የቤት ጋዝ 5.75 የነበረው 8.59 ሆኗል

Ethiopia Zare (ዓርብ መስከረም ፳፫-23 ቀን ፳፻፩-2001 ዓ.ም. October 3, 2008)፦ ከዛሬ መስከረም 23 ቀን 2001 ዓ.ም. ጀምሮ የነዳጅ ዋካ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች አረጋገጡ። የላምባ ወይንም የቤት ጋዝ 8 ብር ከ59 ሣንቲም ገብቷል።

 

ከጠዋት ጀምሮ የአዲስ አበባና የሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች የነዳጅ ማደያዎች ተጨናንቀው የታዩ ሲሆን፣ ዋጋ እንደሚጨመር የማደያዎች ባለቤቶች ሰምተው ስለነበርና ጭምጭምታ በከተማዎች በመወራቱ በነዳጅ ማደያዎች ከፍተኛ ወረፋ እንደነበር ምንጮቻችን ገለረጸዋል።

 

ጭማሪው

ቤንዚን 9.40 የነበረው 10.15 ሣንቲም ሲገባ

 

ኬሮሲን (ላምባ ወይም የቤት ጋዝ) 5.75 የነበረው 8.59 ሆኗል

 

ናፍጣ (ነጭ ጋዝ) 9.62

 

ከባድ ጥቁር 7.84፣ ቀላል ጥቁር 7.39 እየተሸጠ መሆኑን ለማዎቅ ችለናል።

 

በነዳጅ ጭማሪው መሰረት የትራንስፖርት ዋጋም እየጨመረ ከመሆኑም በላይ ከነዳጅ ጋር የተያያዙ ማናቸውም የፋብሪካ ውጤቶችም በህዝቡ የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚያስከትሉ ታዛቢዎች ተናግረዋል።

 

በታክሲ ላይ እንደየታሪፋቸው ከ5 ሣንቲም እስከ 25 ሣንቲም ጭማሪ ከመደረጉም በላይ በአንበሳ አውቶብስ ተሳፋሪዎች ላይ ከ5 ሣንቲም እስከ 80 ሣንቲም ጭማሪ ተደርጓል።

 

የክፍለ ሀገር አውቶብስ እንደየርቀቱ የዋጋ ጭማሪ የተደረገ ሲሆን፣ ጭማሪው ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!