President El-Sisi addressing the 74th session of United Nations General Assembly

የግብጹ ፕሬዝዳንት አልሲሲ 74ኛው የተመድ ስብሰባ ላይ ንግግር ሲያደርጉ

ኢዛ (ሐሙስ መስከረም ፲፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. September 26, 2019):- በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ግብጽ ያነሳችውን አዲሱ ጥያቄ ወደ ተባበሩት መንግሥት ድርጅት በመውሰድ ጉዳዩ ስጋት ሆኗል በማለት ትናንት ገለፀች።

ከአንድ ሳምንት በፊት በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ የጋራ የምክክር መድረክ ላይ ከግብጽ የተነሳው አዲስ ጥያቄ በኢትዮጵያ በኩል ቁርጥ አቋም የተወሰደበትና የግብጽን አዲስ መደራደሪያ ሐሳብ ማሳወቁ አይዘነጋም።

ሆኖም የግብጹ ፕሬዝዳንት አልሲሲ ሰሞኑን እየተካሄደ ባለው ሰባ አራተኛው የተባበሩት መንግሥት ድርጅት (ተ.መ.ድ) ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ያገኙትን መድረክ፣ የህዳሴው ግድብ ላይ ትኩረት በመሥጠት ተናግረዋል።

አሁን ባለው ሁኔታ በግድቡ ዙሪያ እየተካሄደ ያለው ውይይት ውጤት እያመጣ አይደለም በማለት ገልፀዋል።

ግብጽ ከግድቡ ግንባታ በመጠናቀቅ በኋላ መሆን አለበት ብላ ያቀረበችው ሐሳብ እስከዛሬ በሦስቱ አገራት ሲደረግ ከቆየው የድርድር መንፈስ ያፈነገጠ ሆኖ የተገኘ በመሆኑ፤ ኢትዮጵያ የግብጽን ሐሳብ በተለያዩ መንገዶች እንደማትቀበልና ሥራዋን እንዳምትቀጥል አስታውቃለች። እንዲሁም የግድብ ሥራውን ብቻ አጠናቆ ወደ ሥራ መገባት እንዳለበት በማመን በቅድሚያ ሥራ ይጀምራሉ ተብለው የሚጠበቁ የመጀመሪያዎቹ የኃይል ማመንጫ ተርባይኖች ላይ ትኩረት ሰጥታ እየሠራች ነው።

ከሁለት ቀናት በፊት ወደ ግድቡ ያመሩት የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ጉባ ከሚገኘው የግድቡ ሥፍራ በሰጡት መግለጫ፤ ግብጽ እስከዛሬ ከነበረው ድርድር አፈንግጣ ያመጣችውን ሐሳብ ኢትዮጵያ እንደማትቀበል አረጋግጠዋል።

ግብጽ ባልተጠበቀ ሁኔታ ይዛ የቀረበችው ሐሳብ በአገሯ ጋዜጦች ላይ እንዲራገብ እያደረገች ሲሆን፣ አልሲሲም ጉዳዩ ያሳስበናል በሚል በተ.መ.ድ. ንግግራቸው የማንፀባረቃቸው ነገር ሆን ተብሎ የሚደረግ ስለመሆኑም እየተገለፀ ነው።

ይህም ከሰሞኑ ግብጻውያን ታሪር አደባባይ ወጥተው ፕሬዝዳንት አልሲሲ ይውረዱ በሚል የተቀጣጠለውን ተቃውሞ አቅጣጫ ለማስቀልበስ ሊጠቀሙበት በማሰብ የተደረገ ነው ከሚል ነው። ይህም ቢሆን ግን ግብጻውያን ተቃውሟቸውን ቀጥለዋል። ኢትዮጵያም የግድብ ሥራዋን በበለጠ ትኩረት እየሠራች ነው።

ፕሬዝዳንቱና መንግሥታቸው የፊታች ዓርብ መስከረም ፲፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. (September 27, 2019) በዕለተ ጁምዐ ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ ይጠብቃቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ