PM Meles ZenawiEthiopia Zare (ዓርብ ኅዳር 26 ቀን 2001 ዓ.ም. December 05, 2008)፦ በሚኒስትሮች ሹም ሽር የጀመረው የፌደራል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የሥልጣን ሽግግር ወደ ሚኒስትር ዴኤታዎችም እየተጓዘ ነው።

 

የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታዎች የነበሩት ወ/ሮ ስመኝ ውቤና ዶክተር ሃሺም ቶፊቅ ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል። የሴቶች ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ኡባህ መሐመድና የፌደራል ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ የነበሩት አቶ ማዕረጉ ሀብተማርያም ከኃላፊነታቸው ከተነሱት መካከል ይጠቀሳሉ።

 

የማስታወቂያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት አቶ ተሰማ ፎቴ እና በሚኒስትር ማዕረግ የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር የነበሩት ወ/ሮ እንወይ ገብረመድህንም ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል።

 

የሌሎች ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ሚኒስትር ዴኤታዎችም፤ ከኅዳር 17 ጀምሮ ከኃላፊነት መነሳታቸውንና ላበረከቱት አስተዋጽዖም ምሥጋናን የሚገልጽ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ምንጮቻችን ገልፀዋል።

 

ለሚኒስትር ዴኤታዎቹ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ መነሳታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ የደረሳቸው፣ ሚኒስትሮቹ በይፋ ከተነሱበት ማግስት ጀምሮ መሆኑን መረዳት ተችሏል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ