ኢትዮጵያዊ መልኮች በአሜሪካ - መልክአ ኢትዮጵያ - ፪

ጽዮን ግርማ
... በርካቶች ሥራ ፍለጋ በሚሰደዱባት የዓለም ቁንጮ በሆነችው ሀገረ አሜሪካ፣ ገላቸውን ለሽያጭ ላቀረቡት ወጣት እንስቶችስ "አይ የእንጀራ ነገር" ስል ደረቴን ልድቃላቸው ይሆን? ጉዳዩ የእንጀራ አይመስልም፤ እናም ደረት የመድቃቱ ነገር አስፈላጊ አልመሰለኝም። ...
"ከእኔ ልጅ ጋር ሐረር ከተማ ውስጥ አራት ሰው በፓሊስ ነዳጅ እየተደፋበት በእሳት ተቃጥሎ ሞቷል"
ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ (ከሐረር የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈፅሞባቸው የተባረሩ አዛውንት)
ፍኖተ ነፃነት (መጋቢት 7 ቀን 2005 ዓ.ም.)፦ "ልጄ በእሳት ተቃጥላ እንድትሞት ተደርጋ፣ ቤቴን ተነጥቄና ንብረቴ ወድሞ ከሐረር ተባረርኩ" ሲሉ አንዲት የ67 አመት ባልቴት በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ አስታወቁ።
ኢትዮጵያዊ መልኮች በአሜሪካ - መልክአ ኢትዮጵያ ፩
ጽዮን ግርማ
የሚሳሳሙት ደንበኞቻቸው ወንድ እና ሴት ብቻ አይደሉም። አንዳንዴ ወንድና ወንድ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሴትና ሴት ሊሆኑ ይችላሉ። በዲሲ፣ በሳንፍራንሲስኮ፣ በቺካጐ እና በአትላንታ ጉብኝቴ ወንድ ለወንድ እና ሴት ለሴት ሲሳሳሙ በዐይኔ ተመልክቻለሁ። ድርጊቱን ማየት እንደመስማት እና ማውራቱ ቀላል አይደለም። ለእንደኔ ዓይነቷ ሊብራል ነኝ ባይ እንኳን መሣቀቁ ነፍስን ከሥጋ ያላቅቃል። ግን ደግሞ ያየሁትን ጽፌ ለማስነበብ ጓጉቼ ስለምጓዝ እየተሳቀቅኹም ቢሆን እንዲህ ያሉትን ቦታዎች ጐብኝቻለሁ። ...
በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነታቸው የማያምኑ በኢትዮጵያ ቅርሶች ስም መጠቀም የለባቸውም
ቸሩ ላቀው
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገሮች ቀደምትነት ያላት ሀገር መሆኗን ራሳችንን ከፍ ከፍ ለማድረግና ለመመጻደቅ ሳይሆን ታሪክ የመሰከረላት ናት።
የባለሥልጣኖች ደመወዝና ታክስ ክፍያ
ከበደ ኃይሌ
በዓለም ዙሪያ በደረሰው የኢኮኖሚ መንኮታኮት ምክንያት እንኳን በድህነት የላሸቁ አፍሪካ አገሮች ቀርቶ በሃብት የዳበሩ የምዕራቡ አሁጉራትን ጨምድዶ በመያዙ ህዝባቸው በኑሮ ውድነትና ከስራው ተፈናቅሎ የመንግስት፤ የማህበረሰብ፤ ...
"መሪዎቻንን የት አሉ?"
በልጅግ ዓሊ
"እኔ ምን አገባኝ የምትለው ሐረግ፣
እሱ ነው ሃገሬን ያረዳት እንደበግ፣
የሚል ግጥም ልጽፍ፣
ስሜት አንዘርዝሮኝ ብድግ አልኩኝና፣
ምን አገባኝ ብዬ ቁጭ አልኩ እንደገና።" ኑረዲን ዒሣ
ጀርመን ፍራንክፈርት በታማኝ በየነ ስብሰባ ታምሳ ከረመች። ከብዙ ጊዜ በኋላ እንደገና ብዙ የፍራንክፈርት አካባባቢ ነዋሪዎች ተገናኝን። አልፎም ተርፎም ችግራችንን ተወያየን። በዚሁ አጋጣሚ ይህንን ዝግጅት ላዘጋጁት ለወ/ሮ አሳየሽኝና ለአቶ ጥላሁን ምስጋናየን በግሌ አቀርባለሁ።
ሰንሰለቱም ይጠብቃል፤ እርግጫውም ይከፋል ... ካልተነሳን!
ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)
አስተዳደር በየፈርጁና በየደረጃው፤ ከብሄራዊ መንግስት እስከ ታች የቀበሌ አመራር በመጥፎም ይሁን በደግ መልኩ በዜጎች ህይወት የለት ተለት እንቅስቃሴና አኗኗር ላይ ቀጥተኛተጽእኖ እንደሚኖረው ሁሉም ሰው እየኖረው ስለሚያየው ማስረጃ መደርደር ላያስፍልገው ይችላል።
ሮም: እንደጎበኘዃት
ኤፍሬም እሸቴ
ከዚህ በታች የምታነቧቸው ሁለት ጽሑፎች በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጡ፣ ስለ ሮም ካየኹት የጻፍኳቸው የግል ጉብኝቴ ትውስታዎች ናቸው። የመጀመሪያው ጽሑፍ ሮም ስለነበረው የአክሱም ሐውልትና ስለ ኮሎሲየም የሚናገር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሁሌም ስለሚገርኝ የሮማ ዋሻ ካታኮምቤ ያትታል። መልካም ንባብ!
ሁጎ ቻቬዝ ሚሊኖችን “ያላቀሱ” የዘመኑ ታላቅ መሪ
ታምሩ ገዳ
ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ የዜና እረፍታቸው ለህዝባቸው እና ለመላው ዓለም ይፋ የተደረገው የቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት ሁጎ ቻቬዝ በብዙዎች ዘንድ አስገራሚ እና አወዛጋቢ ባህሪ የተላበሱ መሪ ነበሩ። ያቺ በላቲን አሜሪካ ውስጥ በተፈጥሮ ጋዝ ሃብቷ ቀዳሚ ስፍራ ያላት ቬንቩዌላን ላለፉት 14 አመታት በሶሻሊስታዊ ርእዮት ዓለም አካሄድ የመሯት ቻቬዝ ላለፉት ሁለት አመታት ከካንሰር ህመም ጋር ውጊያ ቢያደርጉም በተወለዱ በ58 አመታቸው የሚወዱት ህዝባቸውን እና ከብዙዎች አዕምሮ የማይጠፉ አሰገራሚ ትዝታዎቻቸውን ጥለው ወደ ማይቀረው ዓለም ሄደዋል።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጥሪ!
"ክርስቲያኑ ወገናችን፣ ...ተሰለፍ ከጎናችን!"
ሰሎሞን ተሰማ ጂ.
እነዚህ ጎሰኛ የሳዑዲ ወገኖች/ቅጥረኞች በጫሩት እሳት ነው-ዛሬ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በማዕከላዊና በቃሊቲ እስር ቤቶች የሚማቅቁት። እነዚህ ዋሀቢስቶች በጎነጎኑት ከንቱ ደባ ነው፣ ዛሬ የእስልምና ተከታዮች የገዛ መጅሊሳቸውን በመስኪዶቻቸው እንዳይመርጡ የተደረጉት። ያሳዝናል። ...
