በዚህ አምድ ስር የሙዚቃ ቪዲዮዎች ይስተናገዱበታል። እርስዎም ያለዎትን ወይንም ሌሎች ድረ ገጾችና ተመሳሳይ የመገናኛ ብዙኃኖች ጋር ያዩአቸውንና ሌሎቻችንም ብናያቸው ሊያዝናኑንና ሊያስተምሩን ይችላሉ የሚሏቸውን ድረ-ገጻችን ላይ ባለው የቀጥታ ኢ-ሜይል መላኪያችን እዚህ በመጫን ይላኩልን። ወይንም በ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ያገኙናል።

"ጠኃይቱ" የኛ፣ ከአስቴር አወቀ ጋር

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

"ጠኃይቱ" የኛ፣ ከአስቴር አወቀ ጋር የተጫወቱት፣ የአጤ ምኒልክን ባለቤት እቴጌ ጣይቱን እና በኢትዮጵያ ታሪክ መልካሙን ሁሉ ያደረጉ ሴት ኢትዮጵያውያንን በማሰብና በመዘከር የተሠራ ሙዚቃ መሆኑን አስበው ይምልከቱ፣ ያድምጡ!

”ኖ ዉሜን፣ ኖ ድራይቭ” ሂሻም ፋጊህ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ይኸ ቪዲዮ የቦብ ማርሊን ”No Women, No Cry” ሙዚቃ ”No Women, No Drive” በሚል ግጥሙንና የሙዚቃ መሣሪያዎቹን በመቀየር የተሠራ ሙዚቃ ሲሆን፣ ዩቲዩብ ላይ በተለቀቀ በሁለት ቀን ውስጥ ከ3 ነጥብ 6 ሚሊዮን ጊዜ ታይቷል። በሳዑዲ ዐረቢያ ያለው ሥርዓት ሴቶች መኪና እንዳይነዱ የሚያግድ መሆኑን በምፀታዊ ግጥሙ የሚነካ ሲሆን፣ ዘፋኙ ሂሻም ፋጊህ ሲባል ሙዚቃውን ካቀናበሩት ውስጥ አላ ዋርዲ ይገኝበታል። አላ ዋርዲ ሳዑዲ ዐረቢያ ውስጥ የሚኖር ኢራናዊ የሙዚቃ አቀንቃኝና ባለሙያ ነው።

አርቲስት አላ ዋርዲ ከአራት ዮርዳኖሳውያን ጋር በመሆን አ.ኤ.አ. 2011 ሐያጃን የተባለውን ሮክ በዐረብኛ የሚጫወት የሙዚቃ ቡድን (ባንድ) መስርቷል። አላ ዋርዲ በባንዱ ውስጥ በአቀንቃኝነት፣ ኪቦርድ እና አኮስቲክ ጊታር በመጫወት ያገለግላል። ቡድኑ ግንቦት 2013 ላይ ”ያ ባይ” የተሰኘውን የመጀመሪያውን አልበም አውጥቶ ነበር። (ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)

 

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!