ግርማ ወ/ጊዮርጊስ

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የኢትዮጵያውይና ብቻ ሳይሆን የጥቁር ሕዝብ ኩራት የሆነው፣ ብቃት ያለው፣ የግዕዝ ፊደል እያለ፣ የላቲን ፊደልን ለኦሮምኛ መጠቀም ትክክል እንዳልነበረ ገልጸው፤ ላቲን በአፋን ኦሮሞ እድገት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽኖ እንዳሳደረበትና ቋንቋውን በተቀረው የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ እንዳያድግ መሰናክል እንደሆነ በመግለጽ፤ አፋን ኦሮሞ በግዕዝ መጻፍ እንዲጀመር ጠይቀዋል።

ራሱ የኦሮሞ ማኅበረሰብም የሆነ፣ በአፍሪካ ጥንታዊና ብቸኛ የጥቁር ሕዝብ ፊደል ተደርጎ የሚወሰድ፣ የሚያኮራ የግዕዝ ፊደል እያለን፣ ላቲን ለኦሮምኛ መጠቀሙ ትክክል አልነበረም። የኦሮምኛን እድገት በእጅጉ ጎድቶታል። የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ

በአማራ ክልል ኦሮሞኛ እንደ ትምህርት እንዲሰጥ በመጠየቀ ለአማራ ክልል ፕሬዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በጻፉት ደብዳቤ፤ የአማራ ክልል አፋን ኦሮሞን በግዕዝ ፊደል በማስተማር ፈር ቀዳጅ እንዲሆንም ተማጽነዋል። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ የተመጽኖ ደብዳቤ ሙሉው ከዚህ በታች ሰፍሯል።

ለተከበሩ የአማራ ክልል መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ደብዳቤ
የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ለተከበሩ የአማራ ክልል መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የጻፉት ደብዳቤ

ውድ የተከበሩ አቶ ገዱ፤

“ንብ ቢያብር አንበሳን ያስር” እንደሚባለው በሕብረትና በአንድነት የማይፈታ ችግር የማይታለፍ ድልድይ የለም። እኛ ኢትዮጵያውያን ዘርና ሃይማኖት ሳይከፋፍለን በአንድነት በመቆማችን ከእኛ በላይ በዘመናዊ መሳሪያ የታጠቁትን ጠላቶች ለመመከትና የአገራችንን ነፃነት ለማስጠበቅ ችለናል።

አሁን አገራችን የውጭ ወራሪ ጠላቶች ባይኖሯትኝ እንደ ድህነት፣ በሽታ፣ የኋላቀርነት፣ መከፋፈልን የመሳሰሉ ጠላቶች አሏት። አሁንም ሌሎች አገሮች ከደረሱበት አንጻር ብዙ መሥራት ይጠበቅብናል። ለዚህም ነው ኢትዮጵያውያን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መያያዝ ያለብን። በርስ በርሳችን ያሉ መከፋፈሎችና አጥሮችን ማፍረስ አለብን። መግባባት፣ መነጋገር፣ መቀራረብ መቻል አለብን። እነርሱና እኛ የሚለውን አቁመን ሁላችንም “እኛ” ማለት መጀመር አለብን።

ለዚህም ነው በአማራ ክልል አፋን ኦሮሞ እንደ ትምሀርት እንዲሰጥ የሚጠይቅ ጽሁፍ ምሁራን ለርስዎ እንደጻፉ ሳነብ ደስታ የተሰማኝ። አፋን ኦሮሞ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የሚናገሩት የኢትዮጵያውያን ሁሉ የሆነ ቋንቋ ነው። ይህ ቋንቋ ከኦሮሚያ አልፎ በሌሎች ክልሎች እንደ ትምሀርት መሰጠቱ የበለጠ መግባባትንና የበለጠ መቀራረብን የሚያመጣ ብቻ ሳይሆን፤ ቀደም ሲል መደረግ የነበረበት ጉዳይ ነው። ሊደገፍ ብቻ ሳይሆን ለተግባራዊነቱም የሁላችንንም ድርሻ የሚጠይቅ ነው።

አብዛኛው ኦሮምኛ የማይናገር ኢትዮጵያዊ አፋን ኦሮሞ የመማርና የማወቅ እድል ቢመቻችለት ለማወቅና ለመማር ትልቅ ፍላጎት የሚኖረው ነው የሚመስለኝ። የአማራ ክልል መስተዳደርም አፋን ኦሮሞ በክልሉ ማስተማር ቢጀምር የሕዝብ ድጋፍ ሊያገኝ ይችላል ብዬ አስባለሁ።

ሆኖም ግን ሁሉንም የአገራችን ቋንቋዎች በትክክል ለመጻፍ ብቃት ያለው፣ የራሱ የኦሮሞ ማኅበረሰብም የሆነ፣ በአፍሪካ ጥንታዊና ብቸኛ የጥቁር ሕዝብ ፊደል ተደርጎ የሚወሰድ፣ የሚያኮራ የግዕዝ ፊደል እያለን፣ ላቲን ለኦሮምኛ መጠቀሙ ትክክል አልነበረም። የኦሮምኛን እድገት በእጅጉ ጎድቶታል። በሌላው ማኅብረሰብ ዘንድ ኦሮምኛን የመማር ፍላጎትን እንዳይኖር ሆኗል። ያለ ፍላጎት ደግሞ በግድ አስገድዶ ወይም በአዋጅ የሚሆን ነገር አይኖርም። ስለዚህ የአፋን ኦሮሞ ተቀባይነትም ለማሳደግ ሕዝብ በፍቅርና በፍላጎት እንዲማረው ለማበረታታት የአማራ ክልል መስተዳደር ግዕዝን እንዲጠቀም በአጽንዎትና በአክብሮት እጠይቃለሁ።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ