ዳምጠው ወያኔ/ኢሕአዴግና አፈና በኢትዮጵያ
ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም
በቀልድ ልጀምር፤ አንድ ጮሌ የአስመራ ልጅ የእኔ ተማሪ ነበር፤ አንድ ጊዜ የጂኦግራፊ ክፍል ተማሪዎች አንድ ጃፓናዊ አስተማሪ ለመሸኘት ግብዣ አድርገው ነበር፤ በግብዣው ላይ የጠቀስሁት ነገረኛ የአስመራ ልጅ (የአስመራ ልጅ የምለው ላርቀው ፈልጌ እንዳይመስላችሁ፤) በአስተማሪዎች ላይ ቀልድ ያሰማ ነበረ፤ ስለኔ ሲናገር፤– መስፍን ወልደ ማርያም የቢሮውን በር ሁልጊዜ ክፍት አድርጎ የሚቀመጠው ለምንድን ነው? ይልና እሱው ሲመልስ፣
ድሀ ከሆኑ አይቀርስ - ልክ እንደ አቶ መለስ
ኤፍሬም እሸቴ
ሰሞኑን በተካሔደው የኢሕአዴግ ጉባዔ ላይ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ያደረጉትና በኢቲቪ የዜና ዕወጃ ላይ የቀረበው ንግግራቸው የማኅበራዊ ድረ ገጾች የመወያያም የመሳሳቂያም የመሳለቂያም ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ ነበር። "#SomeoneTellAzebMesfin" በሚል "ሐሽ ታግ/ #Hashtag" (ቅምር-ቃል ልበለው?) በትዊተር ላይ ኢትዮጵያውያን የግል ሐሳባቸውን ሲሰጡበት የቆዩት የወይዘሮዋ ንግግር ያተኮረው በአቶ መለስ ደሞዝና ድህነት ላይ ነበር።
ዞምቢዎቹ እየመጡ ነው!
ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)
ሐምሌ 11 ቀን ዓ.ም. በታተመችው በ"አዲስ ነገር" ጋዜጣ ወዳጄ መስፍን ነጋሽ "ዞምቢዎቹ" በሚል ርዕስ ዛሬም ድረስ ከህሊናዬ ያልጠፋ ድንቅ ጽሁፍ አስነብቦን ነበር (የዚህ ፅሁፍ ሃሳብም ከዚሁ የተናጠቀ ነው)። ይኸ ከሆነ ድፍን ሶስት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት ብቻ ቀርቶታል። "አዲስ ነገር" ም ወደ ታሪክነት ከተቀየረች ሁለት ዓመት አልፏታል። ለምን? ... ዞምቢዎቹ ድል ስለነሷት፤ እንዴት? ማንም ዞምቢዎቹን ድል አድርጎ ስለማያውቅ። ዞምቢ ምንድር ነው? ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ እንዲህ ገልጿቸዋል፦
የአማራው መከራ ላገሩ ስለሠራ
ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ጅግሳ
እንሁን ቀና ሰው፣ እውነት እንናገር፣
ለእውነት ጥብቅና፣ ሃቁን አስቀድመን፣
ፖለቲካን ወዲያ፣ ትንሽ አቆይተን፣
እስቲ እንተባበር ሃሰት ላይ አድመን።
ነገን የተሻለ ቀን ለማድረግ፤ ዛሬ ነው መነሳት፤
ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)
ይድረስ ለሀገሬ ወጣቶች
ከዘር ማንነታችን በፊት ሰብአዊ ሰውነታችን፤ ከጎጠኝነታችን በፊት ኢትዮጵያዊነታችን፤ ከሸፍጥ፤ ከተንኮል፤ ከመሰሪነታንችን በፊት ቅንነታችን፤ ከፍርሀታችን በፊት ድፍረታችን፤ እርስ በርስ ከመጠራጠራችን በፊት መተማመናችን፤ ከመፍረክረካችን በፊት በጽናት መቆማችን፤ ከልዩነታችን በፊት አንድነታችን፤ ወያኔ ዛሬ ኢትዮጵያውያንን ከከተተበት መቀመቅ ውስጥ የሚያወጣን ብቸኛ መፍትሄ ከላይ የደረደርኩት ነገር ብቻ ይመስለኛል።
መልካም መሪ ማግኘት ምንኛ መታደል ነው?!
ታምሩ ገዳ
በየትኛውም የእድገት ደረጃ ይሁን የፖለቲካ አመለካከት ወይም የሃይማኖት ስርአት ውስጥ ለሚገኝ ማህበረሰብ ሁነኛ መሪ ማግኘት ከእድሎች ሁሉ ትልቁ እድል ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። አይደለምም።
የትናንቷን እሁድ በወፍ በረር ስንቃኛት
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
ዛሬ እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር እሁድ መጋቢት 15 ቀን 2005 ዓ.ም. ነው። የዚህችን ዕለት ውሎየን ነው እንግዲህ የማካፍላችሁ። እኔም እንዳቅሜ የቤተሰቤን ፍላጎት አፍኜ አልጀዚራን ብቻ በመክፈት በማየው ነገር ሁላ በንዴት ስፎገላ ነው የትም ሳልሄድ ቤቴ ተከርችሜ የዋልኩ።
ዘጠኝ ቦላሌ ...
ይኸነው አንተሁነኝ
የክህደት ቁልቁለት አሉ ታላቁ ምሁር!!! የክህደት ውርስ የበቀል ዛር እያስጎራ፣ የሚሆነውንም የማይሆነውንም እያስቀባጠረ ሃያ አንድ ዓመት እያንደረደረ ወርውሮ እዚህ ያደረሰው ህወሓት ስለመድረሱ እንጅ ወደ ፊት ስለሚሆነው ወይም ስለሚያደርገው ከግምት በላይ የሚያውቀው ነገር ያለ አይመስልም።
ኢትዮጵያዊ መልኮች በአሜሪካ - መልክአ ኢትዮጵያ - ፭
ጽዮን ግርማ

"... እንዴት አድርጌ ደመወዜን እኮ አልሰጠችኝም፤ ቆይ ዛሬ ቆይ ነገ እያለች ይኸው እስከ አሁን ታጉላላኛለች። ማታ ማታ በገባች ቁጥር እስከሚበቃት እነግራታለኁ፤ እርሷ መቼ ሰበብ ታጣለች። ቢጨንቀኝ ላገናኘኝ ልጅ ደውዬ ነገርኁት፤ ይብሱኑ እርሱም እኔም ያበደርኋትን አልከፈለችኝም አለኝ። ወይ አሜሪካ! ጉዷን አየኁላት።" መቼም መመረሯ መግለጫ የለውም። ...
