፳፩ አዳዲስ ሚኒስትሮች ተሾሙ፣ ፱ኙ ባሉበት ቀጠሉ

PM Hailemariam Desalegne

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥቅምት ፳፪ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. November 1, 2016)፦ በዛሬው ዕለት ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 21 አዳዲስ የካቢኔ ሹመቶችን ያቀረቡ ሲሆን፣ ፱ኙን ደግሞ ባሉበት ይቀጥላሉ ብለዋል። ፓርላማው ሹመቱን በሙሉ ድምፅ አጽድቆታል። በዚህ ሹም ሽረት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም እና አቶ ጌታቸው ረዳ ከሥልጣናቸው ተነስተዋል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖምን በመተካት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኹነው የተሾሙት ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ሲሆኑ፣ አቶ ጌታቸው ረዳን በመተካት የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ኹነው የተሾሙት ደግሞ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ናቸው። አዲሶቹን ተሿሚዎች በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ዳኔ መላኩ አማካኝነት ቃለመኀላ ፈጽመዋል።

ሹመታቸው በዛሬው ዕለት ከጸደቀላቸው የካቢኔ አባላት ውስጥ ሦስት ሴቶች የተሾሙ ሲሆን፤ እነርሱም ኢንጂነር አይሻ መሐመድ የኮንስትራክሽን ሚኒስትር፣ ዶ/ር ሂሩት ወልደማርያም የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር እና ወ/ሮ ደሚቱ ሀምቤሳ የሴቶች እና ሕፃናት ጉዳይ ሚኒስትር ናቸው።የአዲሶቹና ባሉበት የሚቀጥሉት ባለሥልጣናት ዝርዝር ከዚህ በታች ቀርቧል።

ባሉበት የሚቀጥሉት ዘጠኙ ባለሥልጣናት የሚከተሉት ናቸው።

፩. አቶ ደመቀ መኮንን፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣
፪. አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፦ የመከላከያ ሚኒስትር፣
፫. አቶ ካሳ ተክለብርሃን፦ የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር አካባቢ ልማት ሚኒስትር፣
፬. ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፦ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር፣
፭. አቶ አህመድ አብተው፦ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር፣
፮. አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂ፦ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር፣
፯. ዶ/ር ይናገር ደሴ፦ የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር፣
፰. አቶ ጌታቸው አምባዬ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ እና
፱. አቶ አስመላሽ ወልደሥላሴ፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ናቸው።

አዲሶቹ ተሿሚዎች ደግሞ የሚከተሉት ናችው፦

፩. ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣
፪. አቶ ታገሰ ጫፎ፦ የፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር፣
፫. ዶ/ር አብረሃም ተከስተ፦ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር፣
፬. ዶ/ር በቀለ ጉላዶ፦ የንግድ ሚኒስትር፣
፭. ፕሮፌሠር ፍቃዱ በየነ፦ የእንሰሳትና የዓሳ ሀብት ልማት ሚኒስትር፣
፮. ዶ/ር ኢያሱ አብረሃ፦ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር፣
፯. ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፦ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር፣
፰. አቶ አህመድ ሺዴ፦ የትራንስፖርት ሚኒስትር፣
፱. ዶ/ር አምባቸው መኮንን፦ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር፣
፲. ኢንጂነር አይሻ መሐመድ፦ የኮንስትራክሽን ሚኒስትር፣
፲፩. ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፦ የውሃ፣ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር፣
፲፪. አቶ ሞቱማ መቃሳ፦ የማዕድን፣ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር፣
፲፫. ዶ/ር ገመዶ ዳሌ፦ የአካባቢ ደን ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር፣
፲፬. ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም፦ የትምህርት ሚኒስትር፣
፲፭. ፕሮፌሠር ይፍሩ ብርሃነ፦ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር፣
፲፮. ዶ/ር ግርማ አመንቴ፦ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር፣
፲፯. ዶ/ር ሂሩት ወልደማርያም፦ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር፣
፲፰. ወይዘሮ ደሚቱ ሀምቤሳ - የሴቶች እና ሕፃናት ጉዳይ ሚኒስትር፣
፲፱. አቶ ርስቱ ይርዳው፦ የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትር፣
፳. አቶ ከበደ ጫኔ፦ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ኃላፊ ሚኒስትር እና
፳፩. ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ፦ የመንግሥት ኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ናቸው።

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!