የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) Ethiopian People's Congress for United Struggle (Shengo)Ethiopia Zare (ረቡዕ የካቲት 5 ቀን 2006 ዓ.ም. Feb. 12, 2014)፦ የአማራ ክልል ም/ፕሬዝዳንት አቶ አለምነው መኮንን በአማራው ላይ የሰነዘሩትን ፀያፍና በዘር ጥላቻ ላይ ያዘነበለ ስድብ በማውገዝ፤ "የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ" ትናንት የካቲት 4 ቀን 2006 ዓ.ም. መግለጫ አወጣ።

"ሸንጎ 'በአማራው' ላይ ያነጣጠረውን የዘር ጥላቻ ያወግዛል" በሚል ርዕስ ሸንጎው ባወጣው በዚሁ መግለጫ፤ ም/ፕሬዝዳንቱ የተሰነዘረውን ለሰሚው የሚከብድ ሕዝቡን የሚያንቋሽሽ ቅጥ ያጣ ውንጀላና ዘለፋን ሽንጎው በጥብቅ እንደሚያወግዘው ገልጿል። አክሎም "በዚህ ድርጊቱም ያሳየው ለሕዝቡ ያለው ዝቅተኛ አስተያየትና ለሰብዓዊ ክብሩም ያለው ጥላቻና ንቀት በማንኛውም መለኪያ ከወንጀለኛ ሰው የማይተናነስ እንደሆነ አስምሮበታል።

ሸንጎው "የዚህ አይነቱ ተግባር በማንም ይቅር ሊባልም ሆነ ሊረሳ የማይችል ነው። ይህ የዝቅተኛነት ስሜት የተጸናወተው ግለሰብ ቀድሞ በህወሓት መሪዎች በተጠነሰሰው አስቀያሚና አፀያፊ የታሪክ ተውኔት የወቅቱ ተዋናይ የመሆን ዕድልን አግኝቷል" በማለት የግለሰቡን ንግግር አውግዟል። የሸንጎውን ሙሉ መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ! 

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!