ዳንኤል በቀለ እና ነፃነት ደምሴ አመክሮ ተከለከሉ

Ato Daniel Bekele (left top) & Ato Netsanet Demiseዓቃቤ ሕግ ይግባኝ ሊጠይቅ ይችላል

Ethiopia Zare (ሰኞ ጥር 19 ቀን 2000 ዓ.ም. January 28,2008)፦ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች መሪ የሆኑትና ምርጫ 97ን ተከትሎ ኢህአዴግ እስር የጨመራቸው አቶ ዳንኤል በቀለ እና አቶ ነፃነት ደምሴ ሊያገኙት ይገባ የነበረውን አመክሮ መከልከላቸውን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ አስረዳ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ነገ ለሚጀመረው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ፤ የጋዜጣ አዟሪዎች እየታፈሱ ነው

Ethiopia Zare (እሁድ ጥር 18 ቀን 2000 ዓ.ም. January 27,2008)፦ በነገው ዕለት ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚጀመረው  የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ስብስባ የአፍሪካ መሪዎች አዲስ አበባ እየገቡ ሲሆን፣ የነሱን መግባት ተከትሎ ማንኛውም የጋዜጣና የሎተሪ አዟሪ እየታፈሰ ይገኛል። ጠዋት የታሰረ አዟሪ ሲመሻሽ ይለቀቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቅርቡ ከእስር ሊፈቱ የሚችሉት ስም ዝርዝር

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ጥር 17 ቀን 2000 ዓ.ም. January 26,2008)፦ ምርጫ 97ን አስከትሎ በተከሰተው የፖለቲካ ነውጥ በኢህአዴግ አመራር በግፍ የታሰሩ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ አባላትና ደጋፊዎችን የማስፈታት ሂደት በምክትል ሊቀመንበሯ የሚመራው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባቋቋመው የእስረኞችን ጉዳይ በሚከታተል ንዑስ ኮሚቴ አማካኝነት ከሽማግሌዎች ጋር በተደረገው ጥረት ቢያንስ 29 እስረኞች በቅርቡ ከእስር እንደሚለቀቁ ምንጮቻችን ገለጹ።

“የማያስፈልግ ዋጋ እንዳይከፈል የስም ለውጥ መደረግ አለበት ብዬ በግሌ አምናለሁ” አቶ ሙሉነህ ኢዩኤል

እነወ/ት ብርቱካንን የተቀበሉ በሳውላ ታሰሩ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥር 13 ቀን 2000 ዓ.ም. January,22,2008):- በደቡብ ኢትዮጵያ ሳውላ ከተማ በወ/ት ብርቱካን የተመራውን ልዑካን የተቀበሉ የቅንጅት ደጋፊዎች ለእስርና ለእንግልት መዳረጋቸውን ከስፍራው የደረሰ ዘገባ ጠቆመ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢሕአዴጉ ተወካይ ራሳቸውን ከፓርላማ አገለሉ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥር 13 ቀን 2000 ዓ.ም. Jan,22,2008):- ወያኔ/ኢሕአዴግን ወክለው ከደቡብ ህዝቦች ተወክለው ፓርላማ ከገቡት ተመራጮች አንዱ የሆኑት አቶ ክፍሌ ደቦባ ለአፈ ጉባኤው በጻፉት ደብዳቤ ከፓርላማ ራሳቸውን ያገለሉ መሆናቸውንና አባልነቴን አልፈልግም ማለታቸውን ታማኝ ምንጮች ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...