አባይ ለሕዝብ ወይስ አባይ ለኢሕአዴግ?

ግርማ ካሳ
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ጨምሮ በርካታ የኢሕአዴግ ባለስልጣናት፣ በተለያዩ የአሜሪካና የአውሮፓ ከተሞች በመዘዋወር፣ ለአባይ ግንባታ ገንዘብ ለማሰባሰብ ሞክረዋል። ነገር ግን በበርካታ ከተሞች፣ ከዚህ በፊት ከነበረው በተለየ ሁኔታ፣ ጠንካራ ተቃውሞ የደረሰባቸው ሲሆን፣ አንዳንድ ከተሞችም፣ ተቃዋሚዎች ስብሰባውን ሙሉ ለሙሉ እስከመቆጣጠር የደረሱበት ሁኔታም እንደነበረም ታዝበናል።
"መሪ አጣን" እያሉ ማላዘን ይቁም!
መሪነት እና የመሪነት ወለፈንዲዎች
ታደሰ ብሩ
መግቢያ
ማኅበራዊ ለውጥንና እድገትን የሚመለከቱ ዓላማዎች በአንድ ወይም በጥቂት ሰዎች ጥረት የሚሳኩ አይደሉም። እነዚህ ትላልቅ ዓላማዎች እንዲሳኩ የብዙ ሰዎች የተባበረ ጥረት ያስፈልጋል። በርካታ ሰዎችን ለእንዲህ ዓይነቶቹ ግዙፍ ዓላማዎች ማነሳሳትና እና ማስተባበር ነው መሪነት (Leadership) የሚባለው።
ከፋውንዴሽኑ ጀርባ ...
ተመስገን ደሳለኝ
(ክፍል ፩)
ያለ ወቅቱ በደረሰ ዝናብ እየራሰች ያለችው አዲስ አበባ ዛሬም ከመለስ መንፈስ ተፅእኖ ነፃ አልወጣችም፤ ጣራና ግድግዳዎቿ እንዲህ በምስሉ እና በድርጅቱ አርማ መዥጎርጎሯን ያስተዋለ አንድ ቀልደኛ የባህር ማዶ ወዳጄ "እኔ ከሀገሬ ከወጣሁ በኋላ የኢህአዴግ ዋና ከተማ ሆነች እንዴ?" ብሎ ፈገግ አሰኝቶኛል። በእርግጥ ይህችን ቀልድ ስንፍቃት የምናገኘው ቁም ነገር፦ ከተማዋ በመለስ ውርስ ድንዛዜ ላይ መሆኗ፣ ...
"እያንዳንዱ ዜጋ ከራሱ ጋር ይነጋገር" አርቲስት ታማኝ በየነ
ታምሩ ገዳ
በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው አስከፊ የሰብአዊ መብት ረገጣ ይቆም ዘንድ እያንዳንዱ ዜጋ የበኩሉን አሰተዋጽኦ ሊያበረክት እንደሚገባው እና ከራሱ ጋር መነጋገር እንዳለበት ተገለጸ።
የዘረፋ ውሎ በእንዳማርያም
(ገብረመድህን አርአያ)
ስብሃት ነጋ ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ በሚታተመው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የሰጠውን ቃለ መጠይቅ አነበብኩት። ስብሃት ነጋ “ኢህዴግን የመሰለ ፓርቲ በአፍሪካ የለም” እና ሌላም ብዙ፣ ብዙ ይላል:: ይዘብታል፣ ይፎክራል፣ ይሸመጥጣል፣ ያቀረሻል፣ በህዝብ ሞራል ላይም ያላግጣል። ብዙም አልደነቀኝም። ስብሃትም ሆኑ የዚህ ፋሺስታዊ ስርዓት አንቀሳቃሾች በብዙሃን ደም ላለፉት አርባ አመታት ታጥበዋል፣ ታሪክ አውድመዋል፣ እጅግ ከፍተኛ ዘረፋ ፈጽመዋል፣ አገር ቆርሰው ሸጠዋል።
ግጭቱን ማን ለኮሰው?
እየሩሳሌም አርኣያ
ቀኑ ማክሰኞ፣ ጥቅምት 22 1998 ዓ.ም፤ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ገደማ... አንድ የከተማ አንበሳ አውቶብስ ተሳፋሪ ሳይጭን ከመርካቶ ተነስቶ ወደ ጎማ ቁጠባ አቅጣጫ በባዶ እየከነፈ ቁልቁል ወርዶ ... ተ/ሃይማኖት ቤ/ክርስቲያን አደባባይን ከዞረ በኋላ ጥግ ይዞ ቆመ። ሹፌሩ አውቶብሱን ገትሮ ወዲያው ከአካባቢው ጠፋ። ለሁለት ሰዓት ገደማ አውቶብሱ እንደተገሸረ ቆየ። ...
99 ቀናት በአዲስ አበባ
ጋዜጠኛው ኤን. ማንጄላ (N. Mandela) በኢትዮጵያ
ሰሎሞን ተሰማ ጂ.
በታኅሣሥ አጋማሽ 1954 ዓ.ም በግርማዊ ንጉሠ ነገሥቱ ጥሪ ተደረገለትና በጥር መጀመሪያ ላይ አዲስ አበባ ገባ። ይህ ሰው በሦስት ወራት ከአንድ ሳምንት (በ98 ቀናት) ቆይታው ወቅት እጅግ የተጣበበ መርሐ ግብር እንደነበረበት ያስታውቃል።
በሲያትል ለኢሳት 50ሺህ ዶላር ተሰበሰበ
የጋዜጠኞቹ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት አለሙና ውብሸት ታዬ ምስል 33ሺህ ዶላር በጨረታ ተወስዷል
Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዚያ 14ቀን 2005 ዓ.ም. April 22, 2013)፦ ትላንት ምሽት በሲያትል ከተማ የኢሳትን ሶስተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ አርቲስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው ታማኝ በየነ እና አቶ መንሱር ኑር በክብር እንግድነት የተገኙበት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ምሽት ላይ 50ሺህ የአሜሪካን ዶላር መሰብሰቡ ታወቀ።
ደሳለኝ ደበረኝ ደሳለኝ
አባጅፋር
ፊት ላይ ያሉት ቀዳዶች የተበጁት ለመተንፍሰ፣ ለመብላት፣ ለመናገርና ለመናፈጥ ነው። እንዳስፈላጊነታቸው እንጠቀመባቸዋለን። በዚህም ምክንያት ሰውየው ተናገሩ።
የግፍ ጽዋ ሲበዛ አያቀረሽም እንዴ?
ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)
ዋናው የኢትዮጵያ ህዝብ ችግርና መፍትሄ ያልተገኘለት ነገር፤ የህውሀት ገዢ ቡድን፤ አሁን አለማችን ካለችበት የስልጣኔና የአስተሳሰብ እድገት ደረጃ እጅግ ወደ ኋላ በቀረ እምነትና ፍልስፍና ላይ ተጣብቀው በመቅረታቸው፤ የሁሉ ነገር መፍትሄ ጉልበት ብቻ ነው፤ ጡንቻ ብቻ፤ ጡንቻን አፈርጥሞ መገኘት ብቻ ነው።
