ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ሚያዝያ 5 ቀን 2002 ዓ.ም. ለፓርላማው ሪፖርት አቅርበዋል። በዕለቱ ጠ/ሚንስትሩ ”... ወራዳ ፍጥረት ነው። አሁንም ልድገመው - 'አቶ ልደቱ አዲስ ኃይማኖት አምጥተዋል' ብሎ የቀሰቀሰ የእኛ ሰው ካለ፤ ያ ሰው የእኛ ሰው አይደለም፤ ያ ሰው ወራዳ ሌባ ነውልድገመው ወራዳ ሌባ ነው። ይሄ ከኢህአዲግ ጋር በምንም መልኩ ሊገናኝ የማይችል የወራዶች አመለካከት ነውየኋላቀሮች የአድኀርያን አመለካከት ነውእንዲያ አይነት ቆሻሻ ይዞ ኢህአዲግ ጋር መጠጋት አይገባውም ማንም ሰው ቢሆን። የሻገተ አመለካከት ይዞ ኢህአዲግ ጋር መጠጋት የለበትም። ...” ሲሉ ተደምጠዋል።

በዕለቱ ጠ/ሚንስትሩ ፀያፍ ቃላትን ከመጠቀማቸው በተጨማሪ፤ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የፓርላማ ተወካዮች ጠ/ሚንስትሩ በጥያቄ አፈጥጠዋቸዋል። ጠ/ሚ መለስ ፀያፍ ቃላትን እንዳሻቸው ሲጠቀሙ፤ ሥርዓት ባለው መንገድ የሚናገሩትን ተቃዋሚዎች ግን አፈጉባዔው እንዳይናገሩ ሲያግዷቸው ይህ ቪዲዮ ያሳያል። ለአንባብያን ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ የ6 ደቂቃ ከ26 ሰከንዱን ቪዲዮ ይመለከቱ ዘንድ እንጋብዛለን።

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!