በፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ቆንስላ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

ዳዊት ፋንታ

ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተሰባሰቡ ቁጥራቸው ከ400 በላይ የሚሆኑ እ.ኤ.አ. በማርች 01 ቀን 2013 ዓ.ም. ፍራንክፈርት በሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ፊት ለፊት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ።


በዚሁ በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ በጠራው ታላቅ የተቃውሞ ሠልፍ ላይ ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተገኙት ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ-ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የተገኙ ሲሆኑ፤ መነሻውን ''ሃውፕትቫኸ'' /Hauptwache/ ከሚባለው የከተማው ክፍል በማድረግ በተለያዩ መፈክሮችና የኢትዮጵያ ባንድራ በማሸብረቅ ጉዞውን ወደ ወያኔ ቆንስላ ጽ/ቤት አድርጓል።

እ.ኤ.አ. በማርች 01 ቀን 2013 ዓ.ም. በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ በጠራው ታላቅ የተቃውሞ ሠልፍ ላይ ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተሰባሰቡ ቁጥራቸው ከ400 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ-ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የተገኙ ሲሆን መነሻውን ''ሃውፕትቫኸ'' /Hauptwache/ ከሚባለው የከተማው ክፍል በማድረግ በተለያዩ መፈክሮችና የኢትዮጵያ ባንድራ በማሸብረቅ ጉዞውን ወደ ወያኔ ቆንስላ ጽ/ቤት አድርጓል።

- ''የህሊና እስረኞች ይፈቱ!''
- ''የፕሬስ ነጻነት ይከበር!''
- ''ሃሳብን በነጻነት የመግለፅ መብት ይከበር!''
- ''ጅሃዳዊ ሐረካት የወያኔ ፈጠራ ነው!''
- ''የሃይማኖት ነፃነት ይከበር!''
- ''በአለም ዙሪያ ያሉ የወያኔ ቆንስላ ፅ/ቤቶች የኢትዮጵያን ህዝብ አይወክሉም!''
- ''የአውሮፓ ህብረት ለአፋኙ የወያኔ አገዛዝ የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፍ ያቁም!''
- ''ከአባይ በፊት ሙስናና ዘረኝነት ይገደብ!'' የሚሉ መፈክሮች በሰፊው የተደመጡ ሲሆን

 

ከአንድ ሰዓት ተኩል የእግር ጉዞ በኋላ ተሰላፊው የወያኔ ቆንስላ ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሲደርስ በከፍተኛ ጩኸት እና ፉጨት ተቃውሞውን ማሰማት ችሏል። በዚህም የተደናገጡት የወያኔ ቆንስላ ሠራተኞች የህንፃውን መስኮት በፍጥነት በመዝጋት ከፊሎቹ ህንፃውን እየለቀቁ የወጡ ሲሆን፤ ቁጥራቸው ከአራት የማይበልጥ የቆንስላው ሠራተኞችም ከውስጥ በመሆን ሠልፈኞችን ለማስፈራራት በሚመስል መልኩ ፎቶ ሲያነሱ ተስተውለዋል።

ሰልፈኛውም ተቃውሞውን ይበልጥ በማጠናከር ለአንድ ሰዓት ያህል መፈክሮችን በማሰማት፣ የሀገር ፍቅር ዜማዎችን በማዜም እንዲሁም ይህንን ሰልፍ በቅርብ ርቀት ይመለከቱ ለነበሩ የሀገሬው ዜጎች በጀርመንኛ፣ በእንግሊዝኛና በአማርኛ ቋንቋዎች የተዘጋጁ በራሪ ወረቀቶችን በማደል የኢትዮጵያ ህዝብ በዘረኛው የወያኔ አገዛዝ እየደረሰበት ያለውን ግፍና መከራ ለአለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይፋ አድርገዋል።

 

በፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ቆንስላ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ተወካይ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች እና የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተወካዮች በአካል ተገኝተው አጠር ያለ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎም ከኔዘርላንድ የላከው ደብዳቤ ተነቧል።

 

ይህ ከሶስት ሰዓት በላይ የፈጀው የተቃውሞ ሠልፍም በሠላምና በታላቅ ድምቀት መጠናቀቅ ችሏል።

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!