የአሜሪካ ህዝብ ታሪክ ሠራ

Presidant Barack Hussein Obama

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥቅምት 26 ቀን 2001 ዓ.ም. November 5, 2008)፦ የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ህዝብ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቁር ፕሬዝዳንት መረጠ። ሴናተር ባራክ ኦባማ 44ኛው የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ሆኖ ተመረጠ። የ2008 ምርጫ ታሪካዊ ምርጫ ሆነ።  ኋይት ሐውስ የመጀመሪያዋን ጥቁር ቀዳማዊ እመቤት አገኘች።

 

በአባቱ ኬንያዊ፣ በእናቱ ነጭ የሆነው ባራክ ሁሴን ኦባማ የ47 ዓመቱ ሲሆን፣ በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ሙያ ተምሯል። የጥቁሩ ማኅበረሰብ መሪ የነበረውና ለለውጥ ከፍተኛ ትግል ያካሄደው ማርቲን ሉተር ኪንግ ለነጭና ለጥቁር እኩልነት የነበረውን ሕልም ከ45 ዓመት በኋላ አሜሪካን በኋይት ሐውስ ፕሬዝዳንት ባራክ ሁሴን ኦባማን በማስተናገድ ዕውን አድርጋዋለች።

 

”The Change We Need” የሚል የመወዳደሪያ መፈክር የነበረው ባራክ ኦባማ ከአሜሪካ ውጭ ያሉ በርካታ ሀገራት በፕሬዝዳንታዊ ፉክክሩ ወቅት ድጋፋቸውንና ተስፋቸውን ሲሰጡት እንደነበር ይታወቃል።

 

በዚህ ምርጫ የአሜሪካን ህዝብ ባራክ ኦባማን በፕሬዝዳንትነት መምረጡ ለለውጥ ከልቡ ቆርጦ መነሳቱን የሚያሳይ መሆኑ ታምኗል። ፕሬዝዳንት ባራክ በተለይም በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዳውን የአሜሪካንን ኢኮኖሚ ያስተካክላል፣ የአሜሪካንን ከኢራቅ መውጣት ያረጋግጣል፣ በሀገር ውስጥ ያሉትን የማኅበረሰቡን ችግሮች ይፈታል፣ … ተብሎ ይጠብቃል።

 

ታዋቂው የሰብዓዊ መብት ተከራካሪውና በ1984 እና 1988 እ.ኤ.አ. የዴሞክራቲክ ፓርቲ እጩ ፕሬዝዳንት የነበረው ጄሲ ጃክሰን የኦባማ በፕሬዝዳንትነት መመረጥ ከመደሰቱ የተነሳ አልቅሷል።

 

ባራክ ኦባማ ኦገስት 4 ቀን 1961 እ.ኤ.አ. በሐዋይ ነው የተወለደው። የባራክ ኦባማ አያት (የእናቱ እናት) ማድሊን ፓይኔ ዱሃም ምርጫው ሁለት ቀን ሲቀረው ሰኞ ዕለት ጥቅምት 24 ቀን 2001 ዓ.ም. (November 3, 2008) በካንሰር ምክንያት በ86 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

 

አርባ አራቱን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንቶች የሥልጣን ጊዜ፣ ምስል፣ ስም፣ የወከሉትን ፓርቲ፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶቻቸውን በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ