Ethiopia Zare (ቅዳሜ የካቲት 8 ቀን 2000 ዓ.ም. February 16,2008)፦ የሰሜን አሜሪካ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ድጋፍ ሰጪዎች ማኅበር በሚያደርገው የቦርድ ምርጫ አቶ ክፍሌ ጥግነህ ተገኝተው ሊያስመርጡ መሆኑን አንድ ዘገባ ጠቆመ።

 

እንደ ዘገባው ከሆነ በአቶ አክሎግ ልመንህ ሊቀመንበርነት እየተመራ የሚገኘው የሰሜን አሜሪካ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ የድጋፍ ሰጪዎች ማኅበር የአመራሩ የሥራ ዘመን የተጠናቀቀ በመሆኑ በየካቲት 15 ቀን 2000 ዓ.ም. አዲስ የቦርድ አመራር ይመርጣል።

 

ማኅበሩ ከ14 ስቴቶች የተውጣጡ ቻፕተሮች አባል የሆኑበት ሲሆን፣ እነዚህ ቻፕተሮች የራሳቸውን አመራር መርጠው አቅርበዋል። ከእነዚህ 14 እጩዎች መካከል ሌላ ምርጫ በማድረግ የማኅበሩ ቦርድ እንዲመረጥ እንደሚደረግ ታውቋል።

 

ለሚደረገው ለዚሁ ምርጫም አዲስ አበባ ከሚገኘውና በእነ ወ/ት ብርቱካን ከሚመራው ቡድን ሰው እንዲገኝላቸው በጠየቁት መሠረት፤ ሥራ አስፈፃሚው በመጀመሪያ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ከዛም ዶ/ር ኃይሉ አርኣያን እንዲሄዲ ይመርጣሉ።

 

ሁለቱም የሥራ ጉዳይ እንዳለባቸው በመግለፅ ሌላ ሰው እንዲመደብ ይጠይቃሉ። ሥራ አስፈፃሚው ተወይይቶበትም አቶ ክፍሌ ጥግነህ በምርጫው ላይ እንዲገኙ በተወሰነው መሠረት ሊሄዱ እንደሆነ ታውቋል።

 

አቶ ክፍሌ ጥግነህ ሕገ-መንግሥቱንና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማፍረስ በሚለው ክስ በራሳቸው ስም በሚጠራ መዝገብ ተከሰው ጉዳያቸው በልደታ ፍርድ ቤት ሲታይ እንደነበርና በመጨረሻም ከቅንጅት አመራሮች ጋር መፈታታቸው ይታወሳል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ