|
ሿ ሿ ... ዳግም ምርጫ (የምርጫ ጭውውት ክፍል ሁለት) ዳግማዊ ዳዊት
This e-mail address is being protected from spambots, you need JavaScript enabled to view it
ደሞ ምርጫ! ሿ ሿ ዳግም ምርጫ! አንዋጋም ብለን … ካልን ሠላም ብቻ እርስ በእርስ መናቆር … ሳናቆም ጥላቻ ውስጣችን ሳይጠራ … አንቅረብ ለምርጫ! እስኪ ሠላም ይውረድ! … እስኪ ውስኪ እንራጭ! … ካልቻልን አረንቻታ
ውስኪው ሠላም ይሁን- ፍቅር አረንቻታ!
ምርጫ ቦርዱ ቢለኝ … አልኩት አላውቀውም ፍርድ ቤቱስ ሲለኝ … አልኩት አላምነውም ሰብዓዊ-መብት ሲል … አልኩት አልታደልንም መከላከያ ሲል … ነገርኩት እንዲል ዝም ተቃዋሚወችስ ሲል … አልኩት አሳመሙኝ እየተጣሉ አልኩት … ለምን ብሎ ቢለኝ ፌደራል ሲጠይቅ … ለሞቴ ፈራሁኝ ታድያ ዝግጅቱስ? ... አልኩት ምንም የለም ማሸንፉስ ሲለኝ - እሱ አይታሰብም ታድያ ትርፉስ ሲለኝ - አልኩት አላውቀውም።
ፏ! ፏ! ብሏል መለስ- ፏ! አለ እንጅ በሸገር መተባበር ጠፍቶ … መቻቻሉ ጠፍቶ አገር ትቅደምቀርቶ ቀና ማሰብ ቀርቶ … ደግ መስራት ለአገር ህዝብ ማዳን ቀርቶ … ዘራፍ ማለት ለአገር! ጠላት ቢደነፋም - ቢበዛ እንቅፋቱ አይከፋንም ነበር - ለህዝብ መሞቱ እናንት ሳትስማሙ - ገብታችሁ ለምርጫ አይፈስም አልልም - የደም አረንቻታ።
ደሞ ምርጫ! ሿ ሿ ዳግም ምርጫ! አንዋጋም ብለን … ካልን ሠላም ብቻ እርስ በእርስ መናቆር … ሳናቆም ጥላቻ ውስጣችን ሳይጠራ … አንቅረብ ለምርጫ! እስኪ ሰላም ይውረድ! … እስኪ ውስኪ እንራጭ! … ካልቻልን አረንቻታ
ውስኪው ሰላም ይሁን - ፍቅር አረንቻታ!
እናንት ልብ ብትሉ - ግለኝነት ቀርቶ አገር ማዳን ቢሆን - የዘንድሮው “ሞቶ” ሕዝብ ማዳን ቢሆን - የዘንድሮው ጥረት ለፍትህ ተታግልን - ለፍትህ ብንሞት እንኳን አንድ መለስ - በህዝብ የተተፋ - የጋጠ-ወጥ አውራ ገፍተን ባስወገድን - ግዙፉን ተራራ ጣጥሰነው ገብተን … ድሉን ተቀናጅተን … በህዝብ ለህዝብ የቆመ - መሪያችንን መርጠን ሠላም ብልፅግናን - ገንዝብ ባደረግን።
ደሞ ምርጫ! ሿ ሿ ዳግም ምርጫ! አንዋጋም ብለን … ካልን ሰላም ብቻ እርስ በእርስ መናቆር … ሳናቆም ጥላቻ ውስጣችን ሳይጠራ … አንቅረብ ለምርጫ! እስኪ ሰላም ይውረድ! … እስኪ ውስኪ እንራጭ!… ካልቻልን አረንቻታ
ውስኪው ሠላም ይሁን - ፍቅር አሪንቻታ!
ዳግማዊ ዳዊት የካቲት 2002 ዓ.ም.
This e-mail address is being protected from spambots, you need JavaScript enabled to view it
|