ከሟቾች አንዱ የወረዳው አስተዳዳሪ ናቸው

Ethiopia Zare (እሁድ ሰኔ 8 ቀን 2000 ዓ.ም. June 15 2008)፦ ኀሙስ ዕለት "ገዳማይት" በተባለ መንደር በአፋሮችና በኢሳዎች መካከል በተቀሰቀሰ የጎሣ ግጭት አራት ሰዎች ሲሞቱ፣ ብዛት ያላቸው ለከባድና ለቀላል የመቁሰል አደጋ መዳረጋቸውን ከኢትዮጵያ የደረሰን ሪፖርት ያስረዳል።

 

የኮንትሮባንድ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ የሚካሄድባት የገዳማይት መንደር ከሁለት ወራት በፊት በፌደራል ፖሊስ ከተቃጠለች በኋላ ከእንደገና ያንሰራራች ሲሆን፣ ከኢሳ መንደር ወደ አፋር መንደር የገባችን ፍየል አፋሮች አርደው በመብላታቸው ምክንያት ተነሳ በተባለው በዚህ የጎሣ ግጭት ከሞቱት አራት ሰዎች አንዱ ለማገላገል ወደ ስፍራው የተጓዙት የወረዳው አስተዳዳሪ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ከመኪናቸው እንደወረዱ በጥይት ተመትተው መሞታቸው ታውቋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!