የሁሉም ጠላት ወያኔ ነው!

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ወያኔ የኦሮሞ ጠላት ነው

አንተነህ መርዕድ

Abayi Tsehaye አባይ ፀሐዬ

መለስ ሲያጉረመርምበት ብርክ የሚይዘውና የሚሙለጨለጨው፣ ጓደኞቹን ደጋግሞ በፍርሃቱ የሸጠው አባይ ፀሃዬ ዞር ዞር ብሎ ሲመለከት ከሱ የተሻሉና የሚያስፈሩት ህወሃቶች የሌሉ መሆናቸውን በማረጋገጡ በየመድረኩ ብቅ እያለ መፎከርና መዘባረቅ የእለት ተእለት ሥራው ሆኗል። በተለይም በዋና ባለቤትነት የአዲስ አበባን መሬት ሸጦ ከጨረሰ በኋላ የአካባቢውን ገበሬዎች ከነመሬታቸው ሊቀራመት ያደባበት ተንኮል አልሠራ ሲል “ልክ እናስገባቸዋለን” ሲል ፎከረ። አሁን ደግሞ ፉከራው የለኮሰውን እሳት ማዳፈን ተስኖት “ወያኔ የኦሮሞ ጠላት አይደለም” የሚል የሽሽት ሽምጥ ሩጫ ይዟል። እሳቱ ግን እሱን ሳይለበልበው የሚመለስ አይደለም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ካልተስማማን እንደሀገር እንጠፋለን

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ግርማ ካሳ

በግምት ከሃያ አራት ዓመታት በፊት ይሆናል ቀኑ። በኢትዮጵያ እርቅና ሰላም እንዲኖር ብዙ ጊዜ የሚደክሙና የሚጸልዩ፣ ቄስ ቶሎሳ ጉዲና የሚባሉ አንድ መንፈሳዊ አባት፣ ምዕመናንን ሲያስተምሩ የተናገሩት፣ ሁልጊዜ የማስታወሰውና የማልረሳው አባባል ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ማንነት መሬት ላይ አይዘራም

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ጌታቸው ኃይሌ

Identity crisis ማነኝ?

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ማንነት ዋና የመወያያ ርዕስ ሆኖ ቈይቷል። የሥነ ልቡና ምሁራን identity crisis የሚሉት ነው እንዳልል ያተኰረው "እኔ ማነኝ" ከሚለው ላይ አይደለም። ያተኮረው "ማንነት ከመሬት ጋር ይያያዛል ወይስ አይያያዝም?" ከሚለው ጥያቄ ላይ ነው። ውይይቱን እንዳዳመጥኩትና እንደሰማሁት፣ እኔም አስተያየቴን እንድሰጥ ተጠይቄ እንደተቸሁት፣ ማንነትን ከመሬት ጋር የሚያያይዙ እምነታቸውን ከኃይማኖት እምነት ደረጃ አድርሰውታል። ስለዚህ እነሱን በማስረጃ ማሳመን ሃይማኖታችሁን ለውጡ እንደማለት ሆኗል። "እምነቱ ሀገር አጥፊ ነው፤ ተውት" ቢባሉም፣ ማንነታቸው ከያዙት መሬት ጋር ከተቆራኘ፣ ይህ አደገኛ አቋማቸው ለሚያስከትለው ሀገራዊ ችግር አንዳች ሥጋት አይታይባቸውም። ክልል ይዞ ኢትዮጵያዊ መሆን ይቻላል የሚሉም አይጠፉም። መሳሳታቸውን መስማት አይፈልጉም፤ ግን ማንነት የሚዘራበት መሬት የሚያስፈልገው ዳጉሳ አይደለም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለልጅ የሳቁለት፣ ለውሻ የሮጡለት፣ ለፖለቲከኛ ያጨበጨቡለት

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ይገረም አለሙ

የአበው ተረት ለልጅ የሳቁለት ለውሻ የሮጡለት ነው የሚለው። ለፖለቲከኛ ያጨበጨቡለት የሚል ቢጨመርበት ተስማሚ ይመስለኛል። ልጅ ከሳቁለት ሁሉ ቦታ እየገባ ነገር ያበላሻል፤ ውሻ ከሮጡለት ጥሎ ካላንደባለለ ወይ ካልቦጨቀ አይመለስም ፖለቲከኛም ካጨበጨቡለት አበው ልቤ አደገና ያለ ቁመቴ አላስገባ አለኝ የገዛ ቤቴ እንደሚሉት ይሆንና ከእኔ በላይ ለአሳር በሚል መታበይ ብዙ ጥፋት ያደርሳል ኋላም ራሱን ያዋርዳል። እኛም ጥሎብን ይሁን ባህል ሆኖብን ባይታወቅም እየኮተኮቱ ማሰደግ እየገሩ ለወግ ማዕረግ ከማብቃት ይልቅ እያሞካሹ ማበላሹትን እያጨበጨቡ ወደ ገድል መግፋቱን ተክነንበታል። በዚህ መንገድ ስንት ለሀገርና ለወገን ሊጠቅሙ ይችሉ የነበሩ ሰዎችን አጥተናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመሳይ ከበደ በር

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ተስፋዬ ገብረአብ

ዛሬ ላይ ቆመው ነገን ለማወቅ የሚችሉ ሰዎች “ነቢይ” ሲባሉ ኖረዋል። በዘመናችን ቋንቋ “የፖለቲካ ተንታኝ” ማለት ይሆን? ይህን የሚገልፅ አንድ አባባል አውቃለሁ፣ “ትናንት ታሪክ ሆኖአል፤ ዛሬ ስጦታ ነው፤ ነገ ደግሞ ምስጢር”

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መልስ ለአቶ ብርሃነመስቀል የ”ኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄዎች” ባሉት ላይ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ግርማ ካሳ

አቶ ብርሃነመስቀል አበበ፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ መብት ዙሪያ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ጽሁፎችን ይጽፋሉ። ቢቢሲ በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ስርጭት እንዲኖረው ፔቲሽኖችን በማስፍረም አንድ ዘመቻ እንደነበረ የምናስታወሰው ነው። ይሄንን ዘመቻ ይመሩ ከነበሩት መካከል አቶ ብርሃነመስቀል አንዱ ነበሩ። እኔም ሆንኩም በርካታ ኢትዮጵያዊያን ፔቲሽኑ ላይ ፊርማችንን በማስፈር፣ ፔቲሽኑ ያልፈረሙ እንዲፈረሙ በማበረታታት እንደነ አቶ ብርሃነመስቀል ባይሆንም፣ የድርሻችንን አበርክተናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!