እናንት የዋሆች ከኤርትራ የኢትዮጵያን ነፃነት እንዴት ትሻላችሁ? (ከሙሉነህ ዮሐንስ)
ሙሉነህ ዮሐንስ ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )
ምላሽ “በኤርትራ በቀር ወደ ኢትዮጵያ ነፃነት የሚወስድ መንገድ የለም” በሚል አባኪያና ጓደኞቹ ለጻፉት
በመጀመሪያ ጓደኛየ አባኪያ ሠላም ላንተና ለጓደኞችህ ይሁን! ሰሞኑን ኢትዮጵያ ዛሬ (www.ethiopiazare.com) ድረ-ገጽ ላይ ያወጣችሁትን ጽሑፍ በግርምትና በአንክሮ ደጋግሜ አነበብኩት። ይህን እንደሳማ የሚቆጠቁጥ አርዕስት ደፍራችሁ ለውይይት ስላቀረባችሁት እያመሰገንኩ፤ አስተሳሰባችሁ ግን አስደንግጦኛል፤ አጥብቄም እቃወመዋለሁ። ኢትዮጵያውያን ወገኖች የኤርትራን ጉዳይ በዚህ መልኩ ያዩታል የሚል ግምት አልነበረኝም። አስተያየቴን በግል ልሰጣችሁ አስቤ ነበር። የጉዳዩን አደባባይ መውጣትና ለኢትዮጵያችን ሊኖረው የሚችለውን አደገኝነት ሳስበው እንዲሁም የውይይት ግብዣችሁን ሳክልበት በይፋ ምልከታየን ማድረስ መረጥኩ።
ግንቦት 7 ለእንቁጣጣሽ ወደ ኢትዮጵያ የሚያሰራጨውን ራዲዮ ይጀምራል
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ነኀሴ 27 ቀን 2000 ዓ.ም. September 02, 2008)፦ በቅርቡ የተቋቋመው ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ የሚቀጥለው ሣምንት ኀሙስ መስከረም 1 ቀን 2001 ዓ.ም. (September 11, 2008) በአዲስ አበባ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት (8 P.M. / 20:00) ላይ ስርጭቱን በአማርኛ ቋንቋ እንደሚጀምር የንቅናቄው የህዝብ ግንኙነትና ቅስቀሳ ዘርፍ አስታወቀ።
ቆይታ ከፕሮፌሠር መስፍን ጋር
«በኢትዮጵያ ሠላማዊ ትግል አያዋጣም የሚባለው ከአሜሪካ ወይም ከአውሮፓ አይደለም» ፕሮፌሠር መስፍን ወ/ማርያም
ፕሮፌሠር መስፍን ወ/ማርያም የሰባዊ መብት ታጋይ በመሆን ለረጅም ዓመታት የኢሰመጉ ፕሬዝዳንት ሆነው አገልግለዋል። ከዛም ቅንጅትን ትተው እስከወጡበት ጊዜ ድረስ በፖለቲካ ትግል ውስጥ ቆይተው የነበረ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ በአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል ናቸው። ፕሮፌሠር መስፍን ከፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ አስራት ጣሴ ጋር በመሆን በአሜሪካን ሀገር በዘጠኝ ስቴቶች ለሚገኙ ደጋፊዎቻቸው ቅስቀሳ ሲያደርጉ ቆይተው ባለፈው ሣምንት ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል። ፕሮፌሠር መስፍን የትጥቅ ትግልን አጠንክረው ሲቃወሙ ይደመጣሉ። ጽዮን ግርማ (የእንቢልታ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ) ስለትጥቅና ሠላማዊ ትግል ስልት ከፕሮፌሠር መስፍን ወ/ማርያም ጋር ቆይታ አድርጋለች።
ከኤርትራ ጋር የመሥራት አስፈላጊነት (አባኪያና ጓደኞቹ)
በኤርትራ በቀር ወደ ኢትዮጵያ ነፃነት የሚወስድ መንገድ የለም
አባኪያና ጓደኞቹ ከካናዳ - ነኀሴ 2000 ዓ.ም.
ኤርትራን እንደ አገር፤ ሻዕቢያን እንደ አጋር
ብዙዎቻችሁ ይሄ ቀጥዬ የምጽፈው ነገር፤ ገና ከርዕሱ ወደላይ ሊላችሁ ይችላል። ለምደነዋል። ሃሳብን በነፃነት በመግለጽ መብት ብናምንም፣ ብዙ ራሳችንን እንደ ዲሞክራት የምንቆጥር ሰዎች በፖለቲካችን ውስጥ የሚሰነዘሩ አንዳንድ ሃሳቦች ሽቅብ ሽቅብ ሲሉን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ተመልክቻለሁ። ሃሳብ እንደተመልካቹ ነው። አንዳንድ ሰዎች የኤርትራ ነገር እይይይይይይ … ሊያሰኛቸው ይችላል። አንድ ምልከታ ነውና አልቃወምም።
ፊፋ ኢትዮጵያን ለስድስት ዓመታት ከማናቸውም ውድድሮች ያግዳታል
ኢትዮጵያ ለ2010 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከሞሮኮ ጋር የምታደርገውን የማጣሪያ ውድድር እንዳትካፈል ታገደች
Ethiopia Zare (ዓርብ ነኀሴ 23 ቀን 2000 ዓ.ም. August 29, 2008)፦ አዲሱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራር በተደጋጋሚ ከዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን (ፊፋ) የተለያዩ ማስጠንቀቂያዎች ቢሰጡትም፣ የፊፋን ውሳኔ ሳያሟላና ምላሽ ሳይሰጥ ቀርቷል። በዚህም ምክንያት ለ2010 እ.ኤ.አ. የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ የታገደች ሲሆን፣ ምናልባትም ለሚቀጥሉት ስድስት ዓመታት ከማናቸውም ውድድሮች ልትታገድ እንደምትችል ፊፋ አስጠንቅቋል።
ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ ሠላም ወይስ ወደ ጦርነት?
(ትንታኔ)በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ሠላም ለማስከበርና ለማስፈን በሚል በሁለቱ ሀገራት ድንበር መሃከል ሰፍሮ የነበረው የተባበሩት መንግሥታት ሠላም አስከባሪ ቡድን (አንሚ) ባለፈው ሐምሌ 23 ቀን 2000 ዓ.ም. ተልዕኮው መገባደዱን ገልጾ ከሰፈረበት ጥሎ መውጣቱ አይዘነጋም። የአንሚ ውሳኔ በርካቶችን ያሳሰበ ጉዳይ ከመሆኑም በላይ ሁለቱ ሀገራት ወደ ሠላም ወይንስ ወደ ጦርነት ነው የሚያመሩት? የሚል ጥያቄ አስከትሏል።
“መንግሥት ሀገሪቱን ማስተዳደር ተስኖታል” የምክክር መድረክ
Ethiopia Zare (ዓርብ ነኀሴ 23 ቀን 2000 ዓ.ም. August 29, 2008)፦ ከ14 ሚሊየን ህዝብ በላይ በረሃብ እየተገረፈና በአንዳንድ የሀገሪቱ ክልሎችም በድንበርና በመሬት ይገባኛል ጉዳዮች፣ በርካታ ዜጎች ደም አፋሳሽ ግጭቶች ውስጥ መግባታቸው፣ የመንግሥትን ሀገር የማስተዳደር ብቃት ጥያቄ ውስጥ እንዳስገባ መድረክ ለዲሞክራሲያዊ ምክክር በኢትዮጵያ አስታወቀ።
የሪፖርተር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ከስድስት ቀን በኋላ በዋስ ተለቀቀ
ሰኞ ጎንደር ፍ/ቤት ይቀርባል
Ethiopia Zare (ዓርብ ነኀሴ 23 ቀን 2000 ዓ.ም. August 29, 2008)፦ ባለፈው ሣምንት ዓርብ ነኀሴ 16 ከቢሮው በፖሊሶች ከአዲስ አበባ የሪፖርተር ጋዜጣ ቢሮ ወደ ጎንደር የተወሰደው ጋዜጣው ባለቤትና ዋና አዘጋጅ አማረ አረጋዊ ረቡዕ ነኀሴ 21 ቀን 2000 ዓ.ም. ምሽት ላይ በስድስተኛ ቀኑ ከእስር በዋስ ተለቅቋል።
የአንድነት ፀሎት ጥሪ ለቴዲ አፍሮ
Ethiopia Zare (ዓርብ ነኀሴ 23 ቀን 2000 ዓ.ም. August 29, 2008)፦ የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) አብሮ አደግ የሆኑትና የቤተልሔም ት/ቤት ተማሪዎች በየእምነታቸው በጾምና በፀሎት ሊያስቡት ማቀዳቸውን ገልጸው፣ በጾምና በፀሎቱ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ የቴዲ አፍሮ አድናቂዎች፣ ዘመድና ወዳጆች በያሉበት በመሆን ዘር፣ ፖለቲካ፣ ኃይማኖት ወደማይለየው ፈጣሪያቸው ይማፀኑ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።
ለአቶ አብርሃም ያየህ ጽሑፍ የተሰጠ ምላሽ (ከተስፋዬ ማሩ)
ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ሳይከበር የጥላቻ ፖለቲካን እና የመሳሰሉትን ለመዋጋት መሞከር ከንቱ ልፋት ነው
በተስፋዬ ማሩ ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ) - ለአቶ አብርሃም ያየህ ጽሑፍ የተሰጠ ምላሽ
በሀገራችን ፖለቲካ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የሚነሱትን የጥላቻ ክስተቶች በተመለከተ ጥቂት ተብሏል። ቀና አመለካከት ያላቸው ሰዎች ጥላቻ ሊያመጣ የሚችለውን ክፉ ውጤት እየጠቀሱ ማስጠንቀቂያ በሞላበት ሁኔታ ለማስተማር ሞክረዋል።
