ጠ/ሚኒስትር መለስ ይጎበኟታል ተባለ

ኢትዮጵያዊያኖች ለተቃውሞ እየተዘጋጁ ነው

Ethiopia Zare (ማክሰኞ መስከረም ፲፫ (13) ቀን ፳፻፩ (2001) ዓ.ም. September 23, 2008)፦ ለጉብኝት በሰሜን አሜሪካ ዋና ዋና ከተሞች በመዘዋወር ላይ የምትገኘው ድንቅነሽ (ሉሲ) ከሂውስተን ወደ ሲያትል-ዋሽንግተን የምታቀና ሲሆን፣ ጠ/ሚኒስትር መለስ ጉብኝቱን ትኩረት ለማሰጠት በስፍራው እንደሚገኙ ያወቁ ኢትዮጵያዊያን ለተቃውሞ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች አረጋገጡ።

 

ጠ/ሚ/ር መለስ በሲያትሉ ካውንስለር አቶ ሠለሞን ታደሰ እና በባለቤታቸው የክብር እንግድነት ግብዣ ተደርጎላቸዋል። ጠ/ሚኒስትሩ ለግብዣው የሰጡት ምላሽ ባይታወቅም ሁኔታውን የሰሙ ኢትዮጵያዊያኖች በመተባበር ከፍተኛ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸው ታውቋል።

 

ድንቅነሽ በሲያትል ፓሲፊክ ሳይንስ ማዕከል ለአምስት ወራት ለዕይታ ትቀርባለች።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ