ያሬድ ክንፈ (ከዋሽንግተን ዲሲ)

Tuesday: President-elect Barack Obama and his wife, Michelle, flank President and Mrs. Bush at the White House (AP Photo).

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥር 12 ቀን 2001 ዓ.ም. January 20, 2009)፦ ዛሬ ማክሰኞ ጥር 12 ቀን 2001 ዓ.ም. የአሜሪካን ዋና ከተማ የሆነችው ዋሽንግተን ዲሲ ከመቼውም ጊዜ በላይ በህዝብ የተጨናነቀችበት ዕለት ነው። የዓለም ህዝቦች ዓይንና ጆሮም በዚህችው ከተማ ላይ አነጣጥረዋል። አሜሪካ ፕሬዝዳንቷን የምትቀይርበት ዕለት ነውና።

 

ዛሬ ጠዋት በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ የሥልጣን ሽግግር ሥርዓት መሠረት መጪው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ከነቤተሰቡ፣ እንዲሁም መጪው ምክትል ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በቅዱስ ጆን ኢጲስኮፓል ቤተክርስቲያን የግል አገልግሎት ተሰጥቷቸዋል።

 

(AP) President-elect Barack Obama and Michelle Obama are welcomed by Rev. Luis Leon as they arrive for church service at St. John's Episcopal Church across from the White House in Washington, Tuesday, Jan. 20, 2009.ከአራተኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጄምስ ማዲሰን ጀምሮ በዚህች ቤተክርስቲያን ይህንን ሥርዓት ፕሬዝዳንቶቹ ሥልጣናቸውን ከመረከባቸው በፊት የሚፈጽሙት መሆኑ ታውቋል። ባራክ ኦባማንና ባለቤቱን ሚሼል ኦባማን የተቀበሏቸው የተከበሩ ቄስ ሉዊስ ሊዮን ነበሩ የተቀበሏቸው። የተከበሩ ቄስ ጆዬል ሐንተር ደግሞ ለባራክ ሁሴን ኦባማ ቡራኬ ሰጥተዋል።

 

ከቤተክርስቲያን መልስ በዋሽንግተን ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ ወደ አራት ሰዓት (10 A.M.) ባራክ ኦባማ እና ጆ ባይደን ከባለቤታቸው ጋር ወደ ኋይት ሐውስ አምርተዋል። በኋይት ሐውስም ባራክ ኦባማን እና ባለቤቱን ሚሼል ኦባማን ፕሬዝዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ እና ባለቤቱ ሎራ ቡሽ አቀባበል አድርገውላቸዋል። በዚህ አቀባበል ላይ መጪዋ የአሜሪካ ቀዳማዊ እመቤት ሚሼል ኦባማ ለቀዳማዊት እመቤት ሎራ ቡሽ ስጦታ ሰጥተዋቸዋል።

 

ፕሬዝዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ከባለቤታቸው ሎራ ቡሽ፣ ምክትል ፕሬዝዳንት ዲክ ቼኒ ከባለቤታቸው ሌኒ፣ ባራክ ሁሴን ኦባማ ከባለቤቶቻቸው ሚሼል ኦባማ እንዲሁም ጆ ባይደን ከባለቤታቸው ጂል ባይደን ጋር ሆነው ቡና ጠጥተዋል።

 

የፕሬዝዳንታዊ ሥልጣን ርክክቡ በምሣ ሰዓት አካባቢ በካፒቶል ይከናወናል።

 

የኢትዮጵያ ዛሬ አዘጋጅ ያሬድ ክንፈ ከዋሽንግተን ዲሲ የዛሬውን የሥልጣን ርክክብ እና ተያያዥ ዘገባዎችን ያቀርብልናል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!