Home ኪነ-ጥበብ ግጥም የድል ጎህ ቀደደ (ከአብርሃም ሰሎሞን)
የድል ጎህ ቀደደ (ከአብርሃም ሰሎሞን) Print E-mail
User Rating: / 2
PoorBest 
Art
Sunday, 17 August 2008 20:40

የድል ጎህ ቀደደ

አብርሃም ሰሎሞን (ሚኒሶታ አሜሪካ This e-mail address is being protected from spambots, you need JavaScript enabled to view it ) 

የድል ጎህ ቀደደ ድል ማድረግ ጀመረን፡

ገና በጠዋቱ በአዲስ ክብረ ወሰን።

ጥሩነሽ ዲባባ ኢትዮጵያን ወክላ፡

ፊት ቀድማ ገብታለች ዓለም አስከትላ።

 

Tirunesh Dibaba, Beijing Olympic 2008, August 15, 10000m goldበቤጂንግ ኦሎምፒክ ዓለም ሲወዳዳር፡

ጥሩነሽ ዲባባ ከሴት አጣች ወደር።

አመለጠቻቸው አንድ ዙር ሲቀራት፡

ኢትዮጵያ ስትቀድም ዓለም ተከተላት።

በአዲስ ክብረ ወሰን በድል ስትገባ፡

ክብርት የኢትዮጵያ ልጅ ጥሩነሽ ዲባባ፡

እጅግ ደስ ብሎናል ከደስታ በላይ፡

የኢትዮጵያ ባንዲራ ከፍ ብሎ ስናይ።

 

ቃላት ጠፋ ለአንቺ ማመስገኛ አንደበት፡

በክብር ስናይሽ ቆመሽ በሰገነት፡

ቃልሽ አልታጠፈም በቃልሽ ተገኘሽ፡

እንደ ሰማን አየን ድልሽን ጥሩነሽ።

ትዝታ መልሶ ከሜዳው ወሰደን፡

እግር አጣጣልሽ ለአዲስ ክብረ ወሰን።

ስትሮጪ እንዳልነበር ሃያ ዐራት ዙር አብረሽ፡

ሰዓትሽ ደረሰ ያን ጊዜ ተለየሽ።

የመጨረሻው ዙር ደወሉ ሲደወል፡

ያኔ አንቺ ቀድመሻል ሕዝበ አዳም ሲከተል።

 

ጥሩነሽ ዲባባ ኦሎምፒክ ለድልሽ፡

ያዘጋጀችውን ሽልማት ሰጠችሽ።

የወርቁን ሜዳሊያ የዓለም ሕዝብ እያየሽ፡

በእጅሽ አድርገሻል ጀግናዋ ጥሩነሽ።

ወርቅ ያንስሻል ብላ ኢትዮጵያ ለድልሽ፡

የክብር ካባ ነው የደረበችልሽ።

በዓለም የተሰማው የዛሬው ድል ብስራት፡

አሜን! መንገድ ጠርጓል ለነገው ሽልማት።

በድካምሽ ዋጋ በላብሽ ውጤት ነው፡

አዲስ ክብረ ወሰን የተመዘገበው።

 

ክብርት ጥሩነሽ ከብረሽ አስከበርሽን፡

ድል በየአራት ዓመት ዛሬም አሳየሽን።

የድል ጎህ ቀደደ "ሀ" ብለሽ ጀመርሽው፡

የኢትዮጵያን ባንዲራ ዛሬም ከፍ አስባልሽው።

 

ዕልል በይ ደራርቱ በእግርሽ ሰው ተተካ፡

አሳልፎ የማይሰጥ ወርቅ የማያስነካ።

ድል በባርሲሎና ድል በሲድኒ እንዳይቀር፡

ኢትዮጵያ በቤይጂንግ ሁሌ እንድትዘከር፡

በሚያስደንቅ ፍጥነት በአዲስ ክብረ ወሰን፡

ድል አድርጋ ጥሩነሽ አኩርታለች ወገን።


 

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

አብርሃም ሰሎሞን ሚኒሶታ አሜሪካ

This e-mail address is being protected from spambots, you need JavaScript enabled to view it  

 

 
 

በጽሑፍ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ!

በማናቸውም ጉዳይ ላይ ያለዎትን ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ትችት፣ ግጥም፣ ልብወለድ፣ … በማይክሮሶፍት ወርድ ፕሮግራም በዩኒኮድ ፎንት ጽፈው ከራስዎ ኢ-ሜይል ሳጥን ጽሑፎትን አያይዘው በኢ-ሜይል አድራሻችን 

ethiopiazare@gmail.com ቢልኩልን ለሥራችን ቅልጥፍና ይረዱናል።

ኢትዮጵያ ዛሬ