናቃኛቸውን ሚት ሩምኒን 303 ኤሌክትሮ ቮት ለ206 ኤሌክትሮ ቮት በሆነ ልዩነት አሸንፈዋል።

 

የዚህ ዓመቱ የአሜሪካን ምርጫ ኤግዚት ፖል የሚከተለውን ይመስላል። (ኤግዚት ፖል መራጮች መርጠው እንደወጡ በቃለመጠይቅ መልክ የሚሰበሰብ መረጃ ነው።)

 

በጾታ

በዚህ ዓመቱ የአሜሪካ ምርጫ ድምጻቸውን ከሰጡት አሜሪካውያን ውስጥ 53% ሴቶች ሲሆኑ፣ 47% ደግሞ ወንዶች ናቸው። ከመራጮቹ ሴቶች ውስጥ 55% ለባራክ፣ 44% ደግሞ ለሮምኒ ድምጻቸውን የሰጡ ሲሆን፣ ወንዶቹ መራጮች ደግሞ 52% ለሮምኒ፣ 45% ለኦባማ ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

 

በዕድሜ

ከመራጮቹ ውስጥ ዕድሜአቸው ከ18-29 የሆኑት 19% ሲሆኑ፣ ከእነሱ ውስጥ 60% ለኦባማ፣ 37% ደግሞ ለሮምኒ ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

 

ዕድሜአቸው ከ30-44 የሆኑት ከመራጮቹ ውስጥ 27% ድርሻ ሲኖራቸው፤ ከእነሱ ውስጥ 52% ለኦባማ፣ 45% ደግሞ ለሮምኒ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

 

ዕድሜአቸው ከ45-64 የሆኑት የመራጩን 38% የሚሆኑት ሲሆኑ፤ ከእነሱ ውስጥ 51% ለሮምኒ፣ 47% ደግሞ ኦባማን መርጠዋል።

 

ዕድሜአቸው 65 እና ከዚያ በላይ የሆኑቱ የመራጩን 16% ድምጽ የሰጡ ሲሆን፣ 56% ለሮምኒ፣ 44% ደግሞ ለኦባማ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

 

በዘር

ከመራጮቹ ውስጥ ነጮቹ 72% ሲሆኑ፣ 59% ለሮምኒ፣ 39% ደግሞ ለኦባማ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

 

አፍሪካ አሜሪካውያኑ መራጮች 13% የሚሆነውን የመራጭ ድምፅ የያዙ ሲሆን፣ 93% የሚሆኑት ለኦባማ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

 

ላቲኖዎቹ 10% የሚሆነውን ድምፅ የሰጡ ሲሆን፣ 71% የሚሆኑት ለኦባማ፣ 27% ደግሞ ለሮምኒ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

 

እስያውያኑ 3% የሆነውን ድምፅ የሰጡ ሲሆን፣ 75% ለኦባማ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ