Ethiopia Zare (ቅዳሜ ነኀሴ 3 ቀን 2000 ዓ.ም. August 09, 2008)፦ በግጦሽ መሬትና በድንበር ግጭት ምክንያት በተነሳ አለመግባባት በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን በደቡብ ክልል የሚዋሰኑ ከአዲስ አበባ 534 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ሀገረማርያም ከተማ 47 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙ ሁለት ጎሣዎች መካከል በተነሳ ግጭት ስምንት ሰዎች መሞታቸውን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች አረጋገጡ።

 

 

ከሐምሌ 28 ቀን ጀምሮ እስከ ነኀሴ 1 ቀን በኦሮሚያ ክልልና በደቡብ ክልል ከሀገረማርያም 47 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ከብት አርብተው በሚኖሩ የቦረና ጎሣዎችና አርሰው በሚተዳደሩ በደቡብ ክልል ስር የሚተዳደሩ ጎሣዎች መካከል እርሻችንን አስበላችሁ፣ ከብቶቹ አንዱ ያንዱን ድንበር ጥሶ ይገባል በሚል ግጭቱ እንደተቀሰቀሰ ታውቋል።

 

በግጭቱ 15 ሰዎች ቆስለው ሀገረማርያም ሆስፒታል ለሕክምና የተወሰዱ ሲሆን፣ ሁለቱ ሆስፒታል ደርሰው ሕይወታቸው አልፏል። ስድስቱ የእርስ በርስ ግጭቱ ከተፈጠረበት ቦታ አስከሬናቸው የተነሳ መሆኑን ለማዎቅ ችለናል።

 

እንዲህ ያሉ የጎሣ ግጭቶች ሲከሰቱ በአካባቢው የሚገኙ የክልል ፖሊስ ለመቆጣጠር ወይም ለማብረድ አቅም ስለሌላቸው የፌደራል ፖሊስ እንዲገባበት ይጠይቃሉ፣ በዚህ አካባቢ ግን ፌደራል ፖሊስ ፈጥኖ አለመድረሱ ለጠፋው ሕይወትና ለወደመው ንብረት መበራከት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማድረጉንም ከአካባቢው የደረሰን ማስረጃ ይጠቁማል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!