|
እያንጓለለ (የምርጫ ጭውውት)
ዳግማዊ ዳዊት
This e-mail address is being protected from spambots, you need JavaScript enabled to view it
እያንጓለለ … ያ ገብስማ ዶሮ - ዘንድሮስ ምን አለ?
ሊቀ መኳስ ቆመ - አራት ኪሎ ላይ ትናንት መለስ መለስ … ዛሬም መለስ መለስ … ነገም መለስ መለስ - መለስ መለስ ባይ። ሀገር አሳደጉ ሠላም አወረዱ ይህን አድርገዋል - ስሙ ያልሰማችሁ ተገቢ ነውና - በሙሉ ድምፃችሁ ለዘንድሮው ምርጫ - እነርሱን ባትመርጡ ትዝብት ነው እንጅ - ምንም አታመጡ።
ኩኩሉ አለ ዶሮ የምን ምርጫ ነው ዘንድሮ ውጤቱን ያወቅነው ገና ዱሮ መለስ ሊመረጥ ዞሮ ዞሮ እያንጓለለ … ያ ገብስማ ዶሮ - ዘንድሮስ ምን አለ? መሪው ሊቀ መኳስ - አጭር ሰው መላጣ “ላሌ ላሌ” እያለ - ይኸውና መጣ። “ቂ ... ቂ … ልደቱ ልደቱ - እያሉ ሲያለቅሱ እነኃይሉም መጡ - ከእኔ ሊቋደሱ”
ኩኩሉ አለ ዶሮ ማን ነው የሚገደል ዘንድሮ ማን ነው አስገዳይ ዘንድሮ እያንጓለለ … ያ ገብስማ ዶሮ - ዘንድሮስ ምን አለ? ያዝ ልደቱ … አውቄ ነው እንጅ ድሮም ስግደረደር እኔስ ለአድዋው ሰው - አሽከር ሆኘ ልደር እንደምን ነው ስሜን - ወገብ ለወገቡ እንደምን ነው ትግራይ - ወገብ ለወገቡ የእነአዜብዬ ሀገር - የእነአይጠገቡ አላማጣ ውዬ - መልሸ አላማጣ ሽህ ሰው ይተላለቅ - እናንተን ከማጣ እኔስ በመለስ ላይ - ክፉም አላመጣ።
ኩኩሉ አለ ዶሮ ምን ተደግሶልናል ዘንድሮ እያንጓለለ … ያ ገብስማ ዶሮ - ዘንድሮስ ምን አለ? ያዝ መለስ … ብለነው ብለነው - የተውነውን ነገር
አምና ኃይሉ ሰምቶ - ታንቆ ሊሞት ነበር ዘንድሮ መምጣቱ - መስማማቱ ላይቀር ልደቱን መውቀሱ - ተገቢም አልነበር። ሀገራችን ትግራይ - ወንዛችን ተከዜ ማነው እምቢ የሚል - ምርጫ ባልን ጊዜ።
እያንጓለለ … ያ ገብስማ ዶሮ - ዘንድሮስ ምን አለ? ኩኩሉ አለ ዶሮ ኃይሉስ ምን አለ ዘንድሮ በእስር በእንግልቴ - ሁሉ እማስብሽ እኔም ልመጣ ነው ፓርላማ እንዴት ነሽ? ኤልያስ የሚሉት - የሻዕቢያ ምላስ መለስ ጠላት ብሎ - ህዝብን ሲቀሰቅስ እኔም ወንድነቴ - ነሸጥ አድርጎኝ ፓርላማ መግባቴ - ውርደት ነው አልኩኝ ያ ክፉ ባለጌ - አሳሳተኝና ባለፈው ባልመጣ - ባላይሽ ታችሃምና ዘንድሮ ቁርጥ ነው - እንገናኛለን እንዲህ ተለያይተን - መች እንቀራለን መልክ ሰጠኝ እንጅ - ሲሉ እሰማ ነበር ሙያ ከልደቱ - ይኸው ጀመርኩ መማር። እኔም ላሞግሰው - ልነሳ አደግድጌ የአድዋው ሰውዬ - ባይሆን አብሮ አደጌ አክብሮ ጥሪዬን - እጀን ሲጨብጠኝ ከእራሴ ጀምሮ - ወገቤን ነዘረኝ። ደጋፊ አስፈልጎኝ - በጋሪ ስገፋ መለስን ስጨብጥ - በሽታዬ ጠፋ። ይኸው መፎከሬ - “መለስ ይውረድ” ቀርቶ ሠላም ሠላም ሆኗል - የዘንድሮው ሞቶ። እኔ ፍራሽ ሆኘ - ልደቱ ትራስ እንጠብቃለን - አልጋህ እንዳይፈርስ።
እያንጓለለ … ያ ገብስማ ዶሮ - ዘንድሮስ ምን አለ? ኩኩሉ አለ ዶሮ በየነስ ምን አለ ዘንድሮ ዓመት አስር ዓመት - የደነስኩብሽ አንች ዉቧ ቆንጆ - ፓርላማ እንዴት ነሽ ህዝቡ ቢቃወመኝ - አትግባ ቢለኝም እመኝኝ ፓርላማ - ከአንች አልለያይም። ዘጠና ሰባትን - ጠፍቶ እሚገድብ ቅንጅት ተፈጥሮ - ወጣና ከህዝብ ለጥቂት ተረፍኩኝ - ዱላ ከሚመዝ ዳግመኛ እንዳይመጣ - ያን መሳይ መዘዝ። ወያኔ ስትዳር - ጎጆ ስትቀልስ ያን ጊዜ ጀምሮ - እስካሁን ድረስ ታማኝ ተቃዋሚ - ሆኘ ለመለስ መልካም ተብሎ ለእኔ - ህዝብም ተዘናግቶ ያልፈኛል ሁልጊዜ - እንዳላዬኝ አይቶ።
ኩኩሉ አለ ዶሮ ምን መዓት ይመጣል ዘንድሮ እያንጓለለ … ያ ገብስማ ዶሮ - ዘንድሮስ ምን አለ? ያዝ ኃይሉ … አድዋ ላይ ሆኖ - መለስ ቢደነፋ ብርሃኑ ነጋ - ሀገር ጥሎ ጠፋ ድሮም በእጀ - ያልኩት መስፍንን አምኘ ያኔ እርሱን ማመኔም - ፍፁም የዋህ ሆኘ “በብልቃጥ ተረግዞ - መስታወት ተወልዶ” ድርጅት መባሉም - ወይ ነዶ ወይ ነዶ እንግዲህስ በቃኝ - መስፍን የለ ሌላ ጠቃሚ ላይሆኑ - የኋላ የኋላ ፓርላማው ሰፊ ነው - ቧ ያለው መንገዱ ሥነ ምግባር ብቻ መፈረም ነው ኮዱ። ቀብቸ አሽሞንሙኘ - ከላይ ባረግሽ አምባገነን ብለሽ - ስሜን አጠፋሽ በገዛ ምላሷ - በገዛ አንደበቷ ቃሊቲ ገብታለች - ከዘላለም ቤቷ አትሳቂ እያልኳት - ባህር ማዶ ስቃ አመጣችው እስሩን - ነቅንቃ ነቅንቃ።
ኩኩሉ አለ ዶሮ በችግር ላይ ችግር ሆኖ የእኛ ኑሮ እያንጓለለ … ያ ገብስማ ዶሮ - ዘንድሮስ ምን አለ? ያዝ ብርሃኑ … ስሙልኝ ይኸን ሰው - እዩት ስም ሲያጠፋ ምርጫ ውሸት ነው ብል - አለኝ ጥሎ ጠፋ እኔስ ያከበርኩህ - በሽምግልናህ ነው አመራር ሲመጣ- ጉድክን ሳስተውለው አምባገነንነት - ፍፁም መለያህ ነው እነ መለስ ዜና - ሰይጣን መርቋቸው ተቃዋሚ ጀባ - ብለው በጫታቸው አንገዋለለና - ልደቱን ሰጣቸው አንገዋለለና - በየነን ሰጣቸው አንተን በምራቂ - ይኸው ጨመራቸው
እያንጓለለ … ያ ገብስማ ዶሮ - ዘንድሮስ ምን አለ? ያዥ ብርቱካን … ዓለም ዓለም … ዓለም ዓለምዬ እሽሩሩ ስቃይ - ውረድ ከጀርባዬ ደብተራው የማነ - አረጋሽ እህቴ አብረው የሚኖሩ - ቤታቸው ከቤቴ የእግዜር ፈቃድ ሆኖ - ቢሰማ ፀሎቴ ለፍች ያብቃችሁ - ከዓላማችሁ ግብ አምላክ ያውርድና - የሠላም ድባብ። ዛሬ በመልዓኩ - በገብርኤል በበዓሉ ወዲ መለስ ዜና - መሸረብ ጀመረ አሉ ኃይሉ መላጣ ላይ - ሽሩባ ጎንጉኖ “እኔን እኔን ሥራኝ” ይላል ልደት አብሮ ፀጉር እንዲህ ይሠራል - ከክዳን ጀምሮ። ተወኝ አላልኩም ወይ - ይህን ዓመልህን ልክ እንደልደቱ - አንተም መክዳትህን ልደቱስ ቢያንስ እንኳን - ይሂድ ይመለሳል ምርጫ መጣ ሲሉት - መለስን ይወቅሳል።
እያንጓለለ … ያ ገብስማ ዶሮ - ዘንድሮስ ምን አለ? * * * * * * * * * ኩኩሉ አለ ዶሮ አራት ኪሎ አስመራን ምን ይላል ዘንድሮ ያዝ መለስ … ከሰማዩ በላይ - ያለኸው ሰማይ ወዲ አፎም በጤናው - ዘግቶኝ ቀረ ወይ ደግሞ በዚህ ምርጫ ያደናቅፍ ወይ? የቀይ ዳማ ረጅም - ጎራዴ ታጣቂ ልግደልህ እያለኝ - እኔ እርሱን ናፋቂ
እያንጓለለ … ያ ገብስማ ዶሮ - ዘንድሮስ ምን አለ? ኩኩሉ አለ ዶሮ ኢሳያስ ምን ይላል ዘንድሮ ልቤ አብጦ ጀግኘ - አንበሳ ነኝ ስል ጦር አዘመትክና - አደረከኝ ድል አስራ ሁለት ሌሊት - አስራ ሁለት ቀን ከትግራይ ተነስትህ - ልትይዝ አስመራን ጉዴ ፈልቶ ነበር - ክሊንተን ባይኖር ያስጎራሃል አሉ - በየአምስት ዓመት ደም የለመደ እጅህ - ሲሻ መስዋዕት ሲሉ ሰምታ ሆኖ - ሆነና ነገሩ ምዕራብ ያለው ሁሉ - ይመስልሃል ጥሩ። ምርጫ ምርጫ - ብለህ ብትፈጥር ግርግር እኔ ጌታህ ሆኘ - ካልሆንከኝ አሽከር ውጊያ መቀስቀሱ - ምንጊዜም አይቀር።
እያንጓለለ … ያ ገብስማ ዶሮ - ዘንድሮስ ምን አለ? ያዝ መለስ ... ጠያቂው ቢያስጨንቀኝ - ስለኤርትራ ሁኔታ አልወዳትም አልኳቸው - እንዲያገኙ ፋታ። ቁርጡማ ሲመጣ - አስመራ ልትያዝ የኔ ተግባር ነበር - እነስየን ማዘዝ አልጀርስ ሳገኝህ - ውል ልትፈራርም አልነበረምና - እኔ ያልኩኝ ጥምጥም ይናፍቃል ለካስ - እንደዚያ ወንድም።
እያንጓለለ … ያ ገብስማ ዶሮ - ዘንድሮስ ምን አለ? ያዝ ስዬ … ተወኝ አላልኩም ወይ - ይህን አመልህን ጫት እንዳዬ ጀዝባ - አስመራን መዞርክን ጫትን ያዬ ቃሚስ - ቅሞ ይመለሳል የአንተ ሁኔታ ግን - ግራ ነው እሚያጋባን።
እያንጓለለ … ያ ገብስማ ዶሮ - ዘንድሮስ ምን አለ? ኩኩሉ አለ ዶሮ ህዝባችን ምን አለ ዘንድሮ የሚመጣው ምርጫ - ምኞታችሁ መክኖ የፍትህ አካላት - ፕሬስ ነፃ ሆኖ ገለልተኛ ሆኖ - መከላከያችን ገለልተኛ ሆኖ - የምርጫ ቦርዳችን በነፃ እንዲሰማ - እንደ ህዝብ ድምፃችን በዘር በኃይማኖት - መጋጨት ትታችሁ ኤርትራና ትግራይ - አማራ ኦሮሞ ማለቱን ትታችሁ አብዮት - አብዮት ማለት አቁማችሁ ሁላችንን በእኩል - ሕጉ እንዲመዝነን የሥልጣኑ ምንጮች - እኛ ህዝቡ እንሁን።
ዳግማዊ ዳዊት
This e-mail address is being protected from spambots, you need JavaScript enabled to view it
ጥር 2002 ዓ.ም. |