ወ/ሮ አዜብ ስለየትኛው ድህነታቸው ነው ሊነግሩን የፈለጉት?!
ፍቅር ለይኩን
በ2000 ዓ.ም. ይሁን በ2001 ለጊዜው እርግጠኛ ባልሆንም ግን ከሁለቱ በአንዱ ዓመት ይመስለኛል። በመዲናችን በአዲስ አበባ ላይ በተካሄደ ዓመታዊው የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ላይ የአፍሪካ ቀዳማይ እመቤቶችም በበኩላቸው ከባሎቻቸው እኩል አፍሪካውያን እመቤቶች ስለ አፍሪካ ጉዳይ ተፈጥሮ የተቸራቸውን የሴትነት ጥበብና ብልሃታቸውን በመጠቀም ኁልቆ መሣፍርት ለሌለው ለአፍሪካና ለአፍሪካውያን ችግሮችና እንቆቅልሾች ምክር ቢጤ ለመለገስና መፍትሔ ለማመላከት እነርሱም በተራቸው ለስብሰባ ተቀምጠው ነበር።
አፈወርቆች
ኤፍሬም እሸቴ
ከሰሞኑ "ፋኖስና ብርጭቆ" የምትባለውን የክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤልን ግጥም በፌስቡክ ገጼ ላይ ለጥፌ ነበር። "ስንቶቻችሁ ይህንን የክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤልን ግጥም ታስታውሣላችሁ? በልጅነቱ ይህንን በቃሉ ይወጣ የነበረ አሁንም ያልረሣ ካለ እነሆ ካንገቴ ዝቅ ብዬ አክብሮቴን ልግለጽ" ከሚል ማስታወሻ ጋር።
በቤንች ማጂ አማርኛ ተናጋሪዎችን ማፈናቀል ዳግም ተጀመረ
(ፍኖተ ነፃነት ቁ. 71፣ መጋቢት 29 ቀን 2005)፦ በደቡብ ክልል ቤንች ማጂ ዞን በሚገኘው ሜኒት ወልድያ ወረዳ በተለይም ዘንባብና አርፋጅ ቀበሌ ነዋሪዎች በካከል ከ350 በላይ የአማርኛ ተናጋሪ ዜጎች ተፈናቅለው በወረዳው አካባቢ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
ትግል ... ሽንፈት፤ ... ድል፤ ሽንፈት ...
ተመስገን ደሳለኝ
ከምሽቱ አንድ ሰአት አልፏል፤ የእጅ ስልኬ ደጋግሞ ቢጮኽም ትኩረት አልሰጠሁትም። ከጥቂት ሰከንዶች ፋታ በኋላ የቢሮዬ ስልክ ጮኸ፤ አነሳሁት። ለካስ እንዲህ በአንዱ አልመልስ ስላት፣ በሌላው እያፈራረቀች የምትደውለው ዕድሜዋ ወደ ሰባ እየተጠጋ ያለው አሮጊቷ እናቴ ኖራለች፦
ዳምጠው ወያኔ/ኢሕአዴግና አፈና በኢትዮጵያ
ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም
በቀልድ ልጀምር፤ አንድ ጮሌ የአስመራ ልጅ የእኔ ተማሪ ነበር፤ አንድ ጊዜ የጂኦግራፊ ክፍል ተማሪዎች አንድ ጃፓናዊ አስተማሪ ለመሸኘት ግብዣ አድርገው ነበር፤ በግብዣው ላይ የጠቀስሁት ነገረኛ የአስመራ ልጅ (የአስመራ ልጅ የምለው ላርቀው ፈልጌ እንዳይመስላችሁ፤) በአስተማሪዎች ላይ ቀልድ ያሰማ ነበረ፤ ስለኔ ሲናገር፤– መስፍን ወልደ ማርያም የቢሮውን በር ሁልጊዜ ክፍት አድርጎ የሚቀመጠው ለምንድን ነው? ይልና እሱው ሲመልስ፣
ድሀ ከሆኑ አይቀርስ - ልክ እንደ አቶ መለስ
ኤፍሬም እሸቴ
ሰሞኑን በተካሔደው የኢሕአዴግ ጉባዔ ላይ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ያደረጉትና በኢቲቪ የዜና ዕወጃ ላይ የቀረበው ንግግራቸው የማኅበራዊ ድረ ገጾች የመወያያም የመሳሳቂያም የመሳለቂያም ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ ነበር። "#SomeoneTellAzebMesfin" በሚል "ሐሽ ታግ/ #Hashtag" (ቅምር-ቃል ልበለው?) በትዊተር ላይ ኢትዮጵያውያን የግል ሐሳባቸውን ሲሰጡበት የቆዩት የወይዘሮዋ ንግግር ያተኮረው በአቶ መለስ ደሞዝና ድህነት ላይ ነበር።
ዞምቢዎቹ እየመጡ ነው!
ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)
ሐምሌ 11 ቀን ዓ.ም. በታተመችው በ"አዲስ ነገር" ጋዜጣ ወዳጄ መስፍን ነጋሽ "ዞምቢዎቹ" በሚል ርዕስ ዛሬም ድረስ ከህሊናዬ ያልጠፋ ድንቅ ጽሁፍ አስነብቦን ነበር (የዚህ ፅሁፍ ሃሳብም ከዚሁ የተናጠቀ ነው)። ይኸ ከሆነ ድፍን ሶስት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት ብቻ ቀርቶታል። "አዲስ ነገር" ም ወደ ታሪክነት ከተቀየረች ሁለት ዓመት አልፏታል። ለምን? ... ዞምቢዎቹ ድል ስለነሷት፤ እንዴት? ማንም ዞምቢዎቹን ድል አድርጎ ስለማያውቅ። ዞምቢ ምንድር ነው? ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ እንዲህ ገልጿቸዋል፦
የአማራው መከራ ላገሩ ስለሠራ
ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ጅግሳ
እንሁን ቀና ሰው፣ እውነት እንናገር፣
ለእውነት ጥብቅና፣ ሃቁን አስቀድመን፣
ፖለቲካን ወዲያ፣ ትንሽ አቆይተን፣
እስቲ እንተባበር ሃሰት ላይ አድመን።
ነገን የተሻለ ቀን ለማድረግ፤ ዛሬ ነው መነሳት፤
ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)
ይድረስ ለሀገሬ ወጣቶች
ከዘር ማንነታችን በፊት ሰብአዊ ሰውነታችን፤ ከጎጠኝነታችን በፊት ኢትዮጵያዊነታችን፤ ከሸፍጥ፤ ከተንኮል፤ ከመሰሪነታንችን በፊት ቅንነታችን፤ ከፍርሀታችን በፊት ድፍረታችን፤ እርስ በርስ ከመጠራጠራችን በፊት መተማመናችን፤ ከመፍረክረካችን በፊት በጽናት መቆማችን፤ ከልዩነታችን በፊት አንድነታችን፤ ወያኔ ዛሬ ኢትዮጵያውያንን ከከተተበት መቀመቅ ውስጥ የሚያወጣን ብቸኛ መፍትሄ ከላይ የደረደርኩት ነገር ብቻ ይመስለኛል።
መልካም መሪ ማግኘት ምንኛ መታደል ነው?!
ታምሩ ገዳ
በየትኛውም የእድገት ደረጃ ይሁን የፖለቲካ አመለካከት ወይም የሃይማኖት ስርአት ውስጥ ለሚገኝ ማህበረሰብ ሁነኛ መሪ ማግኘት ከእድሎች ሁሉ ትልቁ እድል ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። አይደለምም።
