“የሕወሓት ማፊያ ቡድን አገሩን ሲጠብቅ የነበረውን ሠራዊት ጨፍጭፎ ግፍ ሠርቷል” ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
L. Gen. Bacha Debele

(ኢዛ) ሕወሓት በሰሜን ዕዝ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ የፈጸመውን ሰቅጣጭ ተግባር በኢትዮጵያ ውስጥ ይፈጸማል ብሎ ማመን እጅግ ይከብዳል፤ ግን ኾኗል።

በትግራይ ሚሊሻ፣ ልዩ ኃይል አባላት፣ የሠራዊቱ አባላትና ኦነግ ሸኔ የተፈጸመውን ዘግናኝ ተግባር በተመለከተ ዛሬ ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ በሰጡት መግለጫ፤ የመቀሌው ጁንታ ቡድን የፈጸመው ተግባር ምናልባትም በአገሩ ሠራዊት ላይ ጨለማን ተገን በማድረግ የወጋ ብቸኛው የዓለም ታሪክ ሊኾን የሚችል ነው።

ሰሜን የሚገኘውንና ከሕወሓት ጋር እየተዋጋ ያለውን የአገር መከላከያ ሠራዊት ጎብኝተው ወደ አዲስ አበባ የተመለሱት ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ፤ መቀሌ የመሸገው ጁንታው የሕወሓት ቡድን በሰሜን ዕዝ ላይ የፈጸመውን ዘግናኝና አረመኔያዊ ድርጊት አስመልክቶ በዓይናቸው ያዩትንና ያሰባሰቡትን መረጃ ዛሬ ማክሰኞ ኅዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ይፋ አድርገዋል። ለመመልከትና ለማዳመጥ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ! (ኢዛ)

ሁሉን አቀፍ አገራዊ የመግባባት ኮሚቴ የሲያትሉ መግለጫ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
ሁሉን አቀፍ አገራዊ የመግባባት ኮሚቴ በሲያትል

23 የተለያዩ የማኅበረሰባዊ ድርጅቶችን (ሲቪክ ማኅበራትን) ያካተተው ”ትብብር የኢትዮጵያ ባለድርሻዎች” ጉባኤ ከፌብሯሪ 16 እስከ 19 ቀን 2018 እ.ኤ.አ.፤ በሲያትል ዋሽንግተን አዘጋጅቶ ነበር። ትብብሩ ባዘጋጀው በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ በኢትዮጵያ ውስጥና በውጭ አገራት የሚገኙ 26 የፖለቲካ ድርጅቶች (የለውጥ ኃይሎች) በመገኘት ለአራት ተከታታይ ቀናት ጥልቅ የሆነ ውይይት አድርገዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ አቻሜለህ ታምሩ በተለይ የአቶ ጁነዲንና የግራ ፖለቲከኞችን ክስ በማስረጃ ውድቅ አደረጉ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ቪዥን ኢትዮጵያና ኢሳት ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ፤ አቶ አቻሜለህ ታምሩ ”ሽግግሩ ከአንድ የመከራ አዙሪት ወጥተን በአይነቱ ልዩ ወደሆነ ሌላ የመከራ አዙሪት የምንዘፍቅበት? ወይንስ ከታሪካዊ ችግሮቻችን የምንገላገልበት?” በሚል ርዕስ ላይ ያቀረቡትን ጥናታዊ ጽሑፍ ይህ ቪዲዮ ያሳያል።

አቶ አቻሜለህ በተለይ አቶ ጁነዲን ሳዶን አስመልክተው፤ በተለይም በደርግና በኃይሥላሴ ዘመን የነበሩትን የት/ቤቶች ቁጥርና የህዝብ ቁጥርን በተመለከተ በመረጃ በማስደገፍ፤ ”ኦሮሞው እንዳይማር ተደርጓል፣ አማራ ገዥ ነበር፣ ...” የሚባለውን የግራ ርዕዮተ ዓለም ፖለቲከኞችን ክስ ውድቅ ያደረጉበት ጥናታዊ ጽሑፍ ነው።

”ጥላቻና ዘረኝነት ያሰከረው፣ ከብሔሩ ጋር ጮቤ ካልረገጠ የዓለም መጨረሻ የሚመስለው ትውልድ” መጋቢ ቶሎሳ ጉዲሳ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

መጋቢ ቶሎሳ ጉዲሳ በወቅቱ የሀገራችን ጉዳይ ሰፋ ያለ ስብከት ለምዕመናን የሰበኩ ሲሆን፣ በሀገሪቷ ሠላም ይመጣ ዘንድ እስከ ኖቨምበር 12, 2016 እ.ኤ.አ. የሚቆይ ጾም ጠሎት አውጀዋል። በዚህ ወቅት ከኃይማኖት አባቶች የሚጠበቀውንና ብዙዎች ግን ለጉዳዩ ትኩረት ባለመስጠትም ሆነ በፍራቻ በዝምታ የተደበቡበትን የሀገሪቱን ችግርና የህዝብ ብሶት በተመለከተ፤ ዝምታውን ሰብረ ከወጡት የፕሮቴስታንት የኃይማኖት አባቶች ውስጥ መጋቢ ቶሎሳ ጉዲሳ አንዱ ናቸው። ይህን ቪዲዮ ይመለከቱት ዘንድ እንጋብዛለን። በዚህ አጋጣሚ ለመጋቢ ቶሎሳ ጉዲሳ ያለንን አድናቆትና ሀገር ወዳድነት ለማድነቅ እንወዳለን።

የ2008 የዓመቱ ምርጥ ቀልድና ቀልደኛው

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

የኢትዮጵያውያን 2008 ዓ.ም. የዓመቱ ምርጥ ቀልድ ኹኖ ያገኘነው ይህ ቪዲዮ ሲሆን፣ ቀልደኛውም የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ናቸው።

ኢትዮጵያ ዛሬ

የኢትዮጵያውያን ፎረም በአውሮፓ ያካሄደው ህዝባዊ ውይይት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ክፍል ፩

ከዚህ በላይ ያለው ቪዲዮ የኢትዮጵያውያን ፎረም በአውሮፓ፤ በኔዘርላንድ ደን ሐግ ከተማ ጁላይ 29 ቀን 2016 እ.ኤ.አ. ባዘጋጀው ኮንፈረንስ ላይ፤ የተደረገ ህዝባዊ ውይይት ክፍል አንድ ሲሆን፤ ክፍል ሁለቱን ከዚህ በታች ያገኙታል። (ክፍል ሁለቱ የማይታይዮ ከሆነ “ሙሉውን አስነብበኝ ...” የሚለውን ይጫኑ!)

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ