ወያኔና እምነት
ቸሩ ላቀው
በመንግሥት አመራር ላይ የተቀመጡ ቡድኖችና በኃይማኖት አመራር ላይም የተቀመጡ የኃይማኖት መሪዎች በየፊናቸው የሕዝብን አደራ በኃላፊነት ተቀብለው በሀገሪቱ ባለው ሕገ መንግሥትና በኃይማኖቱ ሕግ መሠረት በሐቅና ለሕቅ ብለው ምለውና ተገዝተው ሕዝብን ለማገልገል የተቀመጡ ናቸው።
የሚሳናቸው የለም
ቸሩ ላቀው
ሿሚ፣ ሻሪ፣ ሀገር መከፋፈልና መገነጣጠል የነርሱ ተግባር ሆኗል። መለስን ሾሙብን፣ ሀገርን ገንጥለው ኢሳያስ አፈወርቂን ኤርትራን ይዘህ ራስህን ቻል አሉት። ከመለስ ሹመት ጋር ኢትዮጵያን በጎሣ ከፋፍለው እያወደሟትና እያደቀቋት ነው።
በስዊድን የስደተኞች ማኅበር ከስደተኞች ጉዳይ አጥኚ ተወካዮች ጋር ውይይት አደረገ
Ethiopia Zare(እሁድ የካቲት 17 ቀን 2005 ዓ.ም. February 23, 2013)፦ በስዊድን የሚገኘው የኢትዮጵያ ስደተኞች ማኅበር የኢትዮጵያን ጉዳይ ከሚከታተሉ የኢሚግሬሽን ተወካዮች ጋር ፌብሪዋሪ 6 ቀን 2013 ዓ.ም ውይይት አደረገ። ይህንኑም ጉዳይ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ እስር ቤት ከርመው የተፈቱት ጋዜጠኞች ማርቲን ሼቢ እና ዮሃን ፐርሾን ለኢሚግሬሽን ባለስልጣናት እንዳስረዱ አቶ ፋንታሁን ገልጸዋል።
አስሩ የጽልመት ቀናት በኢትዮጵያ
(ከየካቲት 8/1929 - የካቲት 17/1929 ዓ.ም)
ሰሎሞን ተሰማ ጂ.
በመስከረም 1927 ዓ.ም የወጣው Detroit Times — (Sept. 22, 1935, p. 3) መጽሔት ከአንድ ታላቅ ሳይቲስትና የፈጠራ ባለሙያ ጋር የኢትዮጵያንና የጣሊያንን ወረራ አስመልክቶ ቃለ-ምልልስ አድርጎ ነበር።
ወላጆችና መሪዎች
ቸሩ ላቀው
ለዚህ የተቀደሰ ተግባርና ከባድ ኃላፊነትን ለሚጠይቅ ሥልጣን መታጨት ያለባቸው የሀገር መሪዎች ማሟላት ያለባቸው መመዘኛዎች በርካቶች ቢሆኑም በኔ እይታ አንዳንዶቹን ከወላጆች ጋር እያስተያየሁ ለመጠቃቀስ እፈልጋለሁ።
ድንቄም ምርጫ!
ይኸነው አንተሁነኝ
ላንዲት ሀገር መሰረታዊ የእድገት ኃይል ያላት የተፈጥሮ ሃብትና የሕዝቦቿ ሁለንተናዊ ብቃት ናቸው። የሕዝቦቿን ሁለንተናዊ ብቃት ለመገንባት ደግሞ ካሏት የትምህርት ተቋማትና የትምህርቱ ሥርዓት በተጨማሪ በሕዝቦቿ መካከል ያለው የባህል፣ የኃይማኖትና የአኗኗር መስተጋብር የሚያበረክቱት አስተዋጽኦና በዚሁ ሳቢያም የሚገኘው ቀጥተኛ ያልሆነ የእውቀትና የልምድ አቅምና ዝውውሩ የሚናቅ አይሆንም።
የህወሓት ጉዞ የርስ በርስ መበላላት ታሪክ ነው
ትዕዝብት አድማሱ
የትግራይ መሳፍንት እርስ በራሳቸው ሲናቁሩና ሲገዳደሉ ያየች አንዲት የጎጃም አዝማሪ ስታንጎራጉር "ጎጃሜ ቡዳ ነው ስትሉ ስትሉ፣ አላየህም ወይ ትግሬ እርስ በርስ ሲባሉ" በማለት ትልቁ የታሪክ ጠባሳ በአንዲት ዓረፍተ ነገር አጠቃለለች ይባላል። ይህ የትናንት ታሪክ ነው። ዛሬስ ምን እየተደረገ ነው ያለው?
ህወሓት ሊወድቅ ነው
(ለነፃነታችን እንጨክን - እንቆሽሽ!)
ያሬድ አይቼህ
ገዢው ፓርቲ ለጥገናዊ ለውጥ ምንም አይነት ቦታ የማይሰጥ መሆኑን በተደጋጋሚ ግልጽ አድርጓል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም ይህንኑ ጉዳይ አስምረውበታል። ከዚህ የተነሳ ከገዢው ፓርቲ ጋር የነበረው የምርጫ ትግል በአጠቃለይ መክኗል። ዛሬ አገራችን ሙሉ በሙሉ ወደ ነፃነት ትግል ምዕራፍ ገብታለች።
የዳውሮ ሕዝብ ያካሄደው መራር ትግልና ውጤቱ
ዋካ ከስዊድን
በደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘው የዳውሮ ዞን ሕዝብ ለህወሓት መራሹ መንግሥት በተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርቦ እንደነበርና ሕዝቡ ላቀረበው ጥያቄ ተመጣጣኝ ምላሽ በመነፈጉ በመንግሥት ላይ በተለያዩ ጊዜያት ማመጹን በተለያዩ የብዙኃን መገናኛዎች ሲዘገብ ሰንብቷል።
ውሸት! ውሸት! ውሸት! ውሸት! ውሸት!
ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)
የዋሾ መንግስት ጩኸት
ሰሞኑን ወያኔ የተለመደ የውሸት ድራማ ሰርቶ፤ ሲሞን በረከት በሚባል፤ የማያምር፤ የማያፍር የኤርትራ ሰው፤ ጭራሹን አማራ ነኝ ብሎ እንዲያታልል ወያኔ የቀጠረው ባእድ የፕሮፓጋንዳ ሚኒስቴር፤ የሀሰት ፊልም ደራሲና የበላይ አዘጋጅ የሆነ ሰው፤ ሰርቶ ጨርሶ ያሳለፈውን "ጂሀዳዊ ሀረካት" በሚል ርእስ ባለፉት ሀያ ሁለት አመታት ከሚያደርገው ነገር የተለየ ባይሆንም፤ ቀጣይ የማናደድ ስራቸውን ለኢትዮጵያ ህዝብ አቅርበው ነበር።
