እንግሊዝ ለኢትዮጵያ መንግሥት የሰጠችው እርዳታ እያወዛገበ ነው

Theresa May
የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ወ/ሮ ቴሬሳ ሜይ (ፎቶ AP)

ኢዛ (ኀሙስ የካቲት ፲፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Feb. 23, 2017)፦ የእንግሊዝ መንግሥት ለኢትዮጵያ መንግሥት፣ በተለይም ለፖሊስ፣ ለመከላከያ፣ ለፍትሕ ሚኒስቴር እና ለዲፕሎማቲ አባላት እየሰጠችው ያለውና አንድ ቢሊዮን ፓውንድ ወጪ ያደረገችበት በድኅንነትና ማኔጅመንት የከፍተኛ ዲግሪ ሥልጠና ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠመው ሲሆን፣ ጉዳዩ እያወዛገበ ይገኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፕ/ር ሪቻርድ ፓንክረስት ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ

Sylvia's grave and Richard Pankhurst
የሲልቪያ መካነ መቃብር እና ፕ/ር ሪቻርድ ፓንክረስት (ዲዛይን @ ኢዛ)

ኢዛ (ማክሰኞ የካቲት ፲፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Feb. 21, 2017)፦ በኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪነታቸው ታዋቂና አንጋፋ የሆኑት የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስ ሥርዓተ ቀብር አዲስ አበባ በሚገኘው መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በብሔራዊ ክብር ዛሬ ተፈጸመ። በሥርዓቱ ላይ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ሊቃነ ጳጳሳት፣ የተለያዩ የኃይማኖት አባቶች፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና አድናቂዎቻቸው ተገኝተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአንበሳ አውቶቡስ ዲፖ የ፵፮ ሚሊዮን ብር ንብረት በእሳት አደጋ ወደመ

Anbesa autobus

ኢዛ (ሰኞ የካቲት ፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Feb. 13, 2017)፦ አዲስ አበባ፣ ጀሞ አካባቢ በሚገኘው በአንበሳ የከተማ አውቶቡስ ድርጅት ጋራዥ ላይ ዛሬ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ በደረሰ እሳት አደጋ አርባ ስድስት ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገለጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ለ19 ዓመት የተያዘ የዓለም ክብረወሰን ሰበረች

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በሴቶች ፪ ሺህ ሜትር ሁለት የዓለም ክብረወሰኖች ሰበረች

Genzebe Dibaba breaks world 2000M record in Sabadell

ኢዛ (ረቡዕ የካቲት ፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Feb. 08, 2017)፦ ትናንት ምሽት ላይ ስፔይን በምትገኘው ሳባዴል ከተማ በሁለት ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር የገባችበት ሰዓት አዲስ የዓለም ክበረወሰን ማስመዝገቧ ታወቀ። ክብረወሰኑ የተሰበረው ከአስራ ዘጠኝ ዓመት በኋላ ነው። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በታገዱት ሰባት አገራት ዜጎች የተገደለ አሜሪካዊ የለም

እገዳው ከፕ/ት ትራምፕ ጋር የንግድ ግንኙነት ያላቸውን አገራት አላካተተም

Dubai Trump Golf Club

ኢዛ (ሰኞ ጥር ፳፪ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Jan. 30, 2017)፦ ፕ/ት ዶናልድ ትራምፕ ባወጡት አስቸኳይ እገዳ ውስጥ በተካተቱት ሰባት አገራት ዜጎች እ.ኤ.አ. ከ1975 እስከ 2015 ድረስ አንድም አሜሪካዊ አለመገደሉን ሲኤንኤን ዘገበ። በተቃራኒው በእነዚሁ ዓመታት ውስጥ የሳውዲ ዐረቢያ ዜጎች 2,369፣ የተባበሩት ዐረብ ኢምሬትስ ዜጎች ደግሞ 314፣ እንዲሁም ግብጻውያን 162 አሜሪካውያንን መግደላቸውን ዘገባው አክሎ ገልጧል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፕሮፈሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ መጽሐፍ በላስ ቬጋስ

Prof. Fikre Tolossaታህሳስ ፲፱ ቀን ፪ሺ፱ ዓ/ም (DECEMBER 28,2016) ከአሜሪካን ታዋቂ ከሚባሉ ከተሞች መካከል አንዷ በሆነችው በላስ ቬጋስ ከተማ “አገርህን እወቃት፣ ከጠላትም ጠብቃት” በሚል መሪ ቃልና ቅስቀሳ የታደሙው የከተማው ነዋሪ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳን በከፍተኛ ጭብጨባና ከፍ ባለ አክብሮት ወደ አዳራሹ ሲገቡ ተቀብሏቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በስናይፐር የታጀበው ጥምቀት በጎንደር

Timket festival

ከጎንደር ታቦቱን ከመቅደሱ ገብተው መሸከም እስኪቀራቸው ድረስ የመንግሥት ወታደሮች ካህናቱን ቶሎ በሉ፣ ቶሎ በሉ እያሉ ያጣድፏቸው ነበር። ታቦት በራሳቼው ላይ የተሸከሙ አባቶች ሁለት እጆቻቸው ታቦቱን ቢደግፉም እንባዎቻቸው በጎንደር አስፋልት ላይ ጠብ፣ ጠብ፣ እያሉ ሲፈሱ ከበርካታ ካህናት ዓይኖች ቀረብ ብዮ አስተውያለሁ፣ መስቀል ኃይል ነው ብላ የምታምን ቤተክርስቲያን ዛሬ ስናይፐር ኃይል ነው የሚል መንግሥት በስናይፐር የጎንደር ታቦቶች እንዲታጀቡ አደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ እና አወቀ አያሌው በስፔን አገር አቋራጭ ውድድር አሸነፉ

Senbere Teferi

ኢዛ (ሰኞ ጥር ፰ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Jan. 16, 2017)፦ ትናንት በስፔን አገር የሲቪያ ከተማ አካል በሆነችው ሳንቲፖንሴ ከተማ በተካሄደው 35ኛው አገር አቋራጭ ዓለም አቀፍ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ አንደኛ በመውጣት አሸንፋለች። በወንዶች ደግሞ ለባህሬን የሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊው አትሌት አወቀ አያሌው አንደኛ ሲወጣ፣ አትሌት ታፈሰ ሰቦቃ ደግሞ ኢትዮጵያን ወክሎ ሦስተኛ ወጥቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ዳግም ታሪክ ሠራ

Houston half marathon Feyisa Lilesa 2nd place

ኢዛ (ሰኞ ጥር ፰ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Jan. 16, 2017)፦ ኢትዮጵያዊው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ትናንት በሂዩስተን በተካሄደው የግማሽ ማራቶችን ውድድር ዳግም ታሪክ ሠራ። ውድድሩን ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀ ሲሆን፣ እንደለመደው እጆቹን በማመሳቀል በአገሩ ውስጥ መንግሥት እያካሄደ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት አሳይቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!