Home መጣጥፍ አስተያየት የእንቧይ ካቡን ትተን ለወደፊቱ የአለት መሰረት እናብጅ (መርስኤ ኪዲን)
 
የእንቧይ ካቡን ትተን ለወደፊቱ የአለት መሰረት እናብጅ (መርስኤ ኪዲን) Print E-mail
User Rating: / 0
PoorBest 
Articles - Opinion

መርስኤ ኪዲን This e-mail address is being protected from spambots, you need JavaScript enabled to view it

ሰሞኑን የአንድነት ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጂነር ግዛቸው ሺፈራሁ “አንድነት ችግር ላይ ተጋርጧል … ሊዘጋ ይችላል” ሲሉ ዴይሊ ኔሽን ለሚባለው የኬንያ ጋዜጣ መግለጻቸውን ሰንደቅ ጋዜጣ ታህሳስ 28 ቀን 2002 ዓ.ም. ባወጣው ዕትሙ አስፍሯል። የኢትዮጵያን ፖለቲካ በአንክሮ ለሚከታተል ሰው ይህ ዜና ብዙም አስገራሚ አይሆንበትም። ለምን? ቢባል አንድነት መድረክ የተባለውን “የእንቧይ ካብ” የተቀላቀለ ጊዜ እንዳበቃለት ግልጽ ነውና።

 

ይህን ጽሁፍ ለመጻፍ የተነሳሳሁት የአንድነት ፓርቲ ለመፍረስ መቃረብ አሳስቦኝ ሳይሆን፤ በኢትዮጵያዊነት የተሰባሰቡት የአንድነት አባላት በተለይም ወጣቶቹ የተሰባሰቡለት የኢትዮጵያ አንድነት ጉዳይ መድረክ በሚባለው ስብስብ ውስጥ ባለ የጎሣ/የብሔር ፓርቲዎች ተጨናግፎ አንድነት የሚባለው ፓርቲም የአማራው ተወካይ መባሉ ስላልተዋጠልኝና የአንድነት ኃይልች በጎሣ ፖለቲከኞች እየተሸነፉ መሄዳቸው እጅግ ስላሳሰበኝ ነው።

 

የ“አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ” አባላት በአንድነት ዙሪያ የተሰባሰቡት ለምንድነው?

የአንድነት አባላት በፓርቲው የተሰባሰቡት ቅንጅት በማኒፌስቶው ላይ ያሰፈራቸውን እሴቶች ይዘን እንታገላለን በሚል እንደሆነ የሚታወቅ ነው። የቅንጅት ማኒፌስቶ የመጀመሪያ አንቀጽ ቁጥር አምስት “የቅንጅት ልዩ ባህሪያት” የሚለው ክፍል ይህን አስፍሯል …

 

“… ቅንጅት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የተለያየ ልምድ፣ አሠራርና ዝንባሌ ያላቸውን አራት ሕብረ-ብሔር ፓርቲዎች በማስተሳሰር ልዩነቶችን በውይይት፣ በድርድርና በመቻቻል ማስወገድ እንደሚቻል በተጨባጭ ያረጋገጠ የፖለቲካ ድርጅት ነው። …” (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ)

 

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 

በጽሑፍ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ!

በማናቸውም ጉዳይ ላይ ያለዎትን ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ትችት፣ ግጥም፣ ልብወለድ፣ … በማይክሮሶፍት ወርድ ፕሮግራም በዩኒኮድ ፎንት ጽፈው ከራስዎ ኢ-ሜይል ሳጥን ጽሑፎትን አያይዘው በኢ-ሜይል አድራሻችን 

ethiopiazare@gmail.com ቢልኩልን ለሥራችን ቅልጥፍና ይረዱናል።

ኢትዮጵያ ዛሬ