ፕ/ር ኤፍሬም ይስኃቅ ለፈቃዱ መገኘት ሚና ተጫውተዋል

ጉባዔው ነገ ረቡዕ 2፡30 ሰዓት ላይ ይጀመራል

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሰኔ 10 ቀን 2000 ዓ.ም. June 17 2008)፦ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የመሥራች ጉባዔውን ለማካሄድ የሚያስችለውን የስብሰባ ፈቃድ አገኘ። የሸምጋዮቹ ቡድን መሪ የሆኑት ፕ/ሮ ኤፍሬም ይስኃቅ ለፈቃዱ መገኘት ሚና ተጫውተዋል።

 

የአንድነት ፓርቲ ቅዳሜ ሰኔ 7 ቀን ሊያደርገው አቅዶት የነበረውን ጉባዔ እንዳያካሂድ በፖሊስና በደህንነት ኃይሎች “የስብሰባ ፈቃድ የላችሁም” በሚል ሰበብ በኢምፔሪያል ሆቴል እና በፓርቲው ጽሕፈት ቤት መከልከሉን ተከትሎ፣ ፕ/ር ኤፍሬም ይስኃቅ ጉዳዩን እንዲያውቁት መደረጉ ታውቋል።

 

ፕሮፌሰሩ የሚመለከታቸውን ወገኖች ካነጋገሩ በኋላ ትናንት ጠዋት ፓርቲው ለአዲስ አበባ መስተዳድር የስብሰባ ፈቃድ ሰጪ አካል ማመልከቻ አስገብቷል። ትናንት ከሰዓት በኋላ ስብሰባውን ሊያካሂዱ መፍቀዱን መስተዳድሩ ለፓርቲው ጽ/ቤት አሳውቋል።

 

ይህንኑ ተከትሎ ሕጉ በሚጠይቀው መሰረት በስብሰባው ላይ ለሚደርስ ማንኛውም ነገር ኃላፊነቱን የሚወስድ ሰው ፊርማ በማስፈለጉ፣ ዛሬ ጠዋት ወ/ት ብርቱካን ኃላፊነቱን ለመውሰድና ለመፈረም ወደ መስተዳድሩ ማምራቷ ታውቋል።

 

በዚህም መሠረት አንድነት የመሥራች ጉባዔውን ነገ ረቡዕ ሰኔ 11 ቀን 2000 ዓ.ም. በፓርቲው ጽሕፈት ቤት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከ2፡30 ሰዓት ጀምሮ እንደሚያካሂድ ለማወቅ ተችሏል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!