Artist Tilahun GesseseEthiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 12 ቀን 2001 ዓ.ም. April 20, 2009)፦ የሙዚቃው ንጉሥ አንጋፋው ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ (የክብር ዶክተር) ከሁለት ቀናት በፊት ከነበረበት አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ ሰኞ ሚያዝያ 12 ቀን 2001 ዓ.ም. ሌሊት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

 

 

የክብር ዶክትሬት የተቀበለውና ከኢትዮጵያ የሥነ ጥበባትና የመገናኛ ብዙሃን የሽልማት ድርጅት “የሙሉ ዘመን” የሚል የክብር ሽልማት የተቀበለው አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ በከፍተኛ ሕመም ላይ እንደነበረና በአሜሪካን ሀገር ሲረዳ ቆይቶ የፋሲካ በዓልንም ከቤተሰቦቼ ጋር ማሳለፍ እፈልጋለሁ በማለቱ የፋሲካ ዕለት ከምሽቱ 2፡40 ሰዓት ላይ ከቤተሰቦቹ ጋር ቢቀላቀልም፤ ዛሬ ሌሊት በመኖሪያ ቤቱ ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል።

 

አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ ከእናቱ ወ/ሮ ጉቴ ጉሩሙ ከአባቱ አቶ ገሠሠ ንጉሴ በአዲስ አበባ ከተማ ከተወለደ መስከረም 17 ቀን 2001 ዓ.ም. 68 ዓመቱን ደፍኗል። የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ የቀብር ሥነሥርዓት መቼና የት እንደሆነ ያልተወሰነ ሲሆን፣ ቤተሰቦቹ እንደሚሉት ከሆነ በነገው ዕለት ሊሆን ይችላል።

 

የኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ለሙዚቃው ንጉሥ ክቡር ዶ/ር ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶችና አፍቃሪዎች መጽናናትን ትመኛለች።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ