በቅርቡ ወደ ታንዛኒያ ተጉዘው የነበሩ በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ አባት ከሁለት ሺህ በላይ እስረኞች በታንዛኒያ እስር ቤቶች ያለፍርድ እንደሚሰቃዩ ተናገሩ።

 

እኚህ ከየካቲት እስከ ሚያዚያ ወር ከሁለት ወር በላይ በታንዛኒያ የቆዩ ኢትዮጵያዊ እንደተናገሩት በአካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በታንዛኒያ ውስጥ ስለታሰሩት በሺሆች የሚቆጠሩ እስረኞች ሰምተው በማዘናቸው ከሚመለከታቸው የታንዛኒያ ኢሚግሬሽን ኦፊሰር ጋር እንደተነጋገሩና የኢሚግሬሽን ኦፊሰሯም፡ ቁጥራቸው ከሁለት ሺህ የሚበልጥ ኢትዮጵያዊያን በእስር ቤት እንደሚገኙ አረጋግጣላቸዋለች። አንዳንዶቹ እስረኞች ከሁለት ዓመት በላይ በእስር እንደቆዩና ወደመጡበትም ወደሚሄዱበትም መጓዝ እንዳልቻሉ ተናግራለች። ብዙዎቹ እስረኞች ወደ ደቡብ አፍሪካ በመጓዝ ላይ እንዳሉ የታሰሩ ሲሆን፡ ከእስር የሚያስፈታቸው ወገን ባለመኖሩና ቢፈቱም ወደአገራቸው የሚገቡበት ገንዘባ ስለሌላቸው፡ በዚያው እስርቤቶች በመማቀቅ ላይ ይገኛሉ።

 

አንድ የታንዛኒያ ደህንነት ባለስልጣን እስረኞቹ የታንዛኒያን ድንበር ያለፈቃድ ጥሶ ከመግባት ውጪ የፈጸሙት ምንም ወንጀል እንደሌለና፡ ታንዛኒያን ለቀው የሚወጡ ከሆነ በማናቸውም ሰዓት ሊለቋቸው እንደሚችሉ፡ ነግር ግን ታንዛኒያ እነዚህን እስረኞች በራሷ ወጪ ወዳገራቸው ልትልክ የምትችልበት አቅም እንደሌላት፡ እስረኞቹን ሊረዳና ወደመጡበት ሊመልሳቸው ወይንም ከታንዛኒአ ውጪ ወደየትም ሊያደርሳቸው የሚችል ሰው ከተገኘ ሙሉ ትብብር እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

 

ብዙ ወደደቡብ አፍሪካ እናደርሳለን የሚሉ ደላሎች አያሌ ኢትዮጵያዊያንን ቀብድ እየተቀበሉ ወደደቡብ አፍሪካ በማሻገሩ ሂደት ለእስርና ለችግር እየዳረጓቸው እንደሆነ በመገናኛ ብዙሀንና ከዚህ ችግር በሚተርፉ ወገኖች ይዘገባል። በቅርቡ ወደ መቶ ሀምሳ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን በሞዛምቢክ ከዚአ ቀደም ሲልም ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲጓዙ በማላዊ መያዛቸውን አለማቀፍና ኢትዮጵአዊአን መገናኛ ብዙሀን መዘገባቸው ይታወሳል። በታንዛኒያ ስለታሰሩት ኢትዮጵያውያን መረጃ ያጠናቀሩት ኢትዮጵያዊ እንዳሉት ከሆነ፡ ለነዚህ ሰዎች በእስር መቆየት ወደደቡብ አፍሪካ እንወስዳችኋለን ብለው ቃል የገቡት የዚህ አይነት ሰው የማመላለስና የማሻገር ስራ የሚሰሩ ደላሎች እጅ እንዳለበት ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል።

ምክንያቱን እነዚህ ደላሎች፡ ሰዎቹን ለእስር ከመዳረጋቸውም በላይ እናስፈታለን በማለት ከእስረኞቹ ዘመዶች ሌላ የገንዘብ ማግኛ ዘዴ አድርገው እየተጠቀሙበት እንደሆነ ማስረጃ እንዳላቸው ተናግረዋል። እስረኞቹ አንፈልግም ካላሉ በስተቀር፡ የትራንስፖርት ወጪአቸው እስከተሸፈነለት ድረስ የታንዛኒያ መንግስት በማናቸውም ሰዓት ወደአገራቸው ሊመልሳቸው ፈቃደኛ ስለሆነ፡ ኢትዮጵያዊያን እነዚህን ወገኖች ለመታደግ በአይ..ኤም (I.O.M.: International Organization for Migrants-) ላይ ጫና እንዲያሳድሩ አሳስበዋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!