|
ምናለበት?! (ለአምባገነኖችና ለግብረ-አበሮቻቸው) ከጌታቸው አበራ (
This e-mail address is being protected from spambots, you need JavaScript enabled to view it
)
የህዝብ ራዕይ ባታመክኑ፣ ያገር ተስፋ ባታተኑ፣ ያያችሁትን ፍጡር ሁላ - እንደ እብድ ውሻ ባትለክፉ፣ የትውልድን ውብ አበባ - በጭካኔ ባትቀጥፉ፣ ያድባር ቆሌ ባትገፉ፣ የጡር እንባ ባታተርፉ፣ ጣፋጭ ሲሳይ ማር ወለላ - በሬት መራር ባትለውሱ፣ ምናለበትኢ?! ቀኑ አክትሞ - ከመንበሩ ብትነሱ፣
በሥልጣን ጥም ባትሰክሩ፣ ካይጥ ጉድጓድ - የቆቅ ኑሮ ባትኖሩ፣ መውጫ መግቢያው ባይጠባችሁ - ጥላችሁን ባትፈሩ፣ እኩይ ድርጊት ተደራርቦ - ሰው ፊት መቅረብ ባታፍሩ፣ አራጅ፣ ውራጅ ... አምባገነን - የሰቆቃ የጭካኔ ...፣ የዲያቢሎስ ቁራጭ ቁንጮ - ሠይጣን፣ አውሬ፣ አረመኔ፣ ... ተብላችሁ ተንቃችሁ - የውርደት ሥም ባትለብሱ፣ ምናለበት! ለክብራችሁ - ላገር ክብር ብትሳሱ!! ልጆቻችሁ ያልታደሉት፣ ፍርሃት ታቅፈው የሚኖሩት፣ አንገት መድፋት፣ መሸማቀቅ - ሽብር፣ ሥጋት፣ ... ሳይገባቸው፣ ባደባባይ ቢራመዱ - ልበ-ሙሉ ኩሩ ሆነው ... ፣ ህዝበብ ሲራብ፣ ሀገር ሲወድም - ጥሪ ማሸሻ በያለበት፣ ላትበሉት ለዝንተ-ዓለም - ላትኖሩ ምዕተ-ዓመት፣ መኖር ከቶ እንዲያኮራ - በንጽኅና በነፃነት፣ ከማንዴላ፣ ከኦባማ፣ ... - ብትማሩ ምናለበት?! የብዙኃን ምክር፣ ቁጣ፣ ... - የህዝብ ድምፅ ባትንቁ፣ ልቦናውን ቢሰጣችሁ - ከእንቅልፋችሁ ብትነቁ፣ ብልጽግና፣ ሠላም፣ ፍቅር፣ ... - ፍትህ፣ ጤና፣ ... እንዲያብቡ፣ ሰብዓዊነት እንዲሰፍኢኢ - እፎይ ብሎ ሊኖር ህዝቡ፣ እንዲከበበር ክቡር ድምፁ - ሳያሰልስ ሲወተውት፣ ሳትተብቱ ብትሰሙ - ቢያምርባችሁ ምናለበት?! አልያ ግን ካልገባችሁ - የህዝብ እንባ ያገር ብሶት፣ አሁን ደርሶ ምናለበት?! - ቢጠርጋችሁ አንድ መዓት!!
ጌታቸው አበራ ኅዳር 2001 ዓ.ም. (ኖቨምበር 2008) |