የዘረፋ ውሎ በእንዳማርያም
(ገብረመድህን አርአያ)
ስብሃት ነጋ ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ በሚታተመው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የሰጠውን ቃለ መጠይቅ አነበብኩት። ስብሃት ነጋ “ኢህዴግን የመሰለ ፓርቲ በአፍሪካ የለም” እና ሌላም ብዙ፣ ብዙ ይላል:: ይዘብታል፣ ይፎክራል፣ ይሸመጥጣል፣ ያቀረሻል፣ በህዝብ ሞራል ላይም ያላግጣል። ብዙም አልደነቀኝም። ስብሃትም ሆኑ የዚህ ፋሺስታዊ ስርዓት አንቀሳቃሾች በብዙሃን ደም ላለፉት አርባ አመታት ታጥበዋል፣ ታሪክ አውድመዋል፣ እጅግ ከፍተኛ ዘረፋ ፈጽመዋል፣ አገር ቆርሰው ሸጠዋል።
ግጭቱን ማን ለኮሰው?
እየሩሳሌም አርኣያ
ቀኑ ማክሰኞ፣ ጥቅምት 22 1998 ዓ.ም፤ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ገደማ... አንድ የከተማ አንበሳ አውቶብስ ተሳፋሪ ሳይጭን ከመርካቶ ተነስቶ ወደ ጎማ ቁጠባ አቅጣጫ በባዶ እየከነፈ ቁልቁል ወርዶ ... ተ/ሃይማኖት ቤ/ክርስቲያን አደባባይን ከዞረ በኋላ ጥግ ይዞ ቆመ። ሹፌሩ አውቶብሱን ገትሮ ወዲያው ከአካባቢው ጠፋ። ለሁለት ሰዓት ገደማ አውቶብሱ እንደተገሸረ ቆየ። ...
99 ቀናት በአዲስ አበባ
ጋዜጠኛው ኤን. ማንጄላ (N. Mandela) በኢትዮጵያ
ሰሎሞን ተሰማ ጂ.
በታኅሣሥ አጋማሽ 1954 ዓ.ም በግርማዊ ንጉሠ ነገሥቱ ጥሪ ተደረገለትና በጥር መጀመሪያ ላይ አዲስ አበባ ገባ። ይህ ሰው በሦስት ወራት ከአንድ ሳምንት (በ98 ቀናት) ቆይታው ወቅት እጅግ የተጣበበ መርሐ ግብር እንደነበረበት ያስታውቃል።
በሲያትል ለኢሳት 50ሺህ ዶላር ተሰበሰበ
የጋዜጠኞቹ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት አለሙና ውብሸት ታዬ ምስል 33ሺህ ዶላር በጨረታ ተወስዷል
Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዚያ 14ቀን 2005 ዓ.ም. April 22, 2013)፦ ትላንት ምሽት በሲያትል ከተማ የኢሳትን ሶስተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ አርቲስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው ታማኝ በየነ እና አቶ መንሱር ኑር በክብር እንግድነት የተገኙበት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ምሽት ላይ 50ሺህ የአሜሪካን ዶላር መሰብሰቡ ታወቀ።
ደሳለኝ ደበረኝ ደሳለኝ
አባጅፋር
ፊት ላይ ያሉት ቀዳዶች የተበጁት ለመተንፍሰ፣ ለመብላት፣ ለመናገርና ለመናፈጥ ነው። እንዳስፈላጊነታቸው እንጠቀመባቸዋለን። በዚህም ምክንያት ሰውየው ተናገሩ።
የግፍ ጽዋ ሲበዛ አያቀረሽም እንዴ?
ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)
ዋናው የኢትዮጵያ ህዝብ ችግርና መፍትሄ ያልተገኘለት ነገር፤ የህውሀት ገዢ ቡድን፤ አሁን አለማችን ካለችበት የስልጣኔና የአስተሳሰብ እድገት ደረጃ እጅግ ወደ ኋላ በቀረ እምነትና ፍልስፍና ላይ ተጣብቀው በመቅረታቸው፤ የሁሉ ነገር መፍትሄ ጉልበት ብቻ ነው፤ ጡንቻ ብቻ፤ ጡንቻን አፈርጥሞ መገኘት ብቻ ነው።
ደሞዝ፣ መንጃ ፈቃድና ንግግር
አባ ጅፋር
ሰው ይናገራል። ፍሬ ነገር የሆነ፤ ገለባ የሆነ ነገር ይናገራል። ገለባብም ጥቅም አለው። ከብት ይመግባል። ከብቶችም ሆዳቸው ይሞላል።
ፍለጋ
ተሾመ ገብረስላሴ
፩
በቅድሚያ ስለራሴ ልንገርህ። አለመኖርን አላውቀውም ላውቀውም አልጓጓም። በመኖር ቤተ-መቅደስ ውስጥ ነኝ። መኖርን እቀድሳለሁ። መኖርን አሞካሻለሁ። እንዳንተው ስለመኖር አዜማለሁ።
ነገም አንድ የሚያደርገን ቅመም ምን ይሆን?
ይኸነው አንተሁነኝ
የዚህ ጽሁፍ መነሻ ሰሞኑን የህወሓት ደጋፊ የሆኑ ራዲዮኖች ጋዜጦች ድረ ገጾችና መወያያ ክፍሎች ከአማራው ወገናችን መፈናቀል ጋር በተያያዘ እያሉት ያለው ፍጹም ሚዛን የጎደለው ሀዘኔታ ያልዳሰሰው ከዚያም ሲከፋ ጭካኔ የተሞላበት ንግግር ነው።
ከማግለል ማሳተፍ ይቅደም
አዋሽ አዳል
ሰሞኑን በአንድ ድረገጽ ላይ "የኢሳት 3ኛ አመት ክብረ-በዓል የሙስሊሞች ብቻ ነው እንዴ?" በሚል ርዕስ ከልጅ ተክሌ የፃፈውን ካየሁ በሁዋላ ፀሐፊውን በልቤ ወቅሼ አለፍኩት። በነጋታው በሌላ ድረገፅ ላይ ሌላ ርዕስ ይዞ፣ ትንሽ ተቀይሮ አየሁት።
