Suicide gun

ኢትዮጵያ ዛሬ (ኀሙስ ኅዳር ፳፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 8, 2016)፦ ለአስራ ሦስት ዓመት ካለእናት ልጁን ሲያሳድግ የቆየ አባት፣ የ፲፫ ዓመት ልጁን ገንዘብ ሰርቀሃል በሚል ባደረሰበት ድብደባ የልጁን ሕይወት መቅጠፉን ሲረዳ የገዛ ሕይወቱን በሽጉጥ አጠፋ።

ነዋሪነቱ በአዲስ አበባ ቂሊንጦ አካባቢ የነበረውና ራሱንና ልጁን በግብርና ሥራ ላይ ተሰማርቶ ሲያስተዳደር የነበረው አቶ ሲሳይ አዲሴ የተባለ ግለሰብ፤ ልጁን አቤል ሲሳይን ባለፈው ኅዳር ፳፫ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. ገንዘብ ሰርቀሃል በሚል ”ቅጣት” በሚል ሰበብ ልጁን ሲደበድብ ጎረቤቶ ያስጣሉት ቢሆንም፤ በማግስቱ ጠዋት ሕፃን አቤል በተኛበት ሕይወቱ አልፋልች።

የልጁን ሕይወት መጥፋት ጠዋት የተረዳት አባት የገዛ ሕይወቱን በሽጉጥ አጥፍቷል። አቶ ሲሳይ ከልጁ እናት ጋር ሕፃን አቤል እንደተወለደ ከአሥራ ሦስት ዓመት በፊት ተለያይቶ ልጁን ለብቻው ያሳድ የነበረ ሲሆን፣ ሕፃን አቤል የአምስተኛ ክፍል ተማሪ ነበር።

የሕፃን አቤል አስከሬን እናቱ ወደምትኖርበት ሸኖ (ሰሜን ሸዋ) ተሸኝቶ የቀብር ሥነሥርዓቱ የተፈጸመ ሲሆን፣ የአባትየው ደግሞ በአቃቂ መፈጸሙን ለመረዳት ችለናል። አቶ ሲሳይ አዲሴ የሠላሳ ዘጠኝ ዓመቱ ነበር።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ