በኦባማ መመረጥ ከተሞች በደስታ በተሞሉ ነዋሪዎች ተጨናንቀዋል

Ethiopia Zare (ኀሙስ ጥቅምት 27 ቀን 2001 ዓ.ም. November 6, 2008)፦ የኬንያው መሪ ምዋይ ኪባኪ በአባቱ ኬንያዊ የሆነውን ባራክ ኦባማን ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት መመረጥ አስመልክተው ኀሙስ ኖቨምበር 6 ቀን በሀገሪቱ የበዓል ቀን ሆኖ እንዲውል መልዕክት አስተላለፉ።

 

"የዚህ ዕለት ታሪካዊነት ለአሜሪካዊያን ብቻ ሳይሆን ለእኛ ለኬንያዊያኖችም ጭምር ነው" በማለት የተናገሩት ፕሬዝዳንት ኪባኪ "የዘር ግንዱ ከኬንያ በመሆኑ የሴናተር ኦባማ ማሸነፍ የእኛም ድል ነው። ለስኬታማነቱም ክብር ይሰማናል" ሲሉ ተደምጠዋል።

 

በኬንያ በተለያዩ ከተሞዎች ሲ.ኤን.ኤን. የፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማን ማሸነፍ ካረጋገጠበት ሰዓት ጀምሮ በከፍተኛ ደስታ በተዋጡ ነዋሪዎች ተጨናንቀው እንደሚገኙ ዘግቧል።

 

የኦባማ የቅርብ የስጋ ዘመድ የሆኑት የኬንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ለጉብኝት ካሉበት ቻይና የደስታ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!