ሁሉን አቀፍ አገራዊ የመግባባት ኮሚቴ በሲያትል

ሁሉን አቀፍ አገራዊ የመግባባት ኮሚቴ በሲያትል

23 የተለያዩ የማኅበረሰባዊ ድርጅቶችን (ሲቪክ ማኅበራትን) ያካተተው ”ትብብር የኢትዮጵያ ባለድርሻዎች” ጉባኤ ከፌብሯሪ 16 እስከ 19 ቀን 2018 እ.ኤ.አ.፤ በሲያትል ዋሽንግተን አዘጋጅቶ ነበር። ትብብሩ ባዘጋጀው በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ በኢትዮጵያ ውስጥና በውጭ አገራት የሚገኙ 26 የፖለቲካ ድርጅቶች (የለውጥ ኃይሎች) በመገኘት ለአራት ተከታታይ ቀናት ጥልቅ የሆነ ውይይት አድርገዋል።

ጉባኤው የኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ አገራዊ የመግባባት ኮሚቴ ያቋቋመ ሲሆን፤ ኮሚቴውን የሚመሩ 11 አባላቶችን መርጧል። በሲያትል በተደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ባለዘጠኝ ነጥብ የውሳኔ ሃሳቦችን ያካተተውን መግለጫ ይፋ በማድረግና ለኢትዮጵያ ሕዝብ አገራዊ ጥሪ በማስተላለፍ ተጠናቋል። የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ በፒዲኤፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!

የትብብሩን መግቢያ ንግግርና የኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ አገራዊ የመግባባት ኮሚቴን ሙሉ መግለጫ ለማድመጥ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ