“አልቅሳችሁ አትቅበሩኝ” የአሰፋ ጫቦ ሥርዓተ ቀብር ተከናወነ

አክሊሉ ሀብተወልድ

Assefa Chabo | አሰፋ ጫቦ
አቶ አሰፋ ጫቦ (፲፱፻፴፮ - ፳፻፱ ዓ.ም. | እ.ኤ.አ. 1944 - 2017)

(ሚያዝያ 27 ቀን 2009 ዓ.ም)፡- ሚያዝያ 27 ታሪካዊ ቀን ናት፤ ከሰባት አስርት ዓመታት በፊት ከፋሺስት ጣሊያን ወረራ በኋላ አገር ነጻነቷን ያወጀችበት ሕዝብ እንደ ሕዝብ ደስ የተሰኘበት ቀን ናት። የዛኔ በስደት የነበሩት ንጉሥ ከስደት መልስ አገራቸው የገቡበት ቀን ነው፤ ዛሬ ግን በደርግ ዘመነ መንግሥት በጽሑፋቸው ለአስር ዓመት ከስድስት ወር በማዕከላዊ ካሳለፉ በኋላ በዘመነ ኢሕአዴግ የ16 ዓመት እስር የተፈረደባቸው። ላለፉት 25 ዓመታት በስደት በአገረ አሜሪካ ሕይወታቸውን የገፉት የሦስት ልጆች እና የዘጠኝ የልጅ ልጆች አባት፤ አገራቸውን ለማቅናት ዕድሜ ዘመናቸውን ሲወጡ ሲወርዱ፤ አገሬን ... አገሬን እያሉ ሞታቸው ከስደት አገር ከወደ ዳላስ የተሰማው አንጋፋው ጎምቱ ጸሐፊ፤ የሕግ ባለሙያ፤ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ፖለቲከኛና ምሁር የአቶ አሰፋ ጫቦ ሥርዓተ ቀብር የተከናወነበት ቀን ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እውቁ ፖለቲከኛና አንጋፋው ምሁር አቶ አሰፋ ጫቦ አረፉ

Assefa Chabo
አቶ አሰፋ ጫቦ

ኢዛ (ሰኞ ሚያዝያ ፲፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. April 24, 2017)፦ በአንደበተ ርዕቱነታቸውና በብዕራቸው በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆኑት አቶ አሰፋ ጫቦ እሁድ ሚያዝያ ፲፭ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. (April 23, 2017) በሰባ ሦስት ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በግብጽ የሆሳዕናን በዓል እያከበሩ የነበሩ አርባ ሦስት ሰዎች በሽብርተኞች ቦምብ ተገደሉ

አንድ መቶ ሰዎች ቆሰሉ
ጥቃቱ የተፈጸመው በታንታ እና በአሌክሳንድሪያ ከተሞች ነው
ኃላፊነቱን አይሲስ ወስዷል

Church bombing in Tanta, Egypt
በግብጽ ታንታ ከተማ በሽብርተኞች ቦንብ ጥቃት የደረሰበት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ውስጥ

ኢዛ (እሁድ ሚያዝያ ፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. April 9, 2017)፦ ክርስቲያኖች የሆሳዕና በዓልን እያከበሩ ባሉበት በዛሬው ዕለት፣ በግብጽ ሁለት ከተሞች አርባ ሦስት ሰዎች በሽብርተኞች ሲሞቱ አንድ መቶ አስራ ዘጠኝ ሰዎች ቆሰሉ። የሽብር ጥቃቱን ኃላፊነት አይሲስ መውሰዱ ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሽብር የተጠረጠር የጭነት መኪና በስቶክሆልም ሦስት ገድሎ፣ ስምንት አቆሰለ

Stockholm attack, April 7, 2017
የጭነት መኪናው ከተጋጨ በኋላ በአካባቢው የሚገኙ ሰዎች ራሳቸውን ለማዳን ጥረት ሲያደረጉ (ፎቶ፣ Aftonbladet)

ኢዛ (ዓርብ መጋቢት ፳፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. April 7, 2017) ዛሬ ረፋዱ ላይ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም አንድ የጭነት መኪና በመዲናዋ እምብርት ሕዝብ በብዛት በሚተላለፍበት አካባቢ በሰዎች ላይ በመንዳት እና በስተመጨረሻም ኦሊየንስ የሚባለው ሱቅ ከሚገኝበት ሕንጻ ጋር ተላትሞ ነድዷል። በአደጋው ሦስት ሰዎች ሲሞቱ፣ ስምንት ሰዎች ቆስለዋል። ፖሊስ በቦታው ላይ በሰዓቱ ታይቷል ብሎ ያለውን ሰው ፎቶግራፍ ለሕዝብ ይፋ አድርጓል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

121ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በዳላስ ቴክሳስ

121th Adwa Victory Day Anniversary in Dallas Texas
121ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በዳላስ ቴክሳስ፣ መጋቢት ፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም.

የመላው ጥቁር ኩራት የሆነውን የአድዋ ድል 121ኛውን መታሰቢያ በዓል በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በዳላስ ቴክሳስ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል። የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓሉን ያዘጋጀው በዳላስና ፎርትወርዝ የኢትዮጵያውያን ጉዳዮች የውይይት መድረክ ሲሆን፣ ዘንድሮ ሲያዘጋጅ ለሦስተኛ ጊዜ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በተደረመሰው የቆሻሻ ክምር ሳቢያ የሟቾች ቁጥር 113 ደረሰ

የአዲስ አበባ መስተዳድር ለማይጠቀምበት የሰንዳፋ ቆሻሻ መጣያ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ አውጥቷል

የአስከሬን ፍለጋው ባለመጠናቀቁ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል

Suspected to be missing
በቆሻሻ ክምሩ መደርመስ ሳቢያ ጠፍተዋል የተባሉና በመፈለግ ላይ የነበሩ ሕጻናት (ፎቶ፣ REUTERS/Tiksa Negeri)

ኢዛ (ሐሙስ መጋቢት ፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Mar. 16, 2017)፦ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ መጋቢት 2 ቀን ከምሽቱ 1፡30 ላይ በተለምዶ ”ቆሼ” ወይም ”ቄስ” ሠፈር እየተባለ በሚጠራው እና በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ውስጥ በሚገኘው የቆሻሻ ክምር በመደርመሱ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር እስከ ትናንት ማምሻ ድረስ 113 መድረሱ ታወቀ። በዛሬው ዕለትም የአስከሬን ፍለጋው ሥራ የቀጠለ ሲሆን፣ የሟቾች መጠን ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በጋምቤላ 18 ተገደሉ፣ ከ22 በላይ ሕጻናት ታፍነው ተወሰዱ

የጋምቤላ ጥቃትና ታፍነው የተወሰዱት ሕጻናት ጉዳይ

Gambela
የሙርሊ ታጣቂዎች ወደ 13 የሚሆኑ ሰዎች ሞተዋል፤ 21 የሚሆኑ ሕጻናት ታፍነው በሞርሊ ተወስደዋል

(ዶቼቬለ) ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በጋምቤላ ክልል አኝዋክ ዞን በጎን እና በጆር ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች ውስጥ ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሌ ጎሣ ታጣቂዎች በጣሉት ጥቃት ከአስራ ስምንት ሰዎች በላይ መገደላቸውንና ከ22 በላይ ሕጻናት ታግተው መወሰዳቸውን ተቀማጭነቱን ለንደን ላይ ያደረገው ”አኝዋ ሰርቫይቫል” የተሰኘው ድርጅት ገለፀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መሪራስ አማን በላይ በስድሳ አምስት ዓመታቸው አረፉ

Meriras Aman Belay
መሪራስ አማን በላይ፣ በስድሳ አምስት ዓመታቸው ከዚህ ዓለም አረፉ

ኢዛ (ዓርብ የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Mar. 3, 2017)፦ የተከበሩት ባለታሪክ፣ ፈላስፋ፣ ባለመድኃኒት፣ የነገረ-መለኮት አዋቂ እና የ24 መጻሕፍት ደራሲ የነበሩት መሪራስ አማን በላይ ባደረባቸው ሕመም የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. ፌብሩዋሪ 17 ቀን 2017) በሎስ አንጀለስ ከተማ በተወለዱ በ65 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ተለዩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

”ዶ/ር መረራ ጉዲና ከአንድ ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር በላይ ንብረት እንዲውድም አስደርጓል” የዓቃቤ ሕግ ክስ

ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ጃዋር መሐመድ፣ ኢሳት እና ኦኤምኤን ክስ ተመሰረተባቸው

Dr. Merera, Dr. Berhanu & Jawar
ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ጃዋር መሐመድ፣

ኢዛ (ዓርብ የካቲት ፲፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Feb. 24, 2017)፦ ፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በዶ/ር መረራ ጉዲና፣ በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ በጃዋር መሐመድ፣ በኢሳት እና በኦኤምኤን ላይ፤ ”ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማስወገድ ሙከራ አድርገዋል” በሚል ትናንት ክስ መመስረቱ ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!