የውይይቱን ክፍል አንድ በድምፅ ይዘናል (የማጫወቻው ችግር የተስተካከለ)

UDJ public meeting, Sweden

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ኅዳር 6 ቀን 2001 ዓ.ም. November 15, 2008) የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ የአውሮፓ ልዑካን ቡድን የሆኑት የፓርቲው ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ እና የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚ አባልና የዕቅድና የስትራቴጂ ኃላፊ የሆኑት አቶ አክሉ ግርግሬ በስዊድን ዋና ከተማ ዛሬ ቅዳሜ ኅዳር 6 ቀን 2001 ዓ.ም. ከኢትዮጵያውያን ጋር ሲወያዩ ዋሉ። የእራት ግብዣም ነበር።

 

ከቀኑ በሰባት ሰዓት የጀመራል ተብሎ የታቀደው ህዝባዊ ስብሰባ የተጀመረው ከሁለት ሰዓት በላይ አርፍዶ ነበር የተጀመረው። እንግዶቹ ከሰዓት በኋላ ዘጠኝ ሰዓት ከሩብ ላይ ወደ አዳራሹ የገቡ ሲሆን፣ በስዊድን ከአንድነት የድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ አቶ ስሜነህ ታምራት ለልዑካን ቡድኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

 

በመቀጠልም የድጋፍ ሰጪው ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ታምራት አዳሙ ለልዑካን ቡድኑና ለተሰብሳቢው የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልዕክታቸውን ካስተላለፉ በኋላ፣ የአስራ አንድ ደቂቃ ንግግር አድርገዋል።

 

ከሰዓት በኋላ ለአስር ሰዓት ሃያ ጉዳይ ላይ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ነበሩ ንግግር ማድረግ የጀመሩት። ሊቀመንበሯ ለዛሬው ብቻ ሳይሆን የቅንጅት አመራሮች በእስር ቤት በነበሩበት ወቅት በስዊድን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስለሠሩት ሥራ በማመስገን ነበር ንግግራቸውን የጀመሩት። አክለውም የመጡበትን ዓላማ አቶ አክሉ እንዲያስረዱ ጋብዘዋል።

 

አቶ አክሉ ግርግሬ አንድነት ፓርቲን በተመለከተ ሰፋ ያለ ንግግር አድርገዋል። የአንድነት ፓርቲን አወቃቀር፣ ዓላማ፣ ዕቅድ፣ ግብ፣ … አጠር ባለና ግልጽነት በተሞላበት ሁኔታ አብራርተዋል።

 

 

UDJ public meeting, Sweden

 

 

ዕረፍት እስከተወጣበት እስከ አስራሁለት ሰዓት ድረስ ያለውን ውይይት በድምፅ ለማድመጥ የሚከተለው ማጫወቻ ላይ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ።

 

 

ወደ ክፍል ሁለት ውሰደኝ ...

 

 

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!