ይኸ ቪዲዮ የቦብ ማርሊን ”No Women, No Cry” ሙዚቃ ”No Women, No Drive” በሚል ግጥሙንና የሙዚቃ መሣሪያዎቹን በመቀየር የተሠራ ሙዚቃ ሲሆን፣ ዩቲዩብ ላይ በተለቀቀ በሁለት ቀን ውስጥ ከ3 ነጥብ 6 ሚሊዮን ጊዜ ታይቷል። በሳዑዲ ዐረቢያ ያለው ሥርዓት ሴቶች መኪና እንዳይነዱ የሚያግድ መሆኑን በምፀታዊ ግጥሙ የሚነካ ሲሆን፣ ዘፋኙ ሂሻም ፋጊህ ሲባል ሙዚቃውን ካቀናበሩት ውስጥ አላ ዋርዲ ይገኝበታል። አላ ዋርዲ ሳዑዲ ዐረቢያ ውስጥ የሚኖር ኢራናዊ የሙዚቃ አቀንቃኝና ባለሙያ ነው።

አርቲስት አላ ዋርዲ ከአራት ዮርዳኖሳውያን ጋር በመሆን አ.ኤ.አ. 2011 ሐያጃን የተባለውን ሮክ በዐረብኛ የሚጫወት የሙዚቃ ቡድን (ባንድ) መስርቷል። አላ ዋርዲ በባንዱ ውስጥ በአቀንቃኝነት፣ ኪቦርድ እና አኮስቲክ ጊታር በመጫወት ያገለግላል። ቡድኑ ግንቦት 2013 ላይ ”ያ ባይ” የተሰኘውን የመጀመሪያውን አልበም አውጥቶ ነበር። (ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ