"የጭካኔና ገደቦች ዓመት በኢትዮጵያ" ሂዩማን ራይትስ ዎች

”መብቶች ይከበሩ፣ ለሕዝብ ቅሬታዎች መልስ ይሰጥ” ሂዩማን ራይትስ ዎች

Irrecha massacre in Ethiopia, 2016

ኢዛ (ዓርብ ጥር ፭ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Jan. 13, 2017)፦ ሂዩማን ራይትስ ዎች ትናንት ባወጣው ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት እ.ኤ.አ. 2016 የሰብዓዊ መብቶች ቀውስ ውስጥ ወድቃለች ማለቱ ተደመጠ። ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ መሰረታዊ መብቶችን ገድባ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ደም አፍሳሽ አፈናዋን ቀጥላለች፣ በዘፈቀደ ታስራለች፣ ማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀንን ገድባለች በማለት ሪፖርቱ ያትታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በመጨረሻ ሀብታሙ አያሌው ለሕክምና ከአገር ወጣ

Habtamu Ayalew arrived in USA

ኢዛ (ዓርብ ጥር ፭ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Jan. 13, 2017)፦ በአገር ውስጥ ታክሞ መዳን በማይችል ሕመም ሲሰቃይ የከረመው ፖለቲከኛ ሀብታሙ አያሌው አሜሪካ ገባ። በእስር ቤት ሳለ በሕክምና ክትትል ማጣት ሳቢያ በቀላሉ ሊድን ይችል የነበረ ሕመሙ ከተፈታም በኋላ ጸንቶበት ሆስፒታል ተኝቶ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቱርክ በድጋሚ በሽብርተኞች ተጠቃች

Turkey, Izmir bomb attack

ኢዛ (ኀሙስ ታህሳስ ፳፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Jan. 05, 2017)፦ በዛሬው ዕለት ኢዝሚር በተባለች የቱርክ ከተማ በፍርድ ቤት አቅራቢያ ሦስት ታጣቂዎች የሽብር ጥቃት ፈጸማቸውንና ሁለቱ ጥቃት ፈጻሚዎች፣ አንድ ፖሊስ እና አንድ የፍርድ ቤቱን ሠራተኛ መግደላቸውን የቱርክ የመንግሥት መገናኛ ብዙኀን ዘገቡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቦሌ መ/ደ/ፍ/ቤት በአቤል ዋበላ እና በኢትዮጵያ አየር መንገድ በነበረው ክርክር ለአየር መንገዱ ፈረደ

አቤል ዋበላ ከሚያዝያ 2006 ጀምሮ ለ18 ወራት "በፀረ ሽብርተኝነቱ" አዋጅ ከዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ጋር ታስሮ ከርሞ በጥቅምት 2008 በነጻ ሲሰናበት የቀድሞ መሥሪያ ቤቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ "መልሼ አልቀበልህም" በማለቱ አቤል ክስ መመሥረቱ ይታወሳል። አየር መንገዱም "እንዲያውም ለሥራ ሥልጠና ያወጣሁበትን ወጪ ካሣ ይክፈለኝ" የሚል ሌላ ክስ መሥርቶበት፣ አቤል የመሠረተው ክስ እስኪጠናቀቅ የአየር መንገዱ ክስ በእንጥልጥል እንዲቆይ ተደርጎ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ አበባ "በአዲሱ ማስተር ፕላን ወደ ጎን መለጠጧን አቁማ ወደ ላይ ከፍ ማለት ትጀምራለች" አዲሱ ኮሚሽን

Addis Ababa

ኢዛ (ረቡዕ ታህሳስ ፳፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Jan. 04, 2017)፦ በ1994 ዓ.ም ተግባራዊ መደረግ የጀመረው ዘጠነኛው ማስተር ፕላን በ2006 ዓ.ም. የመጠቀሚያ ጊዜው አብቅቷል። አሥረኛው ማስተር ፕላን ከኦሮሚያ ልዩ ዞን ጋር አቀናጅቶ ለማካሄድ በርካታ ሥራዎች የተሠሩ ቢሆንም፣ ከኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ በመቅረቡ እንዲቀር ተደርጓል። በዚህ ምክንያት ባለፉት አራት ዓመታት አዲስ አበባ ይፋ ማስተር ፕላን ሳይኖራት ቆይቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጀግናው ሻምበል ምሩጽ ይፍጠር ሥርዓተ ቀብር በወታደራዊ ሥርዓት ተፈፀመ

ለክብሩ ዘጠኝ ጊዜ ተተኮሰ

Mirust Yifter funeral

በኦሊምፒክ፣ በሉላዊና በአህጉራዊ የአትሌቲክስ መድረኮች በ1960ዎቹና በ1970ዎቹ ተደራራቢ ድሎቹ ነግሦ የነበረው ሻምበል ምሩጽ ይፍጠር ሥርዓተ ቀብር፣ እሑድ ታኅሣሥ 23 ቀን 2009 ዓ.ም. በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ የሕብረቱን ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ሥራ በይፋ ጀመረች

United Nations Security Council

ኢትዮጵያ ዛሬ (ሰኞ ታህሳስ ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Jan. 02, 2017)፦ ባለፈው ሰኔ ወር ላይ በጊዜያዊ አባልነት የተመረጠችው ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2017 አዲስ ዓመት መግቢያ ላይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ ካውንስል አባልነቷን በይፋ መጀመሯ ተዘግቧል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ደረሰ

Samara campus viewኢትዮጵያ ዛሬ (ዓርብ ታህሳስ ፳፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 30, 2016)፦ በአፋር ክልል የሚገኘው ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ማታ ከምሽቱ አንድ ስዓት ተኩል አካባቢ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ እንደደረሰበት ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረገጽ የደረሰው ዘገባ አስረዳ። በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ አደጋ ባይኖርም፤ በቃጠሎው የወደመው ንብረት ግምቱ ምን ያህል እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

”ሩዙ የፕላስቲክ ሳይሆን የተመረዘ ነው” ናይጄሪያ

Plastic rice in Nigeria

ኢትዮጵያ ዛሬ (ዓርብ ታህሳስ ፳፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 30, 2016)፦ በናይጄሪያ የፕላስቲክ ሩዝ ተሰራጭቷል ተብሎ የወጣውን ሪፖርት አስመልክቶ፤ ”ሩዙ የፕላስቲክ ሳይሆን የተመረዘ ነው” ሲል የናይጄሪያ ብሔራዊ የምግብና የመድኃኒት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ማስተባበያ ሰጠ። ሩዙ ከቻይና ወደ ናይጄሪያ የገባ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕ/ር መረራ ጉዲና በሽብር ወንጀል ሊከሰሱ ነው

Prof. Merera Gudina

ኢትዮጵያ ዛሬ (ኀሙስ ታህሳስ ፳ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 29, 2016)፦ ባለፈው ኅዳር ፳፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. በአውሮፓ ሕብረት ስብሰባ ላይ ተገኝተው አዲስ አበባ ሲገቡ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በኮማንድ ፖስቱ የታሰሩት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር የሆኑት ፕ/ር መረራ ጉዲና በሽብር ወንጀል ሊከሰሱ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!