ይህ አጭር ፊልም “Democracy is fair play” በሚል ርዕስ በያሬድ ሹመቴ የተዘጋጀ ነው። ዲሞክራሲን አስመልክቶ በዓለም በሚደረገው የአጭር ፊልሞች ውድድር ላይ ፊልሙ ቀርቦ ከፍተኛ ድምፅ ካገኙት 18 ፊልሞች ውስጥ አንዱ ለመሆን በቅቷል። ከ18ቱ ፊልሞች አሸናፊውን ለመለየት በዩቲዩብ እርስዎም ድምፅዎን መስጠት ይችላሉ። የሚከተለውን አስፈንጣሪ በመንካት (http://www.youtube.com/democracychallenge) ቀጥታ ወደ ድምፅ መስጫው መሄድ ይችላሉ። ከዚያም “VOTE” የሚለውን ይጫናሉ፣ በቀኝ በኩል ከሚመጡት ዘጠኝ ፊልሞች ውስጥ ኢትዮጵያውያን ህፃናት ያሉበትን ካላገኙት፣ በቀኝ በኩል ያለውን ቀስት ሲነኩት ቀሪዎቹን ዘጠኝ ፊልሞች ያገኛሉ። ፊልሙን ሲያገኙ አንድ ጊዜ ይጫኑት፣ ከዚያም ከፊልሙ በታች ያለውን አረንጓዴ እጅ በመጫን ድምፅዎትን ይስጡ! … በዚህ ድምፅ አሰጣጥ ድምፅዎ በትክክል ለመረጡት ይደርሳል። ድምፄ ይሰረቃል ብለው አይስጉ! የኢትዮጵያው ምርጫ ቦርድ እዚህ እጁ አይደርስም። ወደ ድምፅ መስጫ ጣቢያው ውሰደኝ!

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!