የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የብር ምንዛሪ ማስተካከያ ማድረግ አለባት ሲል አስጠነቀቀ

World bank

ኢትዮጵያ ዛሬ (ኀሙስ ኅዳር ፳፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 8, 2016)፦ በከፍተኛ ደረጃ እያሽቆለቆለ ያለውን የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ገቢን ለማስተካከልና የወጪ ንግድ ምርቶች አቅርቦት እንዲጨምር ለማበረታታት፣ ኢትዮጵያ የብር የምንዛሪ ምጣኔን እውነተኛውን የኢኮኖሚ አቅሟን በሚያመላክት ደረጃ ማስተካከል ይገባታል ሲል አሳሰበ። አሁን ያለው የብር ምንዛሪ ሚዛኑን የሳተና ከእውነተኛ አቅሙ በላይ የገዘፈ መሆኑንም ጠቁሟል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አባት የ፲፫ ዓመት ልጁን ገድሎ ራሱን አጠፋ

Suicide gun

ኢትዮጵያ ዛሬ (ኀሙስ ኅዳር ፳፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 8, 2016)፦ ለአስራ ሦስት ዓመት ካለእናት ልጁን ሲያሳድግ የቆየ አባት፣ የ፲፫ ዓመት ልጁን ገንዘብ ሰርቀሃል በሚል ባደረሰበት ድብደባ የልጁን ሕይወት መቅጠፉን ሲረዳ የገዛ ሕይወቱን በሽጉጥ አጠፋ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያውያኑ በካይሮ እንግልት እየደረሰባቸው ነው

Ethiopian refugees in Egypt

ኢትዮጵያ ዛሬ (ማክሰኞ ኅዳር ፳፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 6, 2016)፦ የኦሮሞ ብሔረሰብ ሆነው መንግሥትን በመቃወማቸው ምክንያት በደረሰባቸው አፈናና እንግልት አገር ለቀው የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን በግብጽ ሌላ ችግር ገጥሟቸዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች መርጃ (ዩኤንኤችሲአር) ጉዳያቸውን ውድቅ እያደረገባቸው ወደ አገር ቤት ለመመለስም አስቸጋሪ ሆኖባቸው በሜዲትራኒያን ባህር መጓዝ ግድ ሆኖባቸዋል። በዚህም ብዙዎቹ ሕይወታቸውን በማጣት ላይ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የግብጽና የኤርትራ ፕሬዝዳንቶች በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር ተገናኙ

Sisi and Isaias met in Cairo

ኢትዮጵያ ዛሬ (ቅዳሜ ኅዳር ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 3, 2016)፦ የግብጹ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አልሲሲ ከኤርትራው አቻቸው ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በካይሮ ተገናኙ። የተገናኙት በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር እና በቀጣይ ጉዟቸው ላይ ሊመክሩ እንደሆነ ተዘገበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አብርሃ ደስታና ዳንኤል በድጋሚ ሊታሰሩ ነው፤ እነ ሀብታሙ በነጻ ተሰናበቱ

ሀብታሙ አያሌው፣ የሽዋስ አሰፋ እና አብርሃም ሰለሞን በነጻ ሲሰናበቱ፤ ዳንኤል ሺበሺ እና አብርሃ ደስታ ተከላከሉ ተባሉ

Ene Abraha Desta

ከፍተኛ ፍርድ ቤት በነፃ ባሰናበታቸው አምስት ተከሳሾች (ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ አብርሃ ደስታ፣ የሽዋስ አሰፋ እና አብርሃም ሰለሞን) ላይ አቃቢ ሕግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብሎ ዓመት ከሦስት ወር በላይ በቀጠሮ ሲራዘም የነበረው ጉዳይ ዓርብ ኅዳር ፳፫ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. (Dec. 2, 2016) ብይን ተሰጥቶበታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኞች ስደት ቁጥር ጨመረ

- ጋዜጠኛ ሁሴን አብዱልቀኒ፣ ብዛየሁ እና ታምሩ ወደ አገር አይመለሱም!

- ፳፯ የስፖርት ጋዜጠኞች በስደት ይገኛሉ

Ethiopian sport journalists

(ኢትዮኪክ) የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር ዓመታዊ ስብሰባውን በኢንተር ኮንቲነንታል ሆቴል በ2008 ሲያካሄድ፤ የማኅበሩ ም/ፕሬዚዳንት ጋዜጠኛ ሁሴን አብዱልቀኒ እና ጋዜጠኛ አምሀ መድረኩን ሲመሩት እንደነበር የሚታወስ ነው። ሆኖም ዘንድሮ ሁለቱን ጋዜጠኞች ጨምሮ በማኅበሩ ውስጥ አምና የነበሩ ዘንድሮ በስደት ከማኅበሩ 8 የሚደርሱ የስፖርት ጋዜጠኞች አይኖሩም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አና ጎሜዝ የፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን እስር በጽኑ ኮነኑ

Ana Gomes

ኢትዮጵያ ዛሬ (ዓርብ ኅዳር ፳፫ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 2, 2016)፦ በዶ/ር መረራ ጉዲና መታሰር ስጋት እንደገባቸው በመግለጽ፤ አስቸኳይ ደብዳቤ ለአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ክፍል የጻፉት የአውሮፓ ፓርላማ አባል አና ጎሜዝ፤ የኢትዮጵያ ዋነኛ የልማት አጋር የሆነው ሕብረቱ ፈጣን እርምጃ እንዲወስድ ጠየቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ ወዳጅ ፊደል ካስትሮ አረፉ

Fidel Castro

ኢትዮጵያ ዛሬ (ቅዳሜ ኅዳር ፲፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 26, 2016)፦ የቀድሞው የኩባ ፕሬዝዳንት ፊደል ካስትሮ በዘጠና ዓመታቸው ትናንት ማረፋቸው ተሰማ። ፊደል ካስትሮ ኩባን ለ፵፱ (49) ዓመታት ከመምራታቸውም ባሻገር በአብዮተኝነታቸውና በታጋይነታቸው በዓለም ላይ ታዋቂ የነበሩ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ወዳጅና ረዳት እንደነበሩም ይታወሳል። ኩባ የቀድሞ ፕሬዝዳንትዋን ሕልፈተ ሕይወት አስመልክታ ለዘጠኝ ቀናት ብሔራዊ የኀዘን ቀን አውጃለች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ መንግሥት በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን አብራሪዎች ለቀቀ

The vintage planes had taken off from Sudan for the three-hour flight into Ethiopia

ኢትዮጵያ ዛሬ (ዓርብ ኅዳር ፲፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 25, 2016)፦ ትናንት የአየር ንብረቴን በሕገ ወጥ መንገድ ሲያቋርጡ ያዝኳቸው ያላቸውን 20 ቀላል አውሮፕላኖችንና በውስጡ የሚገኙ 42 የተለያዩ ሀገራት ዜጎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የተናገረው መንግሥት አሁን እንደለቀቃቸው ይፋ አድርጓል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!